2016 (እ.አ.አ)
የሰማይ አባት በጉባኤ ንግግር አማካኝነት ተናገረኝ
ኤፕረል 2016


ወጣቶች

የሰማይ አባት በጉባኤ ንግግር አማካኝነት ተናገረኝ

ደራሲው በብራዚል ሰርጂፕ ውስጥ ይኖራል።

በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ምን ማጥናት እንዳለብኝ እርግጠኛ አልነበርኩም። እኔ መውሰድ ስለፈለኩት የትምህርት አይነት ብዙ ሰዎች በመጥፎ ሲያወሩ ነበር፣ ስለዚህ ከእኔ ውሳኔ ጋር መስማማቱን ለማወቅ ለጌታ ፀለይኩኝ።

በቀጣዩ ቀን የአጠቃላይ ጉባኤ ንግግርን በሊያሆናውስጥ ሳነብ ምላሹ መጣ። የሰማይ አባት ለእኔ መምረጥ እንደማይችል እንደነገረኝ ያህል--በእራሴ ማድረግ ያለብኝ ውሳኔ እንደነበር ተሰማኝ። ምንም ይሁን ምርጫዬ፣ ስኬታማ ለመሆን ጠንክሬ መስራት እንደሚኖርብኝ አውቅ ነበር።

ፀሎቴ ተመልሶ እንደነበር አውቃለሁ። የመንፈስ ቅዱስ ማረጋገጫ እንድወስን እረዳኝ። የተቻለኝን ጥረት ማድረግ እንዳለብኝ እናም የሰማይ አባት እንደሚረዳኝ አወኩኝ።