2013 (እ.አ.አ)
እባክህ ልቤን ፈውሰው
ማርች 2013


ወጣቶች

እባክህ ልቤን ፈውሰው

ወንድሜ በሞተበት አመታዊ በዓል፣ እርሱ ከሞተ በኋላ ስለነበረኝ ጊዜ አስተዋውል ነበር። ሀይለኛ ሀዘን ስለነበረኝ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር ስለሰጠኝ በረከቶችም አስታወስኩኝ።

የምንወደው ሰው ሞት በረከቶችን ያመጣል የሚለውን የሰዎች አባባል በምንም አይገባኝም ነበር። በዝልቅ በሚጎዳኝ ነገር እንዴት ለመደሰት እና ምስጋና እንደሚሰማኝ ምንም ሊገባኝ አልቻለም። በአንድ ምሽት ግን ያ አስተያየቴን በሙሉ ቀየረው።

በምሽት መካከል ከዚህ በፊት ተሰምቶኝ የማላውቀው ከባድ ሀዘን በልቤ እየተሰማኝ ከእንቅልፍ ተነሳሁ። ህመሙ ለማስተንፈስ ያስቸግረኝ ነበር። ተንበረከኩኝ እና ወደ ሰማ አባት እያለቀስኩኝ ጸለይኩኝ። በህይወቴ በሙሉ የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ስላለው ታምራታዊ የመፈወስ ሀይል እማር ነበር። አሁን እምነቴ በተፈተና ላይ ነበር። በእውነት አምናለሁን? ልቤን እንዲፈውስልኝ የሰማይ አባቴን ጠየኩት። በብቻዬ ለመሸከም ህመሙ ከባድ ነበር።

ከዚያም የሰላም፣ የመፅናናት፣ እና የፍቅር ስሜት በሰውነቴ በሙሉ አለፈ። እግዚአብሔር እንዳቀፈኝ አይነት እና ከተሰማኝ ከባድ ህመም እንደሚጠብቀኝ አይነት ስሜት ተሰማኝ። ወንድሜ ናፍቆኝ ነበር፣ ግን በተለየ አስተያየት ለመመልከት ቻልኩኝ። ከዚህ አጋጣሚ የተማርኩት ብዙ ነበሩ።

የጌታ ፍቅር እና ሰላም እንደሚገኙ አውቃለሁ። ማድረግ የሚያስፈልገንም መቀበል ብቻ ነው።

አትም