2016 (እ.አ.አ)
ለወላጅነት ያለን አቅም
ጁላይ 2016


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ሐምሌ 2016 (እ.አ.አ)

ወላጆች ለመሆን ያለን አቅም

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ እሹ። “ቤተሰብ፥ ለአለም አዋጅን” መረዳት እንዴት እምነታችሁን በእግዚአብሔር እንድታዳብሩ እናም በጉብኝት ትምህርት በኩል የምትመለከቷቸውን ሰዎች እንዴት ይባርካቸዋል? ለተጨማሪ መረጃ፣ ወደ reliefsociety.lds.org ሂዱ።

እምነት፣ ቤተሰብ፣ እርዳታ

“የእግዚአብሄር የመንፈስ ልጆች ምድራዊ ውልደት እንዲኖራቸው እናም ወደ ዘላለማዊ ህይወት የማደግን እድል እንዲያገኙ አስፈላጊ ነበር” ብለው የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ጉባዔ አባል ሽማግሌ ዴለን ኤች. ኦክስ አስተማሩ። “የታላቁ የደስታ እቅድ የመጨረሻ አላማን በመመልከት፣ በምድር ላይ እና በሰማይ ውስጥ የሚገኝ ታላቅ ሀብት ቢኖር ልጆቻችን እና ትውልዶቻችን እንደሆኑ አምናለሁ።”1

የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን አባል ሽማግሌ ኔል ኤል. አንደርሰን እንዲህ ብለዋል፥

“በቤተሰቦች እናምናለን፣ እንዲሁም በልጆች እናምናለን። …

“‘… እግዚአብሔር ለ[ኣዳም እና ሄዋን] እንዲህም አላቸው፣ ብዙ፤ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት’ [ዘፍጥረት 1፥28]። …

“ይህ ትእዛዝ አልተረሳም ወይም በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ወደ ጎን አልተተወም።”2

ሁላችንም በዚህ ምድር ላይ ወላጆች መሆን ባንችልም፣ በየትኛውም እድሜ ላይ ያሉ ልጆችን ማሳደግ እንችላለን። የሰማይ አባት ቤተሰብ አካል የመሆንን በረከቶች እንደሰታለን፣ እንዲሁም የምድራዊ ቤተሰብ አካል የመሆንን ደስታዎችን እና መከራዎችን ልምድ እናገኛለን። እናም ለብዙዎች፣ ወላጅነት በፊታችን ባልው ዘላለማዊነት ውስጥ ይጠብቃቸዋል።

ተጨማሪ ቅዱሳት መጻህፍቶች

ምሳሌ 127፥3፤ ማቴዎስ 18፥3–5፤ 1 ኔፊ 7፥1ሙሴ 5፥2–3

ህያው ታሪኮች

ሽማግሌ አንደርሰን እንዳሉት፣ “ዛሬ በአለማችን ውስጥ ብዙዎች ልጆች የመውለድን ጠቀሜታ ደባልቀውታል ወይም ማዘግየትን ይመርጣሉ ወይም በቤተሰብ ውስጥ የልጅ ብዛት ገደብ ያወጣሉ።” ሴት ልጆቼ አምስት ልጆች ባላት በአንድ ክርስቲያን እናት (የእኛ እምነት ተከታይ ያልሆነች) ወደ ተፃፈ ብሎግ እንድሄድ በቅርብ ነግረውኝ ነበር። እንዲህ ብላ ሀሳቧን አሰፈረች፤ ‘በዚህ ባህል ውስጥ [ማደግ]፣ በእናት ላይ መፅሀፍ ቅዱሳዊ እይታ ማግኘት በጣም ከባድ ነው። … ልጆች ውጤታቸው ከኮሌጅ በጣም ያነሰ ነው። በእርግጥም ከአለም ጉዞ አናሳ ሆንዋል። በትርፍ ጊዜአችሁ በማታ የመውጣት አቅም አናሳ ሆንዋል። በጅምናዚየም ሰውነታችሁን ማጠናከር አናሳ ሆንዋል። ያላችሁ ስራ ወይም አገኛለው ብላችሁ የምታስቡት ስራ አናሳ ሆንዋል።’ ከዛ ይህንን ጨመረች፤ ‘እናትነት በትርፍ ጊዜ የምናሳልፈው ነገር ሳይሆን፣ ጥሪ ነው። ከምስሎች የበለጡ ያማሩ መስሎዋችሁ ስላገኛችኋቸው አይደለም ልጆችን የምትሰበስቡት። ጊዜያችሁን አጣባችሁ የምታደርጉት ነገር አይደለም። እግዚአብሔር ጊዜን የሰጠን ለዛ ነው።’”3

ማስታወሻዎች

  1. ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “The Great Plan of Happiness፣” Ensign፣ ህዳር 1993፣ 72፣ 75።

  2. ኒል ኤል. አንደርሰን፣ “ህፃናት፣” Liahona፣ ህዳር 2011 (እ.አ.አ)፣ 28።

  3. ኒል ኤል. አንደርሰን፣ “ህፃናት፣” 28።

ይህን አስቡበት

ምድራዊ ቤተሰባችን ከሰማይ ቤተሰባችን ጋር በምን መንገድ ነው የሚመሳሰለው?

አትም