2016 (እ.አ.አ)
ወደ ደስታ የሚመሩ ድርጊቶች
ጃንዩወሪ 2016


ወጣቶች

ወደ ደስታ የሚመሩ ድርጊቶች

ፕሬዘዳንት ኤይሪንግ እንዲህ ያስተምራሉ “ለምናፈቅራቸው ሰዎች የምንፈልገው ደስታ በእነርሱ ምርጫዎች ላይ የተወሰነ ነው።”

ምርጫዎች ሊያመጡ ስለሚችሉት ተፅእኖ ከኔፊ፣ ላማን፣ እና ልሙኤል ምሳሌዎች ማንበብ ትችላላችሁ። ላማን እና ልሙኤል አጉረመረሙ እና ትእዛዛትን መጠበቅ አልፈለጉም ነበር ( 1ኛ ኔፊ 2:12ተመልከቱ)። በውጤቱም፣ እነርሱ እና ትውልዳቸው ተረግመዋል እናም ከጌታ እይታ ተወግደዋል ( 2ኛ ኔፊ 5:20–24ተመልከቱ)። ኔፊ ትእዛዛትን ለመታዘዝ መረጠ ( 1ኛ ኔፊ 3:7)፣ እና በዚያ ምክኒያት፣ እርሱ እና ህዝቦቹ “በደስታ ኖሩ” (2ኛ ኔፊ 5፡27)።

ፃዲቅ እና ደስተኛ ለመሆን መምረጥ ትችላላችሁ። ነገር ግን አሁንም በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች ወደ ስቃይ እና ምቾት አልባነት የሚመሩ ደካማ ምርጫዎችን ያደርጉ ይሆናል። እነዚያ ውሳኔዎችን የሚያደርጉት እነርሱ ሲሆኑ፣ የእናንተ ምሳሌ ምርጫዎቻቸውን መልካም በማድረግ አስተዋፅኦ ሊኖረው ይችላል። የእናንተ ምርጫዎች ለሌሎች ደስታን እንዴት ሊያመጡ ይችለሉ? በአውንታዊ መልኩ በዙሪያቹ ያሉ ሰዎች ላይ ተፅእኖ ማድረግ እና ደስታ እንዲሰማቸው መርዳት የምትችሉባቸውን የተለያዩ መንገዶች ከቤተሰባችሁ ጋር ተወያዩ።

አትም