2013 (እ.አ.አ)
እወቁ፣ አስታውሱ፣ እናም ምስጋና ስጡ
ኦገስት 2013


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ነሐሴ 2013 (እ.አ.አ)

እወቁ፣ አስታውሱ፣ እናም ምስጋና ስጡ

ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ አይሪንግ

እግዚአብሔር ከእርሱ ለምንቀበላቸው ለማንኛቸውም በረከቶች ምስጋና እንድንሰጠው ይጠይቀናል። በምስጋና ጸሎቶቻችን፣ በአብዛኛው ጊዜ ምስጋናችንን ለእግዚአብሔር እንደ ልብ ስጦታ ለመስጠት ምንም ሀሳብ ሳይኖረን አንድ የሆኑ ቃላትን በመደጋገም ጸሎታችንን በማቅረብ እንደ መሺን ለመሆን ቀላል ይሆንልናል። እግዚአብሔር ለሰጠን እውነተኛ ምስጋና እንዲሰማን “በመንፈስ ምስጋና መስጠት” (ት. እና ቃ. 46:32) ይገባናል።

ክፍሉንም ቢሆን እግዚአብሔር የሰጠንን እንዴት ለማስታወስ እንችላለን? ሐዋሪያው ዮሀንስ አዳኝ በመንፈስ ቅዱስ እኩል ስለሚመጠው የማስታውስ ስጦታ ያስተማረንን እንደጻፈው፥ “አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።” (ዮሀንስ 14:26)

መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ያስተማረንን እንድናስታውስ ያደርጋል። እግዚአብሔር የሚያስተምረን አንዱ መንገድ በበረከቶቹ ነው፤ እና ስለዚህ እምነታችንን ለማንቀሳቀስ ከመረጥን፣ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ደግነት እንድናስታውስ ያደርገናል።

ይህንንም ዛሬ በጸሎት ልትሞክሩት ትችላላችሁ። “ጌታ አምላክህን በሁሉም ነገሮች አመስግን” (ት. እና ቃ. 59:7) የሚለውን ትእዛዝ ለመከተል ትችላለህ።

ፕሬዘደንት ኤዝራ ታፍት ቤንሰን [1899–1994(እ.አ.አ)] ጸሎት ይህን ለማድረግ ጊዜ እንደሚፈጥር ሀሳብ አቅርበዋል። እንዲህም አሉ፥ “ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አንድ ጊዜ እንዳለው የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ኃጢያት ከሰሩበት ታላቁ ቢኖር ምስጋና ያለመስጠት ኃጢያት ነው። አብዛኛዎቻችን ይህን እንደ ታላቅ ኃጢያት እንደማንመለከተው አስባለሁ። በጸሎታችን እና ጌታን በምንለምንበት ጊዜ ለተጨማሪ በረከቶች የመጠየቅ ዝንባሌ አለን። ነገር ግን አብዛኛዎቹን ጸሎቶቻችንን ምስጋናን ለተቀበልናቸው በረከቶች በማቅረብ ማሳለፍ እንደሚያስፈልገን ይሰማኛል። በብዛት እንደሰትባቸዋለንና።”1

እናንተም እንደዚህ አይነት አጋጣሚ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሊኖራችሁ ትችላላችሁ። የግል ጸሎታችሁን በምስጋና ለመጀመር ትችላላችሁ። በረከቶቻችሁን በመቁረጥ መጀመር ትችላላችሁ እና ከዚያም ለትንሽ ጊዜ ጸጥ በሉ። ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ጋር እምነት ካላችሁ፣ የሌሎች በረከቶች ትዝታዎች አዕምሮአችሁን ይሞላላችኋል። ለእያንዳንዱም ምስጋናችሁን ለማቅረብ ከጀመራችሁ፣ ጸሎታችሁ በሌላ ጊዜ ከነበረው ትንሽ የረጀመ ይሆናል። ታስታውሳላችሁ፣ እናም ምስጋናም ይኖራችኋል።

በማስታወሻችሁ ላይም ስትፅፉ እንዲህም አይነት ነገር ለማድረግ ትችላላችሁ። መንፈስ ቅዱስ ከጊዜ መጀመሪያ ጀምሮ ሰዎችን በእዚያ ይረዳቸው ነበር። መፅሐፈ ሙሴ እንዲን እንደሚል ታስታውሳላችሁ፣ “እናም በአዳም ቋንቋ የተጻፈበት የመታሰቢያ መፅሐፍን ጻፉ፣ ወደ እግዚአብሔር የሚጠሩት ሁሉም በመንፈስ እንዲፅፉ ለመነሳሳት ተሰጥቷቸዋልና።” (ሙሴ 6:5)

ፕሬዘደንት ስፔንሰር ደብሊው ኪምባል [1895–1985 (እ.አ.አ)] የተነሳሳ ጽህፈትን እንዲህ ገልጸው ነበር፥ “የማስታወሻ መፅሐፍን የሚጠብቅ የጌታን ትዝታ በልባቸው በየቀኑ የሚጠብቁ ናቸው። ማስታወሻዎች በረከቶቻችንን የምንቆጥርበት እና የእነዚህ በረከቶችን ዝርዝር ለወደፊት ትውልዶቻችን የምንተውበት ነው።”2

መጻፍ ስትጀምሩ፣ እራሳችሁን “ዛሬ እግዚአብሔር እኔን እና የምወዳቸውን እንዴት ባረከ?” በማለት እንጠቅይ። ይህን በየጊዜው እና በእምነት ካደረጋችሁ፣ በረከቶችን እያስታወሳችሁ ትሄዳላችሁ። አንዳንዴም በቀን ለማየት ባይታያችሁም የእግዚአብሔር እጅ በህይወታችሁ ላይ እየነካችሁ እንደሆነ የምታውቁትን ስጦታዎች ወደ አዕምሮዎቻችሁ ይመጣላችኋል።

የሰማይ አባታችን እና አዳኛችን ወደ እነርሱ የሚያደርሰውን መንገድ ለመክፈት ላደረጉት እና ለሚያደርጉት ለማወቅ፣ ለማስታወስ፣ እና ምስጋና ለመስጠት ጥረታችንን እንድንቀጥል ጸሎቴ ነው።

ማስታወሻዎች

  1. ኤዝራ ታፍት ቤንሰን፣ God, Family, Country: Our Three Great Loyalties (1974)፣ 199።

  2. ስፔንሰር ደብሊው. ኪምባል፣ “Listen to the Prophets,” Ensign፣ ግንቦት 1978፣ 77።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

በመልእክታቸው ውስጥ፣ ፕሬዘደንት አይሪንግ የሰማይ አባትን ደግነት በጸሎታችን እንድናስታውስ ጋብዘውናል። ከምታስተምሯቸው ጋር በምስጋና መጸለይ በህይወታችን የእግዚአብሔርን እጅ ለማወቅ ሊያስተምረን እንደሚችል ተወያዩበት። ከምታስተምሯቸው ጋር በመንበርከክ ለመጸለይ አስቡበት እናም ጸሎት ለሚያቀርበው/ለምታቀርበውም ምስጋና እንዲገልጽ/እንድትገልጽ ሀሳብ አቅርቡላቸው።

የምስጋናን አስፈላጊነትንም ፕሬዘደንት አይሪንግ ከጠቀሷቸው የቅዱስ መጻህፍት ጥቅሰቶች በተጨማሪ እነዚህን ጥቅሰቶች ለማጥናት ትችላላችሁ።: መዝሙር 100ሞዛያ 2፥19–22አልማ 26፥834፥38ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥2178፥19136፥28.