2015 (እ.አ.አ)
ቤተሰቦች ለዘለአለም በአንድ ላይ መሆን ይችላሉ
ጁን 2015


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ሰኔ 2015 (እ.አ.አ)

ቤተሰቦች ለዘለአለም በአንድ ላይ መሆን ይችላሉ

ምስል
ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ

ቤተሰቦችን ለዘለአለም የሚያስር የክህነት ኃይል ከእግዚአብሔር ታላቅ ስጦታዎች መሃል አንዱ ነው። የደህንነትን ዕቅድ የሚረዳ እያንዳዱ ሰው ለዛ ዘለቄታ ላለው በረከት ይጓጓል። ቡራኬ በተደረገባቸው የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ቤተ-መቅደሶች በሚከናወነው በሕትመት ስነ-ስርዓት ውስጥ ብቻ ቤተሰቦች ለዘለአለም በአንድ ላይ እንደሚታሰሩ እግዚአብሔር ቃል-ኪዳን ይሰጣል።

ይህንን እውን የሚያደርጉት የክህነት ቁልፎች ወደ ምድር በነብዩ ኤሊያስ ለጆሴፍ ስሚዝ በከርትላንድ ቤተ-መቅደስ ውስጥ በዳግም ተመልሰዋል። በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በሕይወት ባሉ ነብያቶች በኩል እነዚያ የክህነት ቁልፎች በማይሰበር መስመር እየተላለፉ ይገኛሉ።

አዳኙ በምድራዊ አገልግሎቱ ውስጥ ቤተሰብን ስለሚያስር ኃይል የሐዋርያቶች አለቃ ለሆነው ለጴጥርስ በሰጠው ቃሎች ውስጥ እንደዚህ ሲል ተናገረ፣ “እውነት እላችኋለሁ፣ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፣ በምድር የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል” (ማቴዎስ 18፥18)።

በሰሌስቲያል ቤተ-መንግስት ውስጥ ብቻ ነው ለዘለአለም እንደቤተሰቦች ለመኖር የምንችለው። እዛ በሰማይ አባታችን እና በአዳኙ ፊት እንደቤተሰቦች መሆን እንችላለን። ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንደዚህ አይነት አስደናቂ ልምድን በትምህርት እና ቃል-ኪዳኖች ውስጥ ገለጿል፥

“አዳኛችን በሚገለጥበት ጊዜ እርሱ እንዳለ እናየዋለን። እርሱም እንደ እኛው ሰው እንደሆነም እናያለን።

“እና በዚህ በመካከላችን የሚገኘው ማህበራዊ ግንኙነት፣ አሁን የማናገኘውን ነገር ግን ዘለአለማዊ ክብር ተጨምሮበት፣ በዚያም እናገኘዋለን።” ት እና ቃ 130፥1–2)።

ይህ ጥቅስ በቤተሰባችን ውስጥ ባለን ግንኙነት በሙሉ ልብ ለሰማይ ስነ-ስርዓት እንድናልም ሀሳብ ይሰጣል። በሕይወት ላሉ እና ለሞቱ የቤተሰብ አባሎቻችን በሰማይ የሚያስረንን የክህነት ስነ-ስርዓቶች ለእነሱ ለመስጠት የተቻለንን ሁሉ ለማድረግ መጨነቅ እንችላለን።

ብዙዎቻችሁ፣ ማለትም ወጣት እና አዛውንት፣ ያንን እያደረጋችሁ ነው። እናንተን በአንድ ላይ የሚያትማችሁን ስነ-ስርዓቶችን ገና ያልተቀበሉትን የቅድመ አያታችሁን ስሞች ፈልጋችኋል።

ሁላችሁም ማለት ይቻላል በክህነት ኃይል በቤተሰቦች ውስጥ ያልታተሙ በሕይወት ያሉ ቤተ ዘመዶች አሏቹ። ብዙዎችም የክህነት ስነ-ስርዓቶችን የተቀበሉ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን ቃል-ኪዳኖች እየጠበቁ ያልሆኑ በሕይወት ያሉ ቤተ ዘመዶች አሏቸው። ለእነዛ ቤተ ዘመዶች ሁሉ በእምነት እርዳታ ለማቅረብ እንድትችሉ እግዚአብሔር ይባርካችኋል። ጌታ ሌሎችን ወደ እርሱ ለማምጣት ለሚሄዱት ለደቀ መዝሙሮቹ የሚገባው ቃል-ኪዳን አላችሁ፥

“እናም ማንም ቢቀበላችሁ፣ እዚያ እኔም እገኛለሁ፣ ከፊታችሁ ቀድሜ እጓዛለሁና። በቀኛችሁ እና በግራችሁ እሆናለሁ፣ እናም መንፈሴም በልቦቻችሁ ውስጥ ይገኛል፣ እናም መላእክቶቼም እንዲያዝሏችሁ ይከብቧችኋል።” ት እና ቃ 84፥88)።

በቢሮዬ መስኮት ሁል ቀን ሙሽሪቶች እና ሙሽራዎች በሚያምሩ አበባዎች እና ፏፏቴዎች መሃል ፎቶ ሲነሱ አያለሁ። ፎቶ አንሺዎች የጋብቻ ፎቶ እስከሚያነሱ ድረስ ብዙውን ጊዜ ሙሽራው የሱን ሙሽሪት ለተወሰነ ደረጃ እየተንገዳገደ በክንዶቹ ይሸከማል። ያንን ባየሁበት ሰአት ሁሉ፣ —አንዳንድ ጊዜ ከጋብቻቸው ቀን አጭር ጊዜ በኋላ ሕይወት ከባድ ሲሆን በተለያየ መንገድ— እርስ በራሳቸው መሸካከም የነበረባቸውን የማቃቸውን ጥንዶችን አስባለው። ስራ ሊጠፋ ይችላል። ልጆች ከታላቅ ችግሮች ጋር ሊወለዱ ይችላሉ። ሕመም ሊመጣ ይችላል። እናም ከዛ —ቀላል በነበረበት ጊዜ— ሌሎች ለእኛ እንዲያደርጉልን የምንፈልገውን ለሌሎች የማድረግ ልምዶች በውስጣችን አለ ብለን ከምናስበው የበለጠ ሲወስድብን ጀግኖች ያደርገናል።

ወደ እግዚአብሔር መገኛ ይዘን መሄድ የምንችለው አይነት ግንኙነት ለቤተሰቦቻችን መለገስ ይኖርብናል ። ጥቃት ላለማድረስ ወይም ተጠቂ ላለመሆን መጣር ይኖርብናል። በፍጥነት እና ሙሉ በሙሉ ይቅር ለማለት መወሰን እንችላለን። የሌሎችን ደስታ ከራሳችን በበለጠ ሁኔታ ለመሻት መሞከር እንችላለን። በንግግራችን ደግ መሆን እንችላለን። እነዚህን ነገሮች ለማድረግ በምንጥርበት ጊዜ፣ መንፈስ ቅዱስን ወደ ቤተሰቦቻችን እና ወደ ሕይወታችን እንጋብዛለን።

ከእኔ ለእናንተ ማረጋገጫ የሚሆነው፣ በጌታ እረዳታ እና ንስሃ በሚገቡ ልቦች በዚህ ሕይወት ውስጥ ለዘለአለም እንዲኖረን የምንፈልገውን አይነት ሕይወት ገፅታ ለመመልከት እንችላለን። የሰማይ አባት ይወደናል። ወደ እርሱ እንድንመለስ ይፈልጋል። አዳኙ፣ በሃጥያት ክፍያ ኃይሉ አማካኝነት፣ ቅዱስ ቤተ-መቅደስ ውስጥ መግባት እንድንችል የሚያስፈልገንን የልባችን ውስጥ መለወጫን፣ ከዛ በኋላ መጠበቅ የምንችለውን ቃል-ኪዳን መግቢያን፣ እና ከጊዜ በኋላም ለዘለአለም በሰለስቲያል ክብር ውስጥ —ዳግም በምንመለስበት ቤት— እንደ ቤተሰቦች የምንኖርበትን እውን አድርጎታል።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

የዘለአለም ቤተሰቦችን ትምህርት በምታካፍሉበት ጊዜ፣ ሽማግሌ ሪቻርድ ጂ ስካት የአስራሁለት ሐዋርያት ምልአተ ጉባኤ አባል ያሉትን ነገር አስቡ፥ “ሁል ጊዜ ቤተሰቦችን ለማጠንከር እሹ። ቤተሰቦች በቤተ-መቅደስ ውስጥ ከመታተም አስፈላጊነት ራእይ ጋር አስተምሩ። …የቤተ-መቅደስ ህትመት ስነ-ስርዓት ህልም ሲኖራችሁ፣ የእግዚአብሔርን ቤተ-መንግስት በመሬት ላይ ለመገንባት ትረዳላችሁ” (“I Have Given You an Example፣”Liahona፣ ግንቦት 2014 (እ.አ.አ)፣ 34)። የምታስተምሯቸውን ሰዎች ቤተ-መቅደስ ውስጥ የመታተምን ጥቅም ህልም እንዲያገኙ እንዴት ማስተማር ትችላላችሁ? ገና ያልታተሙትን ሰዎች ለዛ ስነ-ስርዓት መውሰድ የሚያስችሉትን ደረጃዎች ለመወያየት ጋብዙ። የታተሙትን ሰዎች የዘለአለም ቤተሰብ ህልማቸውን እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ እና የእርስ በእርሳቸው ግንኙነቶች ለማሻሻል እንዴት መስራት እንዳለባቸው ለመወያየት ጋብዙ።

አትም