2013 (እ.አ.አ)
ወንጌልን ማስተማር እና መማር
ጁላይ 2013


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ሐምሌ 2013 (እ.አ.አ)

ወንጌልን ማስተማር እና መማር

ይህን መልእክት አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው። ለተጨማሪ መረጃ ወደ www.reliefsociety.lds.org ሂዱ

እምነት, ቤተሰብ, እርዳታ

ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅ መምህር ነበር። “ሴቶስን በህዝብ መካከል እና በግለሰብ፣ በመንገድ ላይ እና በባህር ዳር፣ በውሀ ጉድጓድ እና በቤቶቻቸው በማስተማር” ለእኛ ምሳሌ ሰጥቷል። “ለእነርሱም ከፍቅር የመነጨደግነት አሳይቷል እናም እነርሱን እና የቤተሰብ አባላታቸውን ፈውሷል።”1

ማርታን እና ማርያምን አስተማረ እናም “የእርሱ ደቀመዛሙርቶች እንዲሆኑ እና ከእነርሱ በምንም የማይወሰደውን ‘የሚያስፈልገውን’ (ሉቃስ 10:42) ደህንነት ተካፋይ እንዲሆኑ ጋበዛቸው።”2

በኋለኛው ቀን ቅዱሳት መጻህፍቶቻችን ውስጥ፣ ጌታ “የመንግስቱን ትምህርት እርስ በርስ ተማማሩ” (D&C 88:77) በማለት ትእዛዝ ሰጥቶናል። ወንጌልን ስለማስተማር እና መማር የመጀመሪያ ክፍል አመራር ሁለተኛ አማካሪ የነበሩት ሸርል ኤ. ኢፕሰን እንዳሉት፣ “የወንጌልን ትምህርት በሙሉ ለመረዳት መማር የህይወት ጊዜ ስራ ነው እናም ‘በትዕዛዝ ላይ ትዕዛዝ፣ ሀበስርዐት ላይ ስርዐት፣ ጥቂት በዚህ፣ ጥቂት በዚያ’ (2 Nephi 28:30) ይመጣል።”3

ስንማር፣ ስናጠና፣ እና ስንጸልይ፣ መልእክታችንን “ወደ ወንድ [እና ሴት] ልጆች ልብ” (2 Nephi 33:1) በሚወስደው በመንፈስ ቅዱስ ሀይል እናስተምራለን።

ከቅዱሳት መጻህፍት

አልማ 17፥2–331፥5ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥12–1384፥85

ከታሪካችን

ሴቶች እንደመሆናችን መጠን በቤት እና በቤተክርስቲያን ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆነ የአስተማሪነት ሀላፊነት እንዳለን ያለፉት ነቢያቶቻችን አስታውሰውናል። በመስከረም 1979 (እ.አ.አ)፣ ፕሬዘደንት ስፔንሰር ደብሊው. ኪምባል [1895–1985 (እ.አ.አ)] “የቅዱሳት መጻህፍት አዋቂ እህቶች” እንድንሆን ጠይቀውን ነበር። እንዲህም አሉ፥ “የቅዱስ መጻህፍት ተማሪዎች ሁኑ—ሌሎችን ለመገሰፅ ሳይሆን፣ ኔሎችን ለማነሳሳት! ከሁሉም በኋላ፣ (እርዳታ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ለማስታወስ) የወንጌሉን እውነቶች እንደ ሀብት ለመጠበቅ ታላቅ ፍላጎ ያላቸው ያለባቸው፣ ብዙ ከሚንከባከቡት እና ከሚያስተምሩት፣ ሴቶች እና እናቶች በላይ ማን አለ?”4

ሁላችንም አስተማሪዎች እና ተማሪዎች ነን። ከቅዱሳት መጻህፍት እና ከህያው ነቢያት ቃላት ስናስተምር፣ ሌሎች ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ እንረዳለን። ትርጉም ያላቸው ጥያቄዎች በመጠየቅ እና ከእዚያም በማዳመጥ በመማር ሁኔታ ስንሳተፍ፣ የግል ፍላጎታችንን የሚያሟሉ መልሶችን ለማግኘት እንችላለን።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. የተሻለች አስተማሪ ለመሆን ራሴን እንዴት አዘጋጃለሁ?

  2. ምስክሬን በእኔ ስር ላሉ እህቶች ጋር እካፈላለሁን?

ማስታወሻዎች

  1. Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society, (2011)፣ 3።

  2. Daughters in My Kingdom፣ 4።

  3. ሸርል ኤ. ኢፕሰን፣ “Teaching Our Children to Understand,” Liahona and Ensign, ግንቦት 2012፣ 12።

  4. ስፔንሰር ደብሊው. ኪምባል፣ በ Daughters in My Kingdom, ውስጥ 50።