ወጣቶች
የእቃ ዝርዝርን መዝግቡ
ፕሬዘደንት አይሪንግ ፕሬዘደንት ደብሊው. ኪምባል (1895–1985) “ማስታወሻዎች በረከቶቻችንን የምንቆጥርበት እና የእነዚህ በረከቶችን ዝርዝር ለወደፊት ትውልዶቻችን የምንተውበት ነው” እንዳሉ ጠቅሰዋል። በጥቅምት 2012 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ፣ ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ፣ ሞንሰን ስለማስታወሻ መፅሐፍ መጻፍ ያላቸውን ምስክርነት ሰጡ። የህይወት አዳጣሚያቸውን ከዚህ ተጨማሪ ጋር ተካፈሉ፣ “በየቀኑ የምጽፋቸው ማስታወሻዎች በሌላ መንገድ ለማስታወስ የማልችላቸውን ነገሮች እንዳስታውስ ረድቶኛል።” እንዲህም መከሩ፣ “እናንተም ስለህይወታችሁ በጥንቃቄ እንድታስቡባቸው እና ትልቅም ይሁኑ ትንሽ ለተቀበላችኋቸው በረከቶች እንድትመለከቱ አበረታታችኋለሁ” (“በረከቶችን አስቡባቸው፣” Liahona እና Ensign፣ ህዳር 2012፣ 86)። እነዚህ ነቢያት የሰጡትን ምክር ለመከተል እና በማስታወሻችሁ ለመጻፍ አላማ አድርጉ።