2015 (እ.አ.አ)
ድል በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት
ማርች 2015


ወጣቶች

ድል በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት

ብዙ ምግብ በመብላት ችግር ነበረብኝ። ተደጋጋሚው የቁንጣን ህመሜ በአስጨናቂ ታላቅ የጥፋተኝነት ስሜቴ፣ በንዴቴ እና በሀዘኔ የመጣ ውጤት ነው። ችግሬን ለማሸነፍ ስጥር በጣም ደካማነት ተሰማኝ።

ለረጅም ጊዜያት የአዳኝ የኃጢያት ክፍያ እኛን የሚያድን ብቻ ሳይሆን ቤዛችን እንደሚሆን እና ፍጹም እንደሚያደርገን፣ እናም ይህም ፍጹም ላልሆነው ከሚያስፈልግ በላይ መብላቴ እንደሚሰራም ረስቼ ነበር።

ራሴን ለአዳኜ አሳልፌ ለመስጠት ወሰንኩኝ። ጸለይኩኝ። ደካማኔቴን እና ለጸጋ ያለኝን ፍላጎት ከልብ ተቀበልኩኝ፣ እና ከዚያም የሰማይ አባትን በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ በመለኮታዊ እርዳታው እንዲባርከኝ ጠየኩኝ። በዚያ ምሽት ልጁን ለመርዳት የማይመዘን ፍላጎት እንዳለው እና ምኞቱን ለማሟላት መጠየቅ የማይቻል ሀይል እንዳለው የአፍቃሪ አባት ማረጋገጫ ተሰማኝ።

ከዚያ ምሽት ጀምሮ፣ ምግብ በእኔ ላይ ተመሳሳይ አድካሚ ተፅዕኖ የለውም። ኢየሱስ ክርስቶስ ለውጤታማነቴ ምክንያት እንደሆነ አውቃለሁ። ልክ እንደ ጳውሎስ፣ “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን [እንደምችል]” እየተማርኩኝ ነው (ፊልጵስዮስ 4፥13)። “በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋናይሁን” (1 ቆሮንቶስ 15፥57) የሚለውን የጳውሎስን ሌላ ትምህርት በምንም ላለመርሳት እየጣርኩኝ ነው።

አትም