2016 (እ.አ.አ)
ለእምነት በእውነት መቆም
ጁላይ 2016


ወጣቶች

ለእምነት በእውነት መቆም

ፕሬዘደንት ሞንሰን የመስራች ቤተሰብ ታሪክን ተናገሩ እናም ከዛ የፕሬዘደንት ጆርጅ አልበርት ስሚዝ ንግግርን እንዲህ ሲሉ ጠቀሱ፤ “ለቅድመ አያቶቻችሁ እምነት በእውነት ትኖራላችሁን? … [እነሱ] ለእናንተ ለከፈሉት መስእዋትነት ሁሉ ብቁ ለመሆን ጣሩ።” መስራች ቅድመ አያት ይኑራችሁም ወይም የመጀመሪያ የቤተክርስቲያን አባል ትውልድ ሁኑም፣ ምሬት ለመቀበል እና ለጥንካሬ የእምነት ተምሳሌቶችን ትመለከታላችሁን? መጀመር የምትችሉበት መልካም መንገድ ይሄው፥

1. የምታደንቋቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር አውጡ። የራሳችሁ የቤተሰብ አባላት (ያለፉ ወይም በህይወት ያሉ)፣ ጓደኞች፣ የቤተክርስቲያን መሪዎች፣ ወይም በቅዱሳት መፅሀፍት ውስጥ ያሉ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ።

2. እናንተ የምትወዱትን ያላቸውን ባህሪያት ፃፉዋቸው። እውነት እናታችሁ ታጋሽ ነችን? ምናልባት ጓደኛችሁ ለሌሎች ደግ ሊሆን ይችላል። በእርግጥም የካፒቴን ሞሮኒን ብርታት ተወዱ ይሆናል።

3. ከዝርዝራችሁ አንዱን ባህሪይ ምረጡና እራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁ፣ “ይህንን ባህሪይ እንዴት ነው የማገኘው? ይህንን በህይወቴ ውስጥ ለማሳደግ ምን ማድረግ አለብኝ?”

4. ይህንን ባህሪይ ለማሳደግ፣ ግባችሁን እንዲያስታውሳችሁ እቅዳችሁን ፃፉ እና ሁሌም በምታዩበት ቦታ ላይ አስቀምጡት። ለሰማይ አባት እርዳታ ፀልዩ እናም እድገታችሁን ሁሌም ተመልከቱ። ይህንን ባሕሪይ በተገቢው ሁኔታ እንዳሳደጋችሁ ሲሰማችሁ፣ ለማሳደግ ሌላ አዲስ ባህሪ መምረጥ ትችላላችሁ።

በህይወቶቻችን ታላቅ ባህሪዎችን በምናሳድግበት ወቅት፣ የቅድመ አያቶቻችንን እምነት እና የከፈሉትን መስእዋእትነት እያከበርን ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን በዙሪያችን ላሉት መልካም ተፅእኖ መሆንም እንደምንችልም አስታውሱ።