2013 (እ.አ.አ)
ዝም በል፥ ፀጥ በል
ማርች 2013


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ መጋቢት 2013 (እ.አ.አ)

ዝም በል፥ፀጥ በል

ምስል
ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን።

ከትንሽ አመቶች በፊት አንድ ቀን፣ በቢሮ ስራዎችን ከፈጸምኩኝ በኋላ፣ በሶልት ሌክ ስቲ ሽማግሌዎችን በሚንከባከቡበት ቦታ ውስጥ የሚኖሩትን እድሜአቸው የገፉትን ባሏቸው የምተባቸውን ሴት እንድጎበኝ ጠንካራ ስሜት መጣብኝ። ወደዚያም ወዲያው መኪና በመንዳት ሄድኩኝ።

ወደ ክፍላቸው ስገባ፣ ባዶ ነበር። የት እንዳሉ ሰራተኛውን ጠይቄ፣ ወደ ማረፊያው ክፍል ተጠቆምኩኝ። በዚያም ቦታ እኚውን አስደሳች እህትና ሌላ ጓደኛ አገኘሁ። ደስተኛ ንግግሮችን አደረግን።

ስንነጋገርም፣ ኮካ ከሚሸጥበት መሺን የሚጠጣውን ለማግኘት አንድ ሰው ወደ በሩ መጣ። ተመለከተኝና እንዲህ አለ፣ “አንት ቶም ሞንሰን ነህ።”

“አዎን”። “እና አንተም የሄምንግዊይ ቤተሰብ አባል ትመስላለህ” ብዬ መለስኩኝ።

እርሱም ከብዙ አመታት በፊት ኤጲስ ቆጶስ በሆንኩበት ጊዜ እንደ አማካሪዬ አብረን ያገለገልነውና ጂን ብዬ እጠራው የነበርኩት የአልፍሬድ ዩጂን ሄምንግዌይ ወንድ ልጅ ስቲቨን ሄምንግዌይ እንደሆነ አሳወቀኝ። ስቲቨንም አባቱ በዚህ ቦታ ውስጥ እንደ ሚኖር እና ለሞት እንደቀረበም ነገረኝ። ጂን ስሜን ይጠራ ነበር፣ እናም ቤተሰቡ ከእኔ ጋር ለመገናኘት ፈልገው ነበር ነገር ግን የስልክ ቁጥሬን ለማግኘት አልቻሉም ነበር።

የማነጋግራቸውን ይቅርታ እንዲያደርጉልኝ ጠየቅሁኝ እናም ከስቲቨን ጋር የድሮ አማካሪዬ ወደነበረበት፣ ባለቤቱ ከብዙ አመታት እፊት ሞታ ስለነበር፣ ልጆቹም ወደተሰበሰቡበት ክፍል ወዲያው ሄድኩኝ። የቤተሰብ አባላትም እኔ ከስቲቨን ጋር በማረፊያው ክፍል ውስጥ መገናኘቴን የእነርሱ አባት ከመሞቱ በፊት እኔ ላየው እንድችል የነበራቸውን ታላቅ ፍላጎት እና የእርሱን ጥሪ ለመመለስ የሰማይ አባት መልስ እንደሰጠበታይነት ነበር የተመለከቱት። እኔም ይህ እንደሆነ ተሰምቶኝ ነበር፣ ምክንያቱም ስቲቨን በጉብኝት በነበርኩበት ክፍል ውስጥ በዚያ ጊዜ ባይገባ ኖሮ፣ ጊን በዚያ ቦታ ውስጥ እንደነበረ አላውቅም ነበር።

በረከት ሰጠነው። የሰላም መንፈስ አሸነፈ። አስደሳች ጉብኝት ነበረን፣ ከዚያም ወጥቼ ሄድኩኝ።።

በሚቀጥለው ጠዋት፣ እልጁ እና ከእኔ በረከትን ከተቀበለ ከ20 ደቂቃ በኋላ ጂን ሄምንግዊይ እንደሞተ የሚገልጽ የስልክ ጥሪ አገኘሁ።

የመንከባከቢያውን ቦታ እንድጎበኝ እና ውድ ጓደኛዬን አልፍሬድ ዩጂን ሄምንግዌይ ወደሚገኝበት በመምራት ላነሳሳኝ ከሰማይ አባታ ለመጣው የመመሪያ መነሳሻ ስሜት የጸጥታ ምስጋና ጸሎት አቀረብኩኝ።

እኔም—በመንፈስ ብርሀን እየተደሰትን፣ በትሁት ጸሎት በመሳተፍ፣ እና የክህነት በረከትን በመስጠት በምናሳልፍበት—በዚያ ምሽት የጂን ሄምንግዌይ ሀሳቦች “Master፣ the Tempest Is Raging” በሚለው መዝሙር ውስጥ ያሉትን ቃላት እንደሚደግም ለማሰብ እፈልጋለሁ።

ቆይ፣ የተባረከው አዳኝ!

ብቻየኢን አትተወኝ፣

እናም ወደተባረከው መሸሸጊያ በደስታ እደርሳለሁ

በባህር ዳሯም በደስታ አርፋለሁ።

ያን መዝሙር እወደዋለሁ እናም መፅናኛ ስለሚሰጠውም ምስክሬን አቀርባለሁ።

በነፋዝ በሚወዛወዘው ባህር ቢሆንም

ወይም ዲያብሎሶች ወይምሰዎች ወይም ምንም ቢሆን፣

ምንም ውሀ አያሰምጣትም

የባህር እና ምድር እና ሰማያት መምህር የተኛባትን መርከቡን።

እነርሱ ፍላጎትህን በደስታ ያከብራሉ፥

ዝም በል፥ ፀጥ በል1

በእምባዎች እና ፈተናዎች፣ በፍርሀቶችና ሀዘኖች፣ የሚወዱትን በማጣት ልብ መሰበር እና ብቸኛነት፣ ህይወት ዘለአለማዊ እንደሆነ ማረጋገጫ አለ። ጌታችን እና አዳኛችን ይህ እንደሆነ ህያው ምስክር ናቸው።2 በቅዱስ መጻህፍት ውስጥ ያሉት ጽሁፎች በቂ ናቸው፥ “ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ” (Psalm 46:10)። ስለዚህ እውነት እመሰክራለሁ።

ማስታወሻዎች

  1. “Master፣ the Tempest Is Raging፣” Hymns፣ no. 105።

  2. ሪቻርድ ኤል. ኤቭንስ፣ “So Let Us Live to Live Forever፣” New Era፣ July 1971፣ 18።

ከዚህ መልእክት ማስተማር።

ይህ መልእክት የሚያፈቅሯቸውን በሞት ላጧቸው ወይም በፈተናዎች የሚታገሉትን ሊያፅናና ይችላል። ከፕሬዘደንት ሞንሰን መልእክት በተጨማሪ፣ በምታስተምሯቸው ሰዎች ፍላጎት መሰረት፣ የሚቀጥሉትን ቅዱሳት መጻህፍት ለመካፈል አስቡባቸው፥ ኢዮብ 19፥25–261 ቆሮንቶስ 15፥19–22ሞዛያ 24፥13–15ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 122፥7–9። ከተነሳሳችሁም፣ ፈተናችሁ አዳኝ ስለሰጣችሁ ሰላም ለመመስከር ትችላላችሁ።

አትም