2016 (እ.አ.አ)
ትንቢት እና የግል መገለጥ
ኤፕረል 2016


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ሚያዝያ 2016 (እ.አ.አ)

ትንቢት እና የግል መገለጥ

እውነተኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዳግም ተመልሷል እናም ዛሬ በምድር ላይ አለ። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሁሌም ከሰማይ ቋሚ ምሬትን በሚቀበሉ ህያው ነብያት እና ሐዋርያቶች ትመራለች።

መለኮታዊ ሂደቱ በጥንትም እውነት ነበር። ከመፅሐፍ ቅዱስ ይህን እንማራለን፥ “በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምስጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም” (አሞፅ 3፥7)።

በነቢዩ ዮሴፍ ስሚዝ አማካኝነት እግዚአብሔር በእኛ ጊዜ በድጋሜ ተናግሯል። እርሱ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ከነ ሙሉነቱ በነብዩ ዮሴፍ አማካኝነት ገለጠ። ቅዱስ ክህነቱን ከነ ቁልፎቹ እና ሙሉ መብቶች፣ ሀይሎች እና ቅዱስ የክህነት ሀይል ግልጋሎቶቹ ጋር ዳግም መለሰ።

በእኛ ጊዜ፣ ለመናገር፣ ለማስተማር፣ እና ከእግዚአብሔር አብ እና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ባለ ስልጣን ለመምራት ህያው ነብያቶች እና ሐዋርያቶች ስልጣን ተሰቷቸዋል። አዳኝ ለነብዩ እንዲህ አለ፣ “እኔ ጌታ የተናገርኩትን፣ ተናግሬያለሁ፣ እና ያልኩትን አልመልስም፤ እናም ሰማይ እና ምድር ቢያፉም፣ የእኔ ቃል ግን አያልፍም፣ ነገር ግን ሁሉም ይሟላል፣ በእራሴ ድምፅም ወይም በአገልጋዮቼ ድምፅ ይሁን፣ አንድ ነው” (ት እና ቃ 1፥38)።

በአመት ሁለት ጊዜ ባለው አጠቃላይ ጉባኤ፣ የጌታን ቃላት ከአገልጋዮቹ በመስማት እድል ተባርከናል። ያ ከዋጋ በላይ የሆነ እድል ነው። ነገር ግን ያ እድል የሚወሰነው ለእነዚያ አገልጋዮች በተሰጡት ተመሳሳይ የመንፈስ ተፅእኖ ቃላቶቹን በምንቀበላቸው መጠን ላይ ነው (ት እና ቃ 50፥19-22 ተመልከቱ)። እነርሱ ምሬትን ከሰማይ እንደሚቀበሉት ሁሉ፣ እኛ እንደዛ ማድረግ አለብን። እናም ያ ተመሳሳይ የመንፈስ ጥረትን ከእኛ ይጠይቃል።

“የቤት ስራችሁን ስሩ”

ከአመታት በፊት ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ጉባኤ አባልዎች ውስጥ አንዱ የሆነው ለአጠቃላይ ጉባኤ ሲያዘጋጅ የነበረውን ንግግር እንዳነብ ጠየቀኝ። እኔ የጉባኤው አዲስ አባል ነበርኩ። ጌታ እንዲናገር የፈለገውን ቃላት እንዲያገኝ ልረዳው እንደምችል ባለው መተማመን ክብር ተሰማኝ። በፈገግታ እንዲህ አለኝ፣ “ኦ፣ ይሄ የንግግሩ 22ኛው ንድፍ ነው።”

ቀደም ብሎ ተወዳጁ እና መልካሙ ፕሬዘዳንት ሀሮልድ ቢ ሊ (1899-1973) በትልክ አፅእኖት ለእኔ የሰጠኝን ምክር አስታወስኩ፤ “ሀል፣ መገለጥን ማግኘት የምትፈልግ ከሆነ፣ የቤት ስራህን ስራ።”

22ኛው ንድፍን አነበብኩት፣ አሰላሰልኩ እናም ፀለይኩበት። በመንፈስ ቅዱስ ተፅእኖ ስር ሆኜ በተቻለኝ መጠን አጠናሁ። የዛ ጉባኤ አባል ንግግሩን ሲሰጥ፣ እኔ የቤት ስራዬን ፈፅሜያለሁ። በማገዜ እርግጠኛ አይደለሁም፣ ነገር ግን ንግግሩ ሲሰጥ ስሰማ እኔ ተለውጬ እንደነበር አውቃለሁ። እኔ ካነበብኩት እና እርሱ ከተናገረው ቃላት በላይ የሆኑ መልእክቶች ወደ እኔ መጡ። ቃላቶቹ በንድፉ ላይ ካነበብኳቸው በላይ ታላቅ ትርጉም ነበራቸው። እናም መልእክቱ ፍላጎቶቼን በሚወክል መልኩ፣ ለእኔ የተላከ ይመስል ነበር።

መገለጥን እና መነሳሳትን ለሚፈልጉት ለመስጠት መልእክቱን ይቀበሉ ዘንድ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ይፆማሉ እናም ይፀልያሉ። ከዛ እና ከብዙ ሌላ ተሞክሮዎች የተማርኩት፣ ህያው ከሆኑ ነብያት እና ሐዋርያትን ከመስማት የሚገኙትን ታላቅ በረከቶች ለማግኘት፣ መገለጥን የመቀበል ዋጋን እራሳችን መክፈል አለብን።

ጌታ መልእክቱን የሚሰሙትን ሰዎች ሁሉ ይወዳል፣ እናም የእያንዳንዱን ልቦች እና ሁኔታዎች ያውቃል። እያንዳንዱ ሰው በዘለአለማዊ ህይወት ጉዞ ላይ የትኛውን መንገድ መምረጥ እንዳለበት ወይም እንዳለባት በተሻለ የሚረዳ ማስተካከያ፣ ማበረታቻ፣ እናም የወንጌል እውነት የትኛው እንደሆነ እርሱ ያውቃል።

እኛ የአጠቃላይ ጉባኤ መልእክቶችን የምናዳምጥ እና የምንመለከት ሰዎች አንዳንዴ እንዲህ እናስባለን፣ “በተሻለ የማስታውሰው ምንድን ነው?” ለእያንዳንዳችን ጌታ ያለው ተስፋ መልሳችን እንዲህ እንዲሆን ነው፤ በአእምሮዬ እና በልቤ ውስጥ የሰማይ አባት እና አዳኝን ለማስደሰት ምን ማድረግ እንደምችል የመንፈስ ድምፅ ሲነግረኝ የተሰማኝን ጊዜያቶች በቼም አልረሳም።

ነብያትን እና ሐዋርያትን ስንሰማ እናም ልክ ፕሬዘዳንት ሊ ማድረግ የምንችለውን እንደነገሩን፣ ለመቀበል በእምነት ስንሰራ ያንን የግል መገለጥ መቀበል እንችላለን። ከተሞክሮ እና ከመንፈስ ምስክርነት ያ እውነት እንደሆነ እኔ አውቃለሁ።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

የጉባኤ አባሎቹን የስብሰባ ንግግር ንድፍ ስለ ማጥናቱ የፕሬዘዳንት ኤይሪንግን ታሪክ ጮክ ብሎ ለማንበብ አስቡ። እንዲህ ልትጠይቁ ትችላላችሁ፣ “መገለጥን የመቀበል ዋጋ ምንድን ነው?” ከውይይታችሁ በኋላ፣ “ለእግዚአብሔር አገልጋዮች በተሰጠው በተመሳሳይ የመንፈስ ተፅእኖ ስር” ቀጣዩን የአጠቃላይ ጉባኤ መልእክቶች ስለመቀበል እቅድ እዲያሰላስሉ እና እንዲተገብሩ የምትጎበኟቸውን ሰዎች መጋበዝ ትችላላችሁ።