2015 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶስ ባህሪያት፥ መፅናት እና ትዕግስት
ማርች 2015


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት መልእክት፣ የመጋቢት 2015 (እ.አ.አ)

የኢየሱስ ክርስቶስ ባህሪያት፥ መፅናት እና ትዕግስት

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ እሹ። የአዳኝን ህይወት እና ተልእኮ መረዳት በእርሱ ያላችሁን እምነት የሚያሳድገው እና በሴቶች የቤት ለቤት ትምህርት ምክንያት የምትንከባከቧቸውን የሚባርከው እንዴት ነው? ለተጨማሪ መረጃ ወደ ሂዱ reliefsociety.lds.org

ምስል
የሴቶች መረዳጃ ማህበር ማህተም

እምነት፣ ቤተሰብ፣ እርዳታ

ትዕግስት በአብዛኛው ጊዜ እንደጸጥተኛነት፣ እንደማይታገል ጸባይ ይታሰብበታል፣ ነገር ግን የቀዳሚ አመራ ሁለተኛ አማካሪ ፕሬዘደንት ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ እንዳሉት፣ “ትዕግስት ባለመታገል መተው ወይም በፍርሀት ምክንያት አለማድረግ አይደለም። ትዕግስት ማለት ንቁ መጠበቅ እና መፅናት ነው። ይህም የልባችን ፍላጎት ቢዘገይም፣ ከአንድ ነገር ጋር መቆየት ማለት ነው። ትዕግስት መፅናት ብቻ አይደለም፤ በደንብ መፅናት ነው!”

በቅድመ ምድራዊ ሕይወታችን ውስጥ፣ የሰማይ አባት ለእኛ ለመንፈስ ልጆቹ እቅድ አዘጋጀልን እናም እኛ ወደ ምድር ለመምጣት ባለን እድል በመደሰት ጮህን (ኢዮብ 38፥7 ተመልከቱ)። በምድር ህይወታችን ፍላጎታችንን ከእርሱ ጋር አንድ ለማድረግ ስንመርጥ፣ እርሱም “ለብዙ ነፍስ መዳኛ [በእጆቹ] መሳሪያ [ያደርገናል]” (አልማ 17፥11)።

ፕሬዘደንት ኡክዶርፍም ቀጥለው፣ “ትዕግስት ማለት ለመቀየር የማንችለውን መቀበል እና ይህን በተስፋ፣ በጸጋ፣ እና በእምነት መቋቋም ማለት ነው። ይህም ማለት “ልጅ አባቱ የሰጠውን እንደሚቀበለው ሁሉንም ነገሮች የተሰጡትን ለመቀበል ፈቃደኛ” መሆን ማለት ነው” [ሞዛያ 3፥19]። በመጨረሻም፣ ትዕግስት ማለት በሁሉም ቀናት በሁሉም ሰዓት፣ እንዲሁም ይህን ለማድረግ በሚከብድበትም ጊዜ፣ ‘የጌታን ትዕዛዝ በመጠበቅ ጠንካራ፣ ፅኑና፣ የማትነቃነቅ’ [1 ኔፊ 2፥10] መሆን ማለት ነው።”1

ተጨማሪ ቅዱሳት መጻህፍቶች

መዝሙር 40፥1ገላትያ 5፥22–232 ጴጥሮስ 1፥6አልማ 17፥11

ከቅዱሳት መጻህፍት

ቅዱሳት መጻህፍት እንደሚነግሩን፣ በምድር ህይወትቻን እኛ “በስቃይህ ታጋሽ ሁን፣ ብዙም ያጋጥምሀልና” ተብለናል።፣ እግዚአብሔር ከዚያም ይህን የሚያፅናና ቃል ኪዳን ሰጥቶናል፣ “በጽናት አሳልፋቸው፣ እነሆም እስከመጨረሻዎቹ ቀኖችህም እንኳን እኔ ከአንተ ጋር ነኝ” (ት. እና ቃ. 24፥8)።

የሚቀጥለው የመፅሐፍ ቅዱስ ታሪክ የትዕግስት እና የእምነት ምሳሌ ነው።

“ከአሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፥ በኋላውም ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፥ የደምዋም ፈሳሽ በዚያን ጊዜ ቆመ።

“ኢየሱስም አንድ ሰው ዳስሶኛል፥ ኃይል ከእኔ እንደ ወጣ እኔ አውቃለሁና አለ።

“ሴቲቱም እንዳልተሰወረች ባየች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፥ በምን ምክንያትም እንደ ዳሰሰችው ፈጥናም እንደ ተፈወሰች በሕዝቡ ሁሉ ፊት አወራች።

“እርሱም። ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ አላት” (ሉቃስ 8፥43–48)።

እንደ እርሷም፣ እኛ የኃጢያት ክፍያው ሊፈውሰን ለሚችለው፣ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ስንቀርብ በረከቶችን እና መፅናኛን፣ እንዲሁም መፈወሻን ማግኘት እንችላለን።

ማስታወሻ

  1. ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “Continue in Patience,” Liahona, ግንቦት 2010(እ.አ.አ.)፣ 57፣ 59።

ይህን አስቡበት

ከሉቃስ 8 ታሪክ ውስጥ፣ የዚህች ሴት የአመቶች ትዕግስት እና ከዚያም በኢየሱስ ክርስቶስ የነበራት እምነት እንዴት አሸለማት?

አትም