2013 (እ.አ.አ)
አለም ዛሬም መስራቾች ያስፈልጋታል
ጁላይ 2013


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ሐምሌ 2013 (እ.አ.አ)

አለም ዛሬም መስራቾች ያስፈልጋታል

ምስል
ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን።

ለብዙዎች የ1847 (እ.አ.አ.) የመስራቾች ጉዞ በናቩ፣ በከርትላንድ፣ በፋር ዌስት፣ ወይም በኒው ዮርክ አልተጀመረም፣ ነገር ግን የተጀመረው ሪቅ በነበሩት በኢንግላንድ፣ በስኮትላንድ፣ በስካንድኔቪያ፣ ወይም በጀርመን ነበር። ትንንሽ ልጆች ወላጆቻቸው ቤተሰባቸውን፣ ጓደኞቻቸውን፣ ምቾትንና፣ ደህንነትን ትተው የሄዱበት የእምነት ሁኔታ በሙሉ አልገባቸውም ነበር።

አንድ ትንሽ ልጅ “እማ፣ ለምንድን ነው ቤታችንን ትተን የምንሄደው? የት ነው የምንሄደው? በማለት ጠየቀ።

“ተከተለኝ፣ ውዱ ልጄ፤ የአምላካችን ከተማ ወደሆነችው ወደ ፅዮን ነው የምንሄደው።

በቤት ደህንነት እና በፅዮን ቃል ኪዳን መካከል አስፈሪውና የማይታመንበት የፓስፊክ ባህር ውሀ ነበር። በእነዚያ አደገኛ ጉዞዎች ጊዜ የሰው ልብን የያዘውን ፍርሀት ለመግለጽ የሚችል ማን አለ? በጸጥተኛው የመንፈስ ሹክሹክታ በመነሳሳት፣ ተራ ቢሆንም በማይቀየረው እምነት በመደገፍ፣ እነዚያ ፈር ቀዳጅ ቅዱሳን በእግዚአብሔር አመኑ እናም ጉዞአቸውንም ቀጠሉ።

በመጨረሻም ወደ ናቩ ሲደርሱም እንደገና በመንገድ ችግርን ለመቋቋም ሄዱ። ከናቩ ወደ ሶልት ሌክ ስቲ በሚወስደው መንገድ ላይ የዛፍ እና የድንጋይ ሀውልቶች መቃብሮች ያመለክታሉ። ይህም መስራቾች የከፈሉት ዋጋ ነበር። ሰውነታቸው በሰላም ተቀብረዋል፣ ነገር ግን ስማቸው ለዘለአለም ይኖራል።

የደከሙ በሬዎች ተጓዙ፣ የጋሪዎች ጎማም ሲጢጥ አሉ፣ ጀግና ሰዎችም በብርቱ ለፉ፣ የጦር ከበሮም ተሰማ፣ እናም ተኩላዎችም ጮሁ። ነገር ግን በመንፈስ የተነሳሱት እና በአውሎ ነፋስ የተገፉት መስራቾች ወደፊት ገፉ። በአብዛኛውም ጊዜ ይህን ዘፈኑ፥

ኑ ኑ ቅዱሳን፣ መከራን አትፍሩ፤

በደስታ ተጓዙ።

ጉዞአችሁም ከባድም ቢሆን፣

ጸጋ ይሁን በጊዜያችሁ። …

ሁሉም መልካም! ሁሉም መልካም!1

እነዚህ መስራቾች የጌታን ቃላት ያስታውሱ ነበር፥ “ለእነርሱ ያለኝን ክብር፣ እንዲሁም የፅዮንን ክብር፣ ለመቀበል ይዘጋጁ ዘንድ፣ ህዝቤ በሁሉም ነገሮች መፈተን አለባቸው።”2

የጊዜ ማለፍ ትዝታችንን ያደበዝዛል እናም ስም በሌለበት መቃብር ላይ በእምባ ምልክት በመተው የጉዳት መንገድን ለተጓዙት ያለንን ምስጋናም ይቀንሳል። ነገር ግን ዛሬ ስላለው ፈተናስ? የሚያስቸግሩ የጉዞ መንገዶች የሉምን፣ የሚወጣበት አባጣ ጎርባጥ ተራራዎች የሉምን፣ የሚቋረጥ ሸለቆ የለምን፣ የሚቋረጥ ወንዝስ የለምን? ወይም ሊውጠን ከሚያስፈራራው አደጋ በመምራት ሊያስወጣንና ወደ ፅዮን ደህንነት ለሚመራን የመስራችን መንፈስ አሁን የምንፈልግበት ምክንያት አለን?

የአለም ሁለተኛው ጦርነት ከተፈጸሙ አመታት በኋላ፣ የግብረገብነት ስነስርዓት በተደጋጋሚ ተቀንሷል። ወንጀል በጣም በዝቷል፤ መልካም ጸባይም ቀንሷል። ብዙዎች የዘለአለም ደስታን ችላ ብለው የጊዜያዊ ደስታ ብቻ በመፈለግ በጥፋት መንገድ ላይ ናቸው ያሉት። በዚህም ሰላምንን እናጣለን።

ግሪኮች እና ሮሜዎች አረመኔአዊ በሆነ አለም ውስጥ እንዴት ድል እንደነበራቸው እና ችላ ማለት እና ለስላሳነት በመጨረሻም ወደ ውድመት እስኪደርሱ ድረስ በማሸነፍ ድላቸው እንደተፈጸመ እንረሳለን። በመጨረሻም፣ ከነጻነት በላይ ደህንነትን እና የተመቸ ህይወትን ፈለጉ፤ እናም ሁሉንም—ምቾትን እና ደህንነትን እና ነጻነትን አጡ።

በሰይጣን አትታለሉ፤ ነገር ግን በጽኑነት ለእውነት ቁሙ። ልዩ ስሜት ባለው እና መጥፎ ልምድ በሆነው ጥልቅ ስሜት መካከል ደስታን ያእማቋረጥበመፈለግ የነፍስ ያልረካ ፍላጎት ማሟላት አይቻልም። መጥፎ ልምድ ወደ ምግባረ ገብነት አይመራም። ጥላቻ ፍቅርን አያበራታታም። ፈሪነት ጀግንነትን አይሰጥም። ጥርጣሬ እምነትን አያነሳሳም።

አንዳንዶች ንጹህነትን፣ ታማኝነትን፣ እና ለእግዚአብሔር ትእዛዛት መታዘዝን በሚያሳልቁ ሞኞች አስጠሊ ንግግሮች እና መሳለቂያዎችን ለመቋቋም አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል። ነገር ግን አለም በመሰረታዊ መርህ ላይ መመካትን ሁልጊዜም ታሳልቃለች። ኖህ መርከብን እንዲገነባ መመሪያ ሲሰጠው፣ ሞኝ የነበሩት ህዝቦች ዳመና የሌለውን ሰማይ ተመልክተው ዝናቡ እስከሚመጣ ድረስ ያሾፉና ያፌዙ ነበር።

ታላቅ ክፍያ የሚያስፈልጋቸውን ትምህርቶች በተደጋጋሚ መማር አለብን? ጊዜ ይቀየራል፣ እውነት ግን በአቋም ይጸናል። በፊት ከነበሩት አጋጣሚዎች ጥቅም ባለማግኘት ስንወድቅ፣ ሁሉንም ከልብ ህመሞች፣ ከስቃዮች፣ እና ከሀዘኖች ጋር እነዚህን በድጋሜ ያጋጥመናል። ወብቱን ለጠላው እባቡ ሳይሆን የደህንነት አላማ ለነደፈውን፣ የመጀመሪያውን እስከመጨረሻው ለሚያውቀው ጌታችን ታዛዥ የመሆን ጥበብ የለንምን?

የትርጉም መዝገበ ቃላት መስራችን “ከሌሎች በፊት በመሄድ ወይም መንገድን ለሌሎች ለማዘጋጀት የሚሄድ” ነው በማለት ትርጉም ይሰጣል።3 ቀዳሚ ትውልድ ባህሪ የሆነውን ብርቱነት እና ከአላማ አለመነቃነቅ እኛ እንደምንም ለማግኘት እንችላለን ወይ? እናንተ እና እኔ በእውነትም መስራቾች ለመሆን እንችላለን?

እኔ ለመሆን እንደምንችል አውቃለሁ። አለም እንዴት መስራቾችን በጣም ትፈልጋለች!

ከዚህ መልእክት ማስተማር።

ቅዱሳት መጻህፍት የቤት ለቤት አስተማሪዎች “ማስጠንቀቅ፣ ማብራራት፣ ማበረታታት፣ እናም ማስተማር፣ እናም ሁሉንም ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ መጋበዝ አለባቸው” በማለት ይገልጻል” (ት. እና ቃ. 20፥59 በፕሬዘደንት ሞንሰን መልእክት ውስጥ ያሉትን ማስጠንቀቂያዎች እና የሚጋብዙበትን ለምታስተምሯቸው ለመጠቆም አስቡበት። ከእነርሱም ጋር ጻድቅ ምሳሌዎችን የሚለዩበትንና የሚከተሉበትን፣ መታለልን የሚያስወግዱበይን፣ እና ከሌሎች ስህተቶች የሚማሩበትን መንገዶች ተወያዩበት። የምታስተምሯቸውን እንዴት ዛሬ መስራቾች ለመሆን እንደሚችሉ ጠይቋቸው።

አትም