2013 (እ.አ.አ)
በቤተሰብ ታሪክ መደሰት
ጁን 2013


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት መልእክት ሰኔ 2013 (እ.ዓ.ዓ)

በቤተሰብ ታሪክ መደሰት

ይህን መልእክት አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው። ለተጨማሪ መረጃ ወደwww.reliefsociety.lds.org ሂዱ

ምስል
የሴቶች መረዳጃ ማህበር ማህተም

እምነት • ቤተሰብ • እርዳታ

የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን አባል ሽማግሌ ራስል ኤም. ኔልሰን የኤልያስ መንፈስ “መንፈስ ቅዱስ ስለቤተሰብ መለኮታዊ ፍጥረት ምስክር ሲሰጥ የሚታይበት ነው” በማለት አስተምረዋል።1

በዳግም እንደተመለሰቸው የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት እንደመሆናችን መጠን፣ ያለፉ ትውልዶቻችንን የመፈለግ እና የሚያድን የወንጌል ስነ ስርዓቶችን የመስጠት ቃል ኪዳን የገባንበት ሀላፊነት አለብን። እነርሱ ካለእኛ “ፍጹም ለመሆን አይችሉም” (ዕብራውያን 11፥40)፣ እናም “እኛም ያለ ሙታኖቻችን ፍጹም ለመሆን አንችልም” (ት. እና ቃ. 128፥15)።

የቤተሰብ ታሪክ ስራ ለዘለአለም ህይወት በረከቶች ያዘጋጀናል እናም እምነታችንን እና የግል ጻድቅነታችንን እንድናሳድግ ይረዳናል። የቤተሰብ ታሪክ የቤተክርስቲያኗ ተልዕኮ ዋና ክፍል ነው እናም ለሁላችንም የደህንነት እና የዘለአለማዊነት ስራ እንዲቻል ያደርጋል።

የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን ፕሬዘደንት፣ ፕሬዘደንት ቦይድ ኬ ፓከር፣ እንዳሉት፥ “የራሳችንን ትውልዶች ስንፈልግ ከስም በላይ ለማወቅ እንፈልጋለን። … ይህም ፍላጎት ልባችንን ወደ አባቶቻችን ያዞራል—እነርሱን ለማግኘት እና ለማወቅ እናም ለማገልገል እንፈልጋለን።2

ከቅዱሳት መጻህፍት

ሚልክያስ 4፥5–61 ቆሮንቶስ 15፥29ት. እና ቃ. 124፥28–36128፥15

ከታሪካችን

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዳስተማረው፣ “እግዚአብሔር ከሰጠን በዚህ አለም ካለው ሀላፊነቶች ታላቁ ሙታኖቻችንን መፈለግ ነው።3 በቤተመቅደስ ለሞቱት ትውልዶቻችን በውክልና ለማገልገል እና ለእነርሱ አስፈላጊ የሆኑትን ስነ ስርዓቶችን ለማከናወን እንችላለን።

የ14 አመት ልጇ የሞተባት በናቩ፣ ኢለኖይ የኖረች ሳሊ ራንዶል በዘለአለም ቤተሰቦች ቃል ኪዳን ታላቅ መፅናኛን አግኝታ ነበር። ባለቤቷ በውክልና ለልጇ ከተጠመቀ በኋላ፣ ለዘመዶቿ እንዲህ ጻፈች፥ “እኛ ለሞቱት [ትውልዶቻችን] መጠመቅ እና ለማወቅ እስከምንችልበት ድረስ እነርሱን ለማዳን ለማዳን መቻላችን…እንዴት ግሩም ነገር ነው።” ከዚያም ዘመዶቿ ስለትውልዶቻቸው መረጃዎች እንዲልኩላት እንዲህ በማለት ጠየቀቻቸው፣ “[ቤተሰባችንን] ለማዳን የምችለውን ለማድረግ አላማ አለኝ።”4

ማስታወሻዎች

  1. ራስል ኤም. ኔልሰን, “A New Harvest Time,” Liahona, July 1998, 34።

  2. ቦይድ ኬ. ፓከር፣ “Your Family History: Getting Started,” Liahona, Nov. 2011, 17።

  3. Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith [2007 (እ.አ.አ)]፣ 475

  4. Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society (2011)፣ 20–21 ተመልከቱ።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. የምጠብቃቸው እህቶች የቤተሰብ ታሪክን እንዲፈልጉ ለመርዳት ምን ማድረግ እችላለሁ?

  2. የግል ታሪኬን እየቀረጽኩኝ ነውን?

አትም