2016 (እ.አ.አ)
ቤተሰብ፤ ለአለምየተላለፈአዋጅ
ጃንዩወሪ 2016


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክቶች፣ ጥር 2016 (እ.አ.አ)

ቤተሰብ፤ ለአለምየተላለፈአዋጅ

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ እሹ። የቤተሰብን አስተምሮት መረዳት በሴቶች የቤት ለቤት ትምህርት ምክንያት የምትንከባከቧቸውን የሚባርከው እንዴት ነው? ለተጨማሪ መረጃ ወደreliefsociety.lds.orgሂዱ

እምነት፣ ቤተሰብ፣ እርዳታ

በ1995 (እ.አ.አ) ውስጥ በአጠቃላይ የሴቶች መረዳጃ ስብሰባ፣ ፕሬዘዳንት ጎርደን ቢ ሂንክሊ (1910-2008 እ.አ.አ) ለመጀመሪያ ጊዜ ይህንን ሲያነቡ “ቤተሰብ፤ ለአለም አዋጅ፣” ቦኒ ኤል ኦስካርሰን፣ አጠቃላይ የወጣት ሴቶች ፕሬዘዳንት እንዲህ፣ ብለዋል፤ “ለዚህ የመገለጥ መዝገብ ግልፅነት፣ ቀላልነት፣ እና እውነታ አመስጋኝ ነን እናም ዋጋ የምንሰጠው ነው። … በቤተሰብ ላይ ያለው አዋጅ ለአለም ፍልስፍና ፍርድ ለመስጠት መመዘኛችን እየሆነ መጥቷል፣ እና የቀረቡት መርሆዎች… ከዛሬ 20 አመት በፊት በእግዚአብሔር ነብይ ለእኛ ሲሰጠን እውነት እንደነበሩት ሁሉ ዛሬም እውነት እንደሆኑ እመሰክራለሁ።”1

ካሮል ኤም ስቴፈንሰ፣ አጠቃለይ የሴቶች መረዳጃ ፕሬዘዳንት እንዲህ በማለት በተጨማሪ ተናግረዋል፣ “ከቤተሰብ አዋጅ ውስጥ፣ የሚከተለውን እንማራለን፣ ‘በቅድመ ሟችነት አለም ውስጥ፣ የመንፈስ ወንድ እና ሴት ልጆች እግዚአብሔርን እንደ ዘለአለማዊ አባታቸው ያውቁ እናም ያመልኩት ነበር’2 …

“… እያንዳንዳችን በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ እንካተታለን እና ተፈላጊዎች ነን።”3

ወላጆች ቤታቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን መጠበቅ ያለባቸው ጊዜ ላይ ነው የምንኖረው። “ቤተሰብ፤ ለአለም አዋጅ” ሊመራን ይችላል።

ተጨማሪ ጥቅሶች

ሞዛያ 8:16–17; ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 1:38

ህያው ታሪኮች

“ከታኦ ዩአን ታይዋን ካስማ፣ ከታኦ ዩአን ሶስተኛ አጥቢያ፣ ሊ ሜይ ቼን ሆ እንዳሉት ኣዋጁ የቤተሰብ ግንኙነቶች መለኮታዊ ባህሪ የሆኑትን እንደ እምነት፣ ትእግስት፣ እና ፍቅር ለማዳበር እንደሚረዱ መማራቸውን ተናግረዋል። ‘በአዋጁ መሰረት እራሴን ለማሻሻል ስሞክር፣ የእውነተኛ ደስታ ተሞክሮ ሊኖረኝ ይችላል፣’ ብለዋል።”4

አዋጁ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲነበብ በቦታው የነበሩ እና ከዛ በኋላም በአጠቃላይ የሴቶች መረዳጃ አመራር እንደ አማካሪ ያገለገሉት፣ባርባራ ቶምሰን፣ እንዲህ ብለዋል፤ ያላገባሁ ስለሆንኩኝ እና ምንም ልጆች ስላልነበሩኝ ይህ (የቤተሰብ አዋጅ) ከእኔ ጋር ብዙ ግንኙነት ያለው አልመሰለኝም ነበር። ነገር ግን ወዲያውም እንዲህ አሰብኩኝ ‘ይህ እኔንም የሚመለከት ነው። እኔ የቤተሰብ አባል ነኝ። እኔ የሴት ልጅ፣ እህት፣ አክስት፣ የወንድም ወይም የእህት ልጅ፣ የአጎት ወይም የአክስት ልጅ እና የልጅ ልጅ ነኝ። ከቤተሰቤ በህይወት ያለሁ ብቸኛው አባል ብሆን እንኳ፣ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባል ነኝ።’”5

ማስታወሻዎች

  1. ቦኒ ኤል ኦስካርሰን “Defenders of the Family Proclamation,” Liahona, ግንቦት 2015 (እ.አ.አ), 14–15.

  2. “ቤተሰብ፤ ለአለም አዋጅ,”Liahona, ህዳር 2010 (እ.አ.አ), 129።

  3. ካሮል ኤም ስቴፈንስ, “The Family Is of God,” Liahona, ግንቦት 2015 (እ.አ.አ), 11.

  4. ኒኮል ሴይሙር፣ “‘The Family: A Proclamation to the World’ reaches 10-Year Milestone, Liahona, ህዳር 2005 (እ.አ.አ), 127.

  5. ባርባራ ቶምሰን, በ Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society (2011 እ.አ.አ), 148.

ይህን አስቡበት

እንዴት ነው “ቤተሰብ፤ ለአለም አዋጅ” ለእኛ ጊዜ የሚሆን መዝገብ የሆነው?

አትም