2013 (እ.አ.አ)
ለእናንተ ምልክቶች
ጁን 2013


ወጣቶች

ለእናንተ ምልክቶች

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን።

ፕሬዘደንት ኡክዶርፍ አጠቃላይ ጉባኤን እና ቅዱሳት መጻህፍትን በመንፈዝ እንዳንንከራተት እንደሚረዱን ምልክቶች ገልጸዋቸዋል። ህይወታችሁን ያነሳሷችሁን እና የመሯችሁን ሌሎች መንፈሳዊ ምልክቶችን አሰላስሉባቸው። አጋጣሚዎቻችሁን በማስታወሻዎቻችሁ ጻፉ። እነዚህ ከፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን የተጠቀሱትም ሊረዷችሁ ይችላሉ፥

“የፔትሪያርክ በረከታችሁ ከሁሉም በላይ ጭለማ የሆኑትን ምሽቶች ረድቶ ያሳልፍላችኋል። በህይወት አደጋዎች ውስጥም ይመራችኋል። በረከታችሁ በጥንቃቄ የሚታጠፍ እና የሚሸጎጡ አይደሉም። በፍሬም ውስጥ የሚቀመጥ ወይም የሚታተምም አይደለም። ነገር ግን፣ መነበብ ይገባዋል። መወደድ ይገባዋል። መከተል ይገባዋል።”

“Your Patriarchal Blessing: A Liahona of Light,” Ensign, ህዳር 1986, 66

“የሰማይ አባታችን በደህና እንድንመለስ ለማረጋገጥ ከእርሱ መመሪያ የምንቀበልበት መንገድ ሳይሰጠን በዘለአለም ጎዞአችን አልላከንም። የምናገረውም ስለ ጸሎት ነው። የምናገረውም በጸጥተኛው እና ትንሽ ድምጽ ስለሚያሸኮሽከው ነው።

“The Race of Life,” Liahona, May 2012, 92።