2013 (እ.አ.አ)
በክብ መዞር
ጁን 2013


የቀዳሚ አመራር መልእክት ሰኔ 2013 (እ.ዓ.ዓ)

በክብ መዞር

ምስል
በፕሬዘደንት ዲየትር ኤፍ ኡክዶርፍ

የሚሄድበት የጠፋባቸው ሰዎች በክብ ይዞራሉ የሚለውን የጥንት አባባልሰምታችኋልን?

የጀርመን የስነ አእምሮ ዶክተር የነበረው ጃን ኤል. ሱማን ይህ እውነት እንደሆነ ለማወቅ በጥናት ለመወሰን ፈለገ። በዚህ ጥናቱ ተሳታፊ የሆኑትን ወደ ትልቅ ደናማ አካባቢ እና ወደ ሰሀራ በረሀ ወሰዳቸው እናም በአለም የት እንደሚገኙ በሚታይበት መሳሪያ የት እንደሄዱ ተመለከተ። አቅጣጫ መለያ መሳሪያ ወይም ሌላ ምንም መሳሪያዎች አልነበሯቸውም። የተሰጣቸውም መመሪያ ቀላል ነበር፥ በተመለከተላቸው አቅጣጫ በቀጥታ ሂዱ።

ዶክተር ሱማን ምን እንደተከሰተ እንዲህ በማለት ገለጸ። “[አንዳንዶቹ] ዳመና በተሸፈነበት ቀን፣ ጸሀይ በዳመና በተሸፈነችበት [የት እንደሚገኙ ለመጥቀስ የሚችሉበት ምንም ሳይኖራቸው] ተጓዙ። …[እነርሱም] በክብ ዞሩ፣ [አብዛኛዎቹም] እነርሱ የተጓዙበትን መንገን ሳይገነዘቡ ደጋግመው አለፉበት። ሌሎች ተሳታፊዎችም ጸሀይ እየበራ፣ የሚጠቅሱባቸው ነገሮች በሩቅ እየታዩአቸው፣ ይሄዱ ነበር “እነዚህም…በፍጹም ቀጥተኛ የሆነ መንገድ ይከተሉ ነበር።”1

ይህ ጥናት ሌሎች የተለያዩ ዘዴዎች በመጠቀም ተደጋግመው ነበር።2 ሁሉም አንድ አይነት የሆነ ውጤት አግኝተው ነበር።

ሰዎች ለመመልከት የሚችሉት የምድር ምልክት ሳይኖራቸው ሲቀር በክብ ይዞራሉ።

የቅዱሳት መጻህፍት ምልክቶች

ያለ መንፈሳዊ ምልክቶች፣ ሰውም ይቅበዘበዛል። ያለ እግዚአብሔር ቃል፣ እኛም በክብ እንዞራለን።

እንደ ግለሰብ እና እንደ ህብረተሰብ፣ ከጊዜ መጀመሪያ ጀምሮ በእያንዳንዱ ዘመናት ይህ አካሄድ ሲደጋገም እንመለከታለን። የእግዚአብሔርን ቃላት ስናጣ፣ እንጠፋለን።

ለዚህም ነው ሌሂ ልጆቹን የነሀስ ሰሌዳውን እንዲያመጡ ወደ እየሩሳሌም እንዲልካቸው ጌታ ያዘዘው። የሌሂ ትውልዶች በትክክል መንገድ ላይ እንዳሉ ለመወሰን የሚችሉበት መመሪያ የሚሰጧቸው የሚመኩበት ምልክቶች እንደሚያስፈልጋቸው እግዚአብሔር አውቆ ነበር።

ቅዱሳት መጻህፍት የእግዚአብሔር ቃል ናቸው። እነዚህም ወደ አዳኛችን እንድንቀርብ እና ብቁ የሆኑትን አላማዎች እንድንደርስባቸው ለመጓዝ የሚያስፈልጉንን መንገዶች የሚያሳዩ የእግዚአብሔር ምልክቶች ናቸው።

የአጠቃላይ ጉባኤ ምልክቶች

በአጠቃላይ ጉባኤ የሚሰጡ መመሪያዎች በትክክለኛ መንገድ ላይ እንዳለን ለማወቅ የሚረዱን ሌላ ምልክቶች ናቸው።

አንዳንዴ እራሴን “በቅርብ አጠቃላይ ጉባኤ የተናገሩትን ወንዶችና ሴቶች ቃላቶች አዳምጫለሁኝን? ቃላቶቻቸውን ደጋግሜ አንብቤአለሁኝን? አሰላስሌአቸዋለሁኝን እናም በህይወቴ ተጠቅሜባቸዋለሁኝን? ወይም ጥሩውን ንግግር ተደስቼበት እናም በመንፈስ የተመሩ መልእክቶች በህይወቴ ለመጠቀም ችላ ብያለሁኝን? በማለት እጠይቃለሁ።”

ምናልባት ስታዳምጡ ወይም ስታነቡ፣ አንድ ወይም ሁለት ነጥቦችን ጽፋችኋል። ምናልባት አንድ ነገርን በተሻለ መንገድ ወይም በተለየ ሁኔታ ለማድረግ ወስናችኋል። ስላለፈው አጠቃላይ ጉባኤ መልእክቶች አስቡበት። ብዙዎቹ ቤተሰቦቻችንን እንድናጠናክር እና ጋብቻችንን እንድናሻሽል አበረታትተውናል። ይህ የ Liahona መፅሔትም ህይወታችንን ከሚባርኩ ሀሳቦች ጋር በእነዚህ ዘለአለማዊ መሰረታዊ መርሆ ላይ ያተኩራል።

እነዚህ ጠቃሚ ምክሮችን እስተውለናል ወይ? እናም እንጠቀምባቸዋለን? እነዚህን እውነተኛ እና ዋጋ ያላቸውን ምልክቶች እያወቅን ወደ እነርሱ እየተጓዝን ነው ያለነውን?

የመንከራተቴ መድሀኒት

መንፈሳዊ ምልክቶች በቀጥተኛው እና በጠባብ መንገዱ ላይ እኛን ለመጠበቅ በጣም አስፈላጊ ናቸው። መጓዝ ስለሚገባን መንገድ ግልጽ መመሪያው ይሰጣሉ፣ ነገር ግን ይህን የሚሰጡት ካወቅናቸው እና ወደ እነርሱ ከሄድን ብቻ ነው።።

በእነዚህ ምልክቶች ለመሄድ እምቢ ካልን፣ ትርጉም የሌላቸው፣ ጌጥ ከመሆን በላይ ምንም ጥቅም የሌላቸው እና ወደ ፊት የሚታየውን ለውጥ እንዲኖረው የሚያሳዩ ብቻ ይሆናሉ።

በአስተያየታችን ብቻ መሄድ የሚበቃ አይደለም።

መልካም ፍላጎት መኖሩ ብቻ የሚበቃ አይደለም።

በተፈጥሮ ባለን አስተያየት ላይ ብቻ መመካትም በቂ አይደለም።

ቀጥተኛ የሆነ መንፈሳዊ መንገድ እንደምንከተል በምናስብበትም ጊዜ፣ መመሪያ የሚሰጡን ምልክቶች ሳይኖረን፣ ያለመንፈስ መመሪያ፣ እንንከራተታለን።

ስለዚህ፣ አይኖቻችንን እንክፈት እናም በጎ አድራጊ አምላካችን ለልጆቹ የሰጠውን ምልክቶች እንመልከት። እናንብብ፣ እናም የእግዚአብሔርን ቃላት እንጠቀምባቸው። በእውነተኛ ፍላጎት እንጸልይ እናም የመንፈስን ምሪት እናዳምጥ እና እንከተል። በሚያፈቅረን የሰማይ አባታችን የተሰጡትን ከሰማይ የመጡትን ምልክቶች ስናውቅ፣ መንገዳችንን በእነርሱ እናስተካክላለን። ወደ መንፈሳዊ ምልክቶችም አቅጣጫችንን በየጊዜው በማስተካከል መንገዳችንን ማቅናት ይገባናል።

በዚህም መንገድ፣ በክብ አንንከራተትም እናም በልበ ሙሉነት እና በእርግጠኛነት በክርስቶስ ደቀ መዛሙርትነት በጠበበና በቀጠነ መንገድ ለሚጓዙት ውርስ ወደሆነው ወደዚያ ታላቅ ሰማያዊ በረከት እንሂድ።

ማስታወሻዎች

  1. Jan L. Souman and others, “Walking in Circles,” Current Biology (Sept. 29, 2009), 1538, cell.com/current-biology/issue?pii=S0960-9822(09)X0019-9 ተመልከቱ።

  2. ለምሳሌ፣ “A Mystery:: Why Can’t We Walk Straight?” ተመልከቱ። npr.org/blogs/krulwich/2011/06/01/131050832/a-mystery-why-can-t-we-walk-straight።

ከዚህ መልእክት ማስተማር።

ከዚህ መልእክት ለማስተማር ስትዘጋጁ፣ በመንፈሳዊ ምልክቶች ስለተመሩ ሰዎች ወይም በክብ ስለተንከራተቱ ሰዎች በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ምሳሌዎችን ለመፈለግ ትችላላችሁ። ጥናታችሁን በእነዚህ ቅዱሳት መጻህፍት ለመጀመር ትችላላችሁ፥ ዘኁልቁ 14፥26–331 ኔፊ 16፥28–29አልማ 37፥38–47። ምሪትን ከተቀበላችሁም፣ ከእነዚህ ምሳሌዎች አስተያየታችሁን ከምታስተምሯቸው ጋር ለመካፈል ትችላላችሁ። ከእነዚህ ታሪኮች ምን ለመማር እንደሚችሉ ጠይቋቸው።

አትም