2016 (እ.አ.አ)
የዘለአለማዊ አባታችን ሴት ልጆች
ኤፕረል 2016


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ሚያዝያ 2016 (እ.አ.አ)

የዘለአለማዊ አባታችን ሴት ልጆች

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ ጣሩ። “ቤተሰብ፤ ለአለም አዋጅ” መረዳት እንዴት እምነታችሁ በእግዚአብሔር እንዲዳብር እናም በጉብኝት ትምህርት በኩል የምትመለከትዋቸውን ሰዎች እንዴት ይባርካቸዋል? ለተጨማሪ መረጃ ወደ reliefsociety.lds.org ሂዱ።

ምስል
የሴቶች መረዳጃ ማህበር ማህተም

እምነት፣ ቤተሰብ፣ እርዳታ

እኛ “የእግዚአብሔር ዘመዶች መሆናችንን” ቅዱሳት መፅሀፍት ያስተምራሉ (ሐዋርያት ስራ 17፥29)። የነብዩ ዮሴፍ ስሚዝ ሚስት፣ ኤማ ስሚዝን፣ እግዚአብሔር “የእኔ ሴት ልጅ” ብሎ ገለፃት (ት እና ቃ 25፥1)። እኛ እያንዳንዳችን “ተወዳጅ መንፈስ… የሰማይ ወላጆች ሴት ልጆች” መሆናችንን የቤተሰብ አዋጅ ያስተምረናል።1

“[በቅድመ ሟችነት] አለም ውስጥ፣ ስለ ዘለአለማዊ የሴት ማንነት ተምረን ነበር፣” በማለት የአጠቃላይ የሴቶች መረዳጃ አመራር ውስጥ አንደኛ አማካሪዋ ካሮል ኤም ስቴፈንስ ተናገረች።

“በምድር ላይ የሟችነት ጉዞአችን እነዚህን እውነቶች አልቀየሩትም።”2

የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አባል ሽማግሌ ጄፍሪ አር. ሆላንድ እንዲህ አሉ፣ “የሰማይ አባታችሁ ስማችሁን ያውቃል እናም ሁኔታዎቻችሁንም ያውቃል”። “ጸሎታችሁን ይሰማል። ተስፋችሁን እናም ህልማችሁን ያውቃል፣ ፍራቻዎቻችሁን እና መሰላቸታችሁንም ጭምር።”3

“ሁላችንም በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ እንካተታለን እና እንፈለጋለን፣” አለች እህት ስቴፈንስ። “ምድራዊ ቤተሰቦች ሁሉ የተለያዩ መስለው ይታያሉ። እና ጠንካራ ባህላዊ ቤተሰቦችን ለመፍጠር የተቻለንን ስናደርግ፣ በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ አባል ለመሆን እንደ የጋብቻ ሁኔታ፣ የወላጅነት ሁኔታ፣ የገንዘብ ሁኔታ፣ የማህበራዊ ሁኔታ፣ ወይም በማህበራዊ መገናኛ ላይ እንኳን የምንለጥፈው አይነት ሁኔታ ምንም ለውጥ አያመጣም።”4

ተጨማሪ ጥቅሶች

ኤርምያስ 1፥5፤ ሮሜ 8፥16፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥23–24

ከታሪካችን

በመጀመሪያው እራይ መዝገብ ውስጥ፣5 ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ብዙ እውነታዎችን አረጋግጥዋል--የሰማይ አባታችን ስማችንን እንደሚያውቅም ጭምር።

ወጣቱ ጆሴፍ የትኛውን ቤተክርስቲያን መቀላቀል እንደነበረብት ለማወቅ ጣረ እናም ከያዕቆብ 1፥5 ላይ ምሬትን አገኘ። ጆሴፍ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ወሰነ።

በ1820 ውስጥ በአንድ ፀደይ ማለዳ፣ ለመፀለይ ወደ ዛፎች ውስጥ ሄዶ ነበር ነገር ግን ወዲያው በጨለማ ሀይል ውስጥ ተውጦ ነበር። ስለዚያም እንዲህ ፃፈ፥

“ልክ በዚህ ታላቅ የመነቃቃት ቅፅበት ላይ፣ የብርሀን አምድ በራሴ ትክክል ላይ አየሁ ከፀኃይ ብርሀን የበለጠ በላዬ ላይ እስኪያርፍ ድረስ በዝግታ ወረደ።

“ወዲያው እንደታየም ይዞኝ ከነበረው የጠላት ሀይል በመዳን ነጻ ሆንኩኝ። ብርሀኑም በእኔ ላይ ባበራም ጊዜ ብርሀናቸውና ክብራቸው ከሚገለፀው በላይ የሆነ ሁለት ሰዎች በአየር ከእኔ በላይ ቆመው አየሁ። አንዱም ስሜን በመጥራት እና ወደ ሌላው በማስመልከት አናገረኝ--ይህ ውድ ልጄ ነው። አድምጠው!” (የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥16-17)።

ማስታወሻዎች

  1. ቤተሰብ፥ ለአለም አዋጅ፣” Liahona፣ ህዳር 2010 (እ.አ.አ), 129።

  2. ካሮል ኤም ስቴፈንስ “The Family Is of God” Liahona፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 11።

  3. Jeffrey R. Holland፣ “To Young Women፣” Liahona፣ ህዳር 2005፣ 28።

  4. ካሮል ኤም ስቴፈንስ፣ “The Family Is of God፣” 11።

  5. Gospel Topics, “First Vision Accounts፣” topics.lds.orgተመልከቱ።

ይህን አስቡበት

የእግዚአብሔር ሴት ልጅ መሆናችሁን ማወቃችሁ በውሳኔዎቻችሁ ላይ እንዴት ተፅእኖን ያመጣል?

አትም