2015 (እ.አ.አ)
በደግ ክንዶቹ ውስጥ ተከበን
ማርች 2015


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ የመጋቢት 2015 (እ.አ.አ)

በደግ ክንዶቹ ውስጥ ተከበን

ልክ እንደ ብዙ ሌሎች ሰዎች፣ በሚያስደስቱ ስዕል እና ሙዚቃ ስራዎች አብዛኛውን ጊዜ እነሳሳለሁ።

ይህ የሚያሳዝነው ስዕል አዳኝ በጌትሰመኔ የአትክልት ስፍራ ውስጥ ተንበርክኮ ያሳያል። ሲጸልይም፣ መላዕክ በአጠገቡ ቆሞ፣ በደግ ክንዶቹ አቅፎ፣ መፅናኛን፣ የሰማይ እርዳታን፣ እና ድጋፍን ሰጠው።

ይህን ስዕል ለረጅም ጊዜ ባሰላሰልኩት ቁጥር፣ ልቤ እና አዕምሮዬ የበለጠ መግለጽ በማይቻል ሩህሩህነት እና ምስጋና ይሞላል። ትንሽም ቢሆን፣ አዳኝ የአለምን ኃጢያቶች በራሱ ላይ በወሰደበት በታላቅ የሟች ህይወቱ ስራ መፈጸሚያ ላይ በአጠገቡ መገኘት ምን ይሆን እንደነበር ይሰማኛል። አብ ለልጆቹ ስላለው መጨረሻ ስለሌለው ፍቅር እና ርህራሄ እደነቃለሁ። ኃጢያት የሌለው ወልድ ለሰው ዘር በሙሉ እና ለእኔ ላደረገውም በታላቅ ምስጋና እጥለቀለቃለሁ።

የእግዚአብሔር ልጅ መስዋዕት

በእያንዳንዱ አመት በዚህ ጊዜ ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ዘር በሙሉ ያደረገውን መስዋዕት እናስታውሳለን እና እናሰላስላለን።

ከጌትሰመኔ እስከ ጎልጎታ ድረስ ለእኛ ያደረገው እኔ መረዳት ከሚችለው በላይ ነው። የኃጢያቶቻችንን ሸከም በራሱ ላይ ወሰደ እናም ለአዳም የመጀመሪያ መተላለፊያ ብቻ ሳይሆን ህይወት ለነበራቸው ለብዙ ቢልዮን ለሚሆኑ ነፍሳት ኃጢያቶች እና መተላለፎች ቤዛ ከፈለ። ይህም ዘላለማዊ፣ ቅዱስ መስዋዕት “ከስቃዩ የተነሳ [እንዲንቀጠቀጥ] እናም ከእያንዳንዱ ቀዳዳ [እንዲደማ] እናም በአካል እና በመንፈስ [እንዲሰቃይ]” አደረገው (ት. እና ቃ. 19፥18)።

ለእኔ ተሰቃየ።

ለእናንተም ተሰቃየ።

የዚህ መስዋዕትን ውድ ትርጉም ሳስብበት ነፍሴ በምስጋና ትጥለቀለቃለች። ይህን ስጦታ የሚቀበሉ በሙሉ እና ልባቸውን ወደ እርሱ የሚያዞሩ፣ እንከናቸው ምንም የጠቆረ ቢሆን እና ሸከማቸው ምንም ከባድ ቢሆን፣ ይቅርታ ለማግኘት እና ከኃጢያቶቻቸው ለመጽዳት እንደሚችሉ ማወቄ ትሁት ያደርገኛል።

እንደገና እንከን የለሽ እና ንጹህ መሆን እንችላለን። በውድ አዳኛችን ዘላለማዊ መስዋዕት መዳን እንችላለን።

ማን ያፅናናናል?

ማናችንም ጌታ የተሰቃየውን ያህል ስቃይ ሊያጋጥመን ባይችልም፣ እያንዳንዳችን ሀዘናችን መሸከም ከምንችለው በላይ የሆነ የሚመስለን የራሳችን ጭለማ እና መራራ ለመቀበል የሚያስቸግሩ ሰአቶችም ይኖሩናል። የኃጢያቶቻችን ክብደት እና ጸጸት እኛን ያለምህረት የሚጨቁኑበት ጊዜም ይኖራል።

ይህም ቢሆን፣ በእነዚያ ጊዜ ልባችንን ወደ ጌታ ከፍ ካደረግን፣ በእርግጥም እርሱ ያውቃል እና ይረዳል። በአትክልት ስፍራው ውስጥ እና በመስቀል ላይ ስለራሱ ሳያስብ ለእኛ የተሰቃየው እርሱም አሁን ያለመፅናኛ አይተወንም። እኛን ያጠነክራል፣ ያበረታታል፣ እናም ይባርካል። በደግ ክንዶቹም ይከበናል።

ለእኛም ከመላእክ በላይ ይሆንልናል።

የተባረከ መፅናኛ፣ መፈወሻ፣ ተስፋ፣ እና ምህረት ያመጣልናል።

እርሱ ቤዛችንስለሆነ።

አዳኛችን።

ምህረተኛ አዳኛችን እና የተባረከ አምላካችን።

ማስታወሻ

  1. በፍራንስ ሽዋርትዝ መቃብር ላይ የተናገረው ቄስ እንዳለው፣ “ስዕሉ በመለኮት የተባረከ እና ከምንም ስብከት በላይ ብቁ የሆነ ነው” (Emmilie Buchanan-Whitlock, “History of Artists’ Lives Gives Greater Context for Exhibit,” Deseret News, Sept. 29, 2013, deseretnews.com)።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

ከማስተማራችሁ በፊት፣ የምታስተምሯቸው ሰዎችን ልዩ ፍላጎት ለመረዳት የመንፈስን መመሪያ ፈልጉ። ከፕሬዘደንት ኡክዶርፍ መልእክት ምንባብ ስትካፈሉ፣ ስለአዳኝ እና ስለሚያድነው መስዋዕቱ ምስክራችሁን አቅርቡ። የምታስተምሯቸውንም የኃጢያት ክፍያው ለእነርሱ ምን ትርጉም እንዳለው እና “ጭለማ እና መራራ ሰአቶቻቸው” ወቅት የጌታ መፅናኛ እንዴት እንደተሰማቸው መጠየቅን አስቡ።

አትም