2015 (እ.አ.አ)
ከቤተሰቦቼ ጋር ለዘለአለም ተሳስሬ
ጁን 2015


ወጣቶች

ከቤተሰቦቼ ጋር ለዘለአለም ተሳስሬ

ደራሲዋ በዩታ፣ ዩኤስኤ ነው የምትኖረው።

በሶስት አመቴ ለጉዲፈቻ ስወሰድ፣ ለጉዲፈቻ የሚወስዱኝ ቤተሰቦቼ የቤተክርስቲያን ስነ-ስርዓቴን 12 አመት ከሆነኝ በኋላ ለማድረግ ከተስማሙ ብቻ ወላጅ እናቴ ጉዲፈቻው እንዲፈፀም ፈቀደች። ምርጫውን በራሴ ለማድረግ ማደግ እንዳለብኝ አሰበች፣ ነገር ግን መጠበቁ በጣም ከባድ ነበር።

አዎ፣ ብዙ ጓደኞቼ ስምንት አመት ሲሆናቸው ሲጠመቁ ማየት ከባድ ነበር፣ ነገር ግን እንደውም የበለጠ ከባድ የነበረው ጉዲፈቻ ከወሰዱኝ ቤተሰቦቼ እና አምስት ታላላቅ ወንድም እና እህቶቼ ጋር አስራሁለት አመት እስኪሞላኝ ድረስ መታተም አለመቻሌን ማወቄ ነበር። እኔ ላይ የሆነ ነገር ተፈጥሮ ከእነሱ ጋር መታተም ላልችል እችላለሁ ብዬ ፈርቼ ነበር።

የ12ኛ አመት ልደቴ ሲቃረብ፣ ለጥምቀቴ እና ከቤተሰቤ ጋር መታተምን ማቀድ ጀመርን። ወላጆቼ የትኛው ቤተ-መቅደስ እንድንታተም እንድመርጥ ፈቀዱልኝ። የሳንዲያጎ ካሊፎርኒያ ቤተ-መቅደስ በጣም ውብ እንደነበረ ሁሌ አስብ ነበር፣ ስለሆነም መላ ቤተሰቤ ለመታተም ወደ ካሊፎርኒያ በመኪና ለመሄድ ተስማሙ።

ከወላጆቼ እና ከእህት ወንድሞቼ ጋር የዘለአለም ቤተሰብ እስከምሆን ድረስ መጠበቅ አልቻልኩም። በህትመቴ ጊዜ፣ በቃሎች መግለፅ በሚከብድ ሁኔታ መንፈስ ቅዱስ በጠነከረ ሁኔታ ተሰምቶኝ ነበር። አሁን በመጨረሻ ከቤተሰቤ ጋር በመታተሜ፣ አሁን ለዘለአለም ከእነሱ ጋር መተሳሰሬን በማወቄ የጭነቀት ስሜቴ በመፅናናት እና በሰላም ተተክቷል።

አትም