2013 (እ.አ.አ)
በእምነት የተገፋፋ
ጁላይ 2013


ወጣቶች

በእምነት የተገፋፋ

ጸሀፊዋ በኖርዝ ኬሮላይና፣ ዮ.ኤስ.ኤ. ውስጥ ትኖራለች።

ከብዙ አመቶች በፊት መስራቾች ይኖሩበት በነበረው በዊንተር ኳርተርስ፣ ነብራስካ፣ ዮ.ኤስ.ኤ. የነበረኝን ጉብኝት በምንም አልረሳም። ቦታው ልክ ቤተመቅደስን እንደምጎበኝ አይነት ቅድስና ይሰማኝ ነበር።

አይኖቼ በእምባ ተሞልተው ማየትም አስቸግሮኝ ነበር። ሀውልትን አየሁ ነገር ግን ምን እንደሆነ ለማወቅ አልቻልኩም ነበር። እምባዬን ስጠርገው፣ ፊታቸው በሀዘን የተሞላ ወንድ እና ሴትን አየሁ። በቅርብ ስመለከትም፣ ህጻን ልጅ በእግራቸው አጠገብ በመቃብር ውስጥ ተኝቶ ተመለከትኩኝ።

እይታው በበዛ ስሜት፣ እንዲሁም በሀዘን፣ በንዴት፣ በምስጋና፣ እና በደስታ እንድሞላ አደረገኝ። እነዚያ ቅዱሳን የተሰማቸውን ሀዘን ለመቀነስ ፍላጎት ተሰማኝ፣ ነገር ግን በዚያ ጊዜም ለወንጌሉ መስዋዕት ባደረጉት ምስጋናም ተሰማኝ።

በዊንተር ኮርተርስ የነበረኝ አጋጣሚ የሰማይ አባት ወንጌሉን ለልጆቹ እንደሚሰጥ እናም እንደፍላጎታቸው እንዲያደርጉበት ነጻ ምርጫ እንደሚሰጣቸው ለማወቅ ረዳኝ። የዚያ ህጻን ልጅ ወላጆች ቀላሉን መንገድ ለመምረጥ ይችሉ ነበር። ነቢይን ለመከተል እና በወንጌል ለመኖር እነዚህ መስራቾች ወደ ፊት እንዲገፉ ልጃቸውን እስከ መቅበር ቢሆንም ዋጋ ይጠይቅ ነበር።። ነገር ግን ወንጌልን በህይወታቸው ለመቀበል እና ፈተናዎቻቸውን ለመቀበል መረጡ። የቅዱሳን ለወንጌል የነበራቸው ቆራጥነት እና ወደፊት ለመግፋት የነበራቸው ውሳኔ በእምነት እና በተስፋ፣ እንዲሁም ወደፊት ለሚኖር መልካምነት ተስፋ እና ጌታ እንደሚያውቃቸውና ሀዘናቸው እንደሚቀንስላቸው ባላቸው እምነት የተገፋፋ እንደሆነ ተመርኩኝ።