የቀዳሚ አመራር መልዕክት፣ ጥር 2016 (እ.አ.አ)
ለምናፈቅራቸው ሰዎችደስታ
ሁላችንም ለምናፈቅራቸው ሰዎች ደስታን እንፈልጋለን፣ እና በተቻለው መጠን እነርሱ እንዳይሰቃዩ እንፈልጋለን። በመጽሐፈ ሞርሞን ውስጥ ስለ ደስታ እና ስቃይ የተፃፉትን እያነበብን፣ የምናፈቅራቸውን ሰዎች ስናስብ ልባችን ይላወሳል። ስለ የደስታ ጊዜ እውነተኛ ፅሁፍ የሚከተለው ነው፤
“እናም እንዲህ ሆነ በህዝቡ ልብ ውስጥ ባለው የእግዚአብሔር ፍቅር የተነሳ፣ በምድሪቱ ፀብ አልነበረም።
“እናም ቅናት፣ ቁጣ፣ ሁከት፣ ዝሙት፣ መዋሸትም፣ ግድያም ሆነ ዝሙትን የሚቀሰቅስ ነገር አልነበረም፤ እናም በእርግጥ በእግዚአብሔር እጅ ከተፈጠሩት ሰዎች መካከል እንደዚህ ያለ ደስተኛ ሊሆን የቻለ ህዝብ አልነበረም።”
ከዛም እንዲህ እናነባለን፤
“እናም እነርሱ እንዴት የተባረኩ ነበሩ! እናም እነርሱ እንዴት የተባረኩ ነበሩ ምክንያቱም ጌታ በስራዎቻቸው ሁሉ ባርኳቸዋልና አዎን አንድ መቶ አስረኛው ዓመት እስኪያልፍ እንኳን ተባርከዋል እናም በልፅገዋል እናም ከክርስቶስ ጀምሮ የመጀመሪያው ትውልድ አልፎአል እናም በምድሪቱ ሁሉ ፀብ አልነበረም” (4ኛ ኔፊ 1፤15–16፣ 18)።
የክርስቶስ አፍቃሪ ደቀመዛሙርት እንደዚህ አይነት በረከት እንዲኖር ለሌሎች እና ለራሳቸው ይፀልያሉ እና ይጥራሉ። ከመጽሐፈ ሞርሞን ፅሁፎች እና፣ አብዛኞቻችን ባለን የግል ተሞክሮዎች፣ የደስታ ስጦታን ማግኘት እንደሚቻል እናውቃለን። የደስታ መንገድ በደንብ የተመላከተ እንደሆነ እናውቃለን። ከአዳኝ ጉብኝት በኋላ በኔፊያውያን እንደሆነው፣ “የእግዚአብሔር ፍቅር” በልባችን ካልሰረፀ በቀር፣ ደስታን ማግኘት ቀላል እንዳልሆነም እናውቃለን።
ያ ፍቅር በኔፋውያን ልብ ውስጥ ነበር ምክንያቱም ያ እንዲቻል የሚያደርገውን ህግ ጠብቀው ነበርና። ተወዳጁ የሰማይ አባታችንን ከልብ በመነጨ ተማፅኖ በሚጀምረው፣ በቅዱስ ቁርባን ፀሎት ውስጥ ያ ህግ በአጭሩ ይገኛል። ከልብ በተሞላ እምነት እና ለግል አዳኛችን ባለን ጥልቅ ፍቅር እንፀልያለን። በላያችን ላይ ስሙን ለመውሰድ፣ እርሱን ለማስታወስ፣ እና ትእዛዛቱን ሁሉ ለመጠበቅ ከልባችን እንወስናለን። በአጠቃላይ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ ሶስተኛው የስላሴዎች አባል፣ ለልባችን ስለ አብ እና ስለ ተወዳጅ ልጁ እንዲመሰክርልን በእምነት እንጥራለን። (ት እና ቃ 20፡77፣ 79ተመልከቱ።)
በመንፈስ ቅዱስ አጣማሪነት፣ የሰማይ አባታችን እና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ፍቅር እንድንፈልግ እና እንቀበል ዘንድ ልቦቻችን ሊቀየሩ ይችላሉ። ፍቅሩ በልባችን ያለውን ስሜት የማጣት መንገድ ቀላል እንደሆነ ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር ወደ ልቦቻችን የማስገባት መንገድም ቀላል ነው። ለምሳሌ፣ አንድ ሰው ለሰማይ አባት መፀለይን መቀነስ ወይም ሙሉ አስራት ላለመክፈል ወይም የእግዚአብሔርን ቃል መመገብ ለማቆም ወይም ድሆችን እና እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ችላ ለማለት ይወስን ይሆናል።
የጌታን ትእዛዛት ላለመጠበቅ የሚደረግ ማንኛውም ምርጫ መንፈስ ቅዱስ ከልባችን እንዲለቅ ምክንያት ሊሆን ይችላል። በዛ እጦት፣ ደስታ ይቀንሳል።
ለምናፈቅራቸው ሰዎች የምንፈልገው ደስታ በእነርሱ ምርጫዎች ላይ የተወሰነ ነው። ልጅን፣ የቤተክርስቲያን አዲስ ምእመን፣ ወይም ጓደኞቻችንን እንደምናፈቅራቸው ሁሉ፣ መንፈስ ቅዱስ እንዲነካቸው እና ልባቸውን ይቅር ዘንድ ብቁ ለመሆን ትእዛዛትን አንዲጠብቁ ልናስገድዳቸው አንችልም።
መስጠት የምንችለው የተሸለ እርዳታ ቢኖር የምናፈቅራቸው ሰዎች የእራሳቸውን ምርጫዎች እንዲቆጣጠሩ በሚመራቸው ማንኛውም ነገር ነው። እናንተ ማቅረብ በምትችሉት ግብዣ አልማ ያንን አድርጎታል።
“በጌታ ፊት እራሳችሁን ትሁት ታደርጉ ዘንድ፣ እናም ቅዱስ ስሙን ትጠሩ ዘንድ፣ እናም ያለማቋረጥ እንድትተጉ እንዲሁም እንድትፀልዩ፣ ከሚቻላችሁ በላይም እንዳትፈተኑም፣ እናም ትሁት፣ የዋህ፣ ታዛዥ፣ ታጋሽ፣ ፍቅር የሞላባችሁ፣ እና ፅኑ መከራን ቻይ በመሆን በመንፈስ ቅዱስ የምትመሩ ሁኑ፤
“በጌታ እምነት ይኖራችሁ ዘንድ፤ ዘለአለማዊ ህይወትን ለመቀበል ተስፋ የሞላባችሁ፤ በመጨረሻው ቀን ከፍ እንድትሉና ወደ እረፍቱም እንድትገቡ የእግዚአብሔር ፍቅር ሁል ጊዜም በልባችሁ ይሁን” (አልማ 13:28–29)።
የምታፈቅሯቸው ሰዎች የዘለአለማዊ ደስታ መንገድን በመምረጥ አነሳሹን ግብዣ እንዲቀበሉ እፀልያለሁ።
© 2016 በIntellectual Reserve፣ Inc መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/15 (እ.አ.አ) ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/15 (እ.አ.አ) የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ጥር 2016 (እ.አ.አ) First Presidency Message, January 2016. ትርጉም Amharic 12861 506