2013 (እ.አ.አ)
በጎ ድርገት
ኦገስት 2013


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት መልእክት፣ ነሐሴ 2013 (እ.አ.አ)

በጎ ድርገት

ይህን መልእክት አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው። ለተጨማሪ መረጃ ወደwww.reliefsociety.lds.org ሂዱ

እምነት • ቤተሰብ • እርዳታ

የቤተክርስቲያኗ የበጎ ድርገት ፕሮግራም አላማ አባላት እራሳቸውን እንዲችሉ ለመርዳት፣ ደሆችን እና እርዳታ የሚያሰልጋቸውን ለመንከባከብ፣ እና አገልግሎት ለመስጠት ነው። በጎ ድርገት ዋና የሴቶች መረዳጃ ማህበር ስራ ነው። የቀዳሚ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ እንዳስተማሩት፥

“[ጌታ] ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ ለደቀ መዛሙርቱ የሚረዱበት መንገዶች ሰጥቷል። ልጆቹን ሌሎችን ከእርሱ ጋር ለመርዳት ጊዜአቸውን፣ ያላቸውን፣ እና እራሳቸውን በመስዋዕት እንዲሰጡ ይጋብዛል። …

እኛንም እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ከፍ ለማድረግ እንድንካፈል ጋብዞናል እናም አዝዞናል። ይህን ለማድረግም በጥምቀት ውሀዎች እና በእግዚአብሔር ቤተመቅደሶች ውስጥ ቃል ኪዳኖች ገብተናል። ይህን ቃል ኪዳንንም በሰንበቶች ቅዱስ ቁርባንን ስንወስድ እናሳድሳለን።”1

በኤጲስ ቆጶስ ወይም በቅርንጫፍ ፕሬዘደንት አመራር ስር፣ የአካባቢው መሪዎች በመንፈሳዊ እና በስጋዊ ደህንነት እርዳታ ያቀርባሉ። የማገልገል እድል የሚጀምረውም የሚጎበኟቸውን እያንዳንዷ እህትን ፍላጎት እንዴት ለማርካት እንደሚችሉ ለማወቅ መነሳሻ በሚፈልጉት የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች ነው።

ከቅዱሳት መጻህፍት

ሉቃስ 10፥25–37ያዕቆብ 1፥27ሞዛያ 4፥2618፥8–11 ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 104፥18

ከታሪካችን

በሰኔ 9፣ 1842 (እ.አ.አ)፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶችን “ደሆችን እንዲረዱ” እና “ነፍሳትን እንዲያድኑ” ሀላፊነት ሰጣቸው።2 ይህም አላማ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ዋና አላማ ነው እናም “ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም” (1 Corinthians 13:8) በሚለው መመሪያ ይገለጻል።

አምስተኛ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት የነበሩት ኤመላይን ቢ. ዌስ እና አማካሪዎቻቸው ይህን መመሪያ በ1913 (እ.አ.አ) መጠቀም የጀመሩት የተመሰረትንበትን መርሆች እንድናስታውስበት ነበር፥ “ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ሴቶች መልካም በሆነ ድርጅት የታመሙት ለመንከባከብ፣ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ለመርዳት፣ ያረጁትን ለማፅናናት፣ የማይጠነቀቁትን ለማስጠንቀቅ፣ እና ወላጆች የሞቱባቸውን ለመደገፍ በክህነት ጥሪ ህጋዊ ስልጣን እንዲሰጣቸው በገለጸበት የተነሳሳ ትምህርቶችን በጥብቅ መያዝ አላማችን ነው ብለን እናውጃለን።”3

ዛሬ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እንደ እህቶች ለጎሪቤቶቻቸው የክርስቶስ ንጹህ ፍቅር የሆነቸውን ልግስናን ለመስጠት የምትችል አለም አቀፍ ድርጅት ነች (ሞሮኒ 7፥46–47ተመልከቱ)።

ማስታወሻዎች

  1. ሔንሪ ቢ. አይሪንግ፣ “Opportunities to Do Good፣” Liahona እና Ensign፣ ግንቦት 2011፣ 22።

  2. ጆሴፍ ፊልዲንግ ስሚዝ፣ በ Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society ውስጥ (2011)፣ 63።

  3. Daughters in My Kingdom፣ 63።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. በመንፈስ እና በስጋ ራሴን እና ቤተሰቦቼን ለመርዳት እንዴት ተዘጋጅቻለሁ።

  2. የምጠብቃቸውን እህቶች ፍላጎት ለማሟላት ስረዳ እንዴት የአዳኝን ምሳሌ ለመከተል እችላለሁ?