2013 (እ.አ.አ)
ተሳታፊ ማስደረግ
ማርች 2013


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ መጋቢት 2013 (እ.አ.አ)

ተሳታፊ ማስደረግ

ይህን መልእክት አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው። ለተጨማሪ መረጃ ወደ www.reliefsociety.lds.org ሂዱ

እምነት, ቤተሰብ, እርዳታ

ነቢያችን፣ ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “እርዳታችንን የሚፈልጉትን ለማዳን እና ወደ ከፍተኛ እና የተሻለ መንገድ ከፍ ለማድረግ ሞክሩ። ይህ የጌታ ስራ እንደሆነ፣ እና በጌታ ስራ ላይ እያለን፣ ለጌታ እርዳታ መብት እንዳለን አስታውሱ” ብለው አበረታትተውናል።1

ከብዙ አመት በፊት ላቪና ኮል እና የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ጓደኛዋ ተሳታፊ ያልሆነች እህትን ይጎበኙ ነበር። በሩን አንኳኩ እና ገዋን የለበሰች ወጣት እናትን አገኙ። የታመመች ትመስል ነበር፣ ነገር ግን ወዲያው ችግሯ መጠጥ እንደሆነ አወቁ። የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎቹ ተቀመጡ እናም ከምትታገለው እናት ጋር ተነጋገሩ።

ከሄዱ በኋላ፣ እንዲህም አሉ፣ “እርሷ የእግዚአብሔር ልጅ ነች። እንሷን የመርዳት ሀላፊነት አለን።” ስለዚህ በየጊዜው ጎበኟት። በየጊዜውም ለመልካም የተቀየረችበትን ይመለከቱና ስሜት ይሰማቸው ነበር። እህትን በሴቶች መረዳጃ ማህበር ተሳታፊ እንድትሆን ጠየቋት። ፈቃደኛ ባትሆንም፣ በመጨረሻም በየጊዜው ተሳታፊ ሆነች። ከተበረታታች በኋላ፣ እርሷ እና ባለቤቷ እና ሴት ልጇ በቤተክርስቲያን ተሳታፊ ሆኑ። ባለቤቱ የመንፈስ ቅዱስ ስሜት ተሰማው። እንዲህም አለ፣ “ኤጲስ ቆጶሱ በሀሳብ እንዳቀረበልኝ አደርጋለሁ።” አሁን በቤተክርስቲያኗ ተሳታፊዎች ናቸው እናም በቤተመቅደስም ተሳስረዋል።2

ከቅዱሳት መጻህፍት

3 ኔፊ 18፥32ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥106138፥56

ከታሪካችን

የጠፉትን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እንዲመለሱ መርዳት ሁልጊዜም የኋለኛ ቀን ቅዱሳንነት እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር አባላትነት ክፍል ነው። ፕሬዘደንት ብሪገም ያንግ [1801–77 (እ.አ.አ)] እንዳሉት፣ “ለእርስ በራስ ርህራሄ ይኑረን፣ … እናም የሚያዩትም አይነ ስውር እሆኑትን በራሳቸው ለማየት እስከሚችሉ ድረስ ይምሩ።”3

የሴቶች መረዳጃ ማህበር ሁለተኛ አጠቃላይ ፕሬዘደንት የነበሩት እላይዛ አር. ስኖው በኦግደን፣ ዩታ፣ ዩ.ኤስ. ኤ. ውስጥ ያሉት እህቶች እርስ በራስ ለመጠነካከር ላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበው ነበር። “[በአገልግሎት ጉዳይ] በ[መዝገብ] መፅሀፍ ላይ ያልተጻፉ በጣም ብዙ በምፅዋት የተሰጠ እንዳለ አውቃለሁ።” ብለዋል። ነገር ግን ልባቸው ቀዝቃዛ ወደሆኑት እህቶች የመርዳት የእህቶች ስራ በሰማይ መዝገብ ላይ እንደሚጻፉ በማወቅ፣ እንዲህም አሉ፥ “ፕሬዘደንት ጆሴፍ ስሚዝ ይህች ማህበር ነፍሳትን ለማዳን የተደራጀች ነች ብለዋል። … ስለእምነታችሁ፣ ስለደግነታችሁ፣ ስለመልካም ስራዎቻችሁ፣ እና ቃላቶቻችሁ ሌላ መፅሐፍ ይጠበቃል። … ምንም የሚጠፋ የለም።”4

ማስታወሻዎች

  1. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “ቅዱሱ የአገልግሎት ጥሪ፣” ግንቦት 2005፣ 55፣ 56።

  2. ወደ ሴቶች መረዳጃ ማህበር ከላቨና ኮል ሴት ልጅ የተላከ ደብዳቤ።

  3. ብሪገም ያንግ፣ ውስጥ (2011)፣ 107።

  4. እላይዛ አር. ስኖው፣ ውስጥ 108።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. ተሳታፊ ያልሆነች እህትን ከእኔ ጋር በሴቶች መረዳጃ ማህበር ተሳታፊ እንድትሆን ለመጠየቅ ብርቱ ነኝን?

  2. የምጠብቃቸው እህቶች ስለወንጌል ጥያቄዎች እኔን ለመጠየቅ የሚመች ስሜት አላቸውን?

አትም