የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ሐምሌ 2016 (እ.አ.አ)
ለአባቶቻችን እምነት በእውነት መቆም
ጆን ሊንፎረድ እሱና ሚስቱ ማርያ፣ እናም ሶስቱ ወንድ ልጆቻቸው በግሬቭሊ እንግሊዝ የነበረውን ቤታቸውን ለቀው ቅዱሳንን ለመቀላቀል ወደ ታላቅዋ ሶልት ሌክ ከተማ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ማይሎችን ሲጓዙ 43 አመታቸው ነበር። ሚስኦን እያገለገለ የነበረውን፣ አራተኛ ወንድ ልጃቸውን ትተውት ሄዱ፣ ንብረቶቻቸውን ሸጡ፣ እንዲሁም ወደ ቶርንተን በመርከብ ለመጓዝ ሊቨርፑል ላይ ተሳፈሩ።
ወደ ኒው ዮርክ በባህር፣ እና ከዚያም በምድር ወደ አየዋ የተግጓዙበት ጉዞ ብዙ ድርጊት የነበረበት አልነበረም። ነገር ግን ችግሩ የተጀመረው፣ በቶረንተን መርከብ ተጉዘው የነበሩት ሊንፎርድ እና ሌሎች የኋላኛው ቀን ቅዱሳን በሐምሌ 15፣ 1856 (እ.አ.አ) እንደ ገደቢስ ከሆኑት ከጄምስ ጂ ዊለስ የእጅ ጋሪ ቡድኖች ከአየዋ ከተማ ወጥተው ሲሄዱ ነበር።
አስቸጋሪው የአየር ፀባይ እና ብርቱ ጉዞ ጆንንም ጨምሮ በብዙ ጓዶች ላይ ጉዳት አደረሱባቸው። ቀስ በቅስ በጣም ታመመና በእጅ ጋሪ እስኪሳብ ድረስ ደከመ። ጓዱ ዋዮሚንግ በደረሱበት ወቅት፣ ጤንነቱ በታላቅ ሁኔታ የከፋ ነበር። የጆን ሟች እድሜ ከማብቃቱ ልክ ከአንድ ሰአት በፊት፣ በጥቅምት 21 ላይ ከሶልት ሌክ ከተማ ከአደጋ አዳኝ ቡድን ደረሰ። ስዊትዋተር ወንዝ ዳርቻ አካባቢ በዛ ቀን በጠዋት ሞተ።
ጆን ምቾቱን በመለወጡና ቤተሰቡን ወደ ፂዮን ለመውሰድ ለትግሎች፣ ለእጦት፣ እንዲሁም ለመከራዎች እራሱን በማመቻቸቱ አዝኖ ነበርን?
ከመሞቱ በፊት “አይሆንም ማሪያ” በማለት ለሚስቱ ነገራት። “በመምጣታችን ደስተኛ ነኝ። ሶልት ሌክ ከተማ ለመድረስ በህይወት መቆየት አልችልም፣ ነገር ግን አንቺ እና ወንድ ልጆቹ ትደርሳላችሁ፣ እንዲሁም ወንዶች ልጆቻችን ማደግ ከቻሉና ቤተሰቦቻቸውን በፂዮን ውስጥ ማሳደግ ከቻሉ እኛ ላይ ስለተከሰቱት ነገሮች ሁሉ ምንም አልቆጭም።”1
ማሪያ እና ወንዶች ልጆችዋ ጉዞዋቸውን አጠናቀቁ። ከወጡ ከ30 አመት በኋላ ማርያ ስትሞት፣ እስዋ እና ጆን የእምነት፣ የአገልግሎት፣ የፍቅር እና የመስዋእትነት ውርስን ነው ትተው የሄዱት።
የኋለኛው ቀን ቅዱሳን መሆን መስራች መሆን ነው፣ ምክንያቱም የመስራች ትርጉም “ሌሎች እንዲከተሉ ቀድሞ ሄዶ የሚያዘጋጅ እና መንገዱን የሚከፍት” ማለት ነው።2 እንዲሁም መስራች መሆን ማለት ከመስዋእትነት ጋር መጣመር ማለት ነው። ምንም እንኳን የቤተክርስቲን አባላት ቤታቸውን ትተው ወደ ፅዮን እንዲጓዙ መጠየቃቸው ቢቀርም፣ አብዛኛውን ጊዜ አሮጌ ልምዳቸውን፣ አብሮ ለብዙ ጊዜ የቆየ ልምዳቸውን እንዲሁም ከፍተኛ ቦታ የሚሰጡዋቸውን ጓደኞች ወደ ኋላ መተው ይኖርባቸዋል። አንዳንዶች የቤተክርስቲያን አባልነታቸውን የሚቃወሙ የቤተሰባቸውን አባላት ወደ ኋላ ትተው በመሄድ በጣም የሚያም ውሳኔን ይወስናሉ። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን፣ ግን፣ እነዚያ ውዶቹ ሰዎች እንዲገባቸው እና እንዲቀበሉት በመፀለይ ወደ ፊት ይጓዛሉ።
የመስራቾች መንገድ ቀላል አይደለም፣ ነገር ግን በመስራቾች የመጨረሻ አርአያነትን — እንዲሁም እንድንከተለው መንገዱን በማሳየት ከፊታችን ቀድሞ የሄደውን የአዳኝ የመጨረሻ አርአያነትን እንከተላለን።
“ኑ፣ ተከተሉኝ”3 ብሎ ጋብዞናል።
“እኔ መንገድና እውነት ህይወትም ነኝ”4 ብሎ አወጀ።
“ወደ እኔ ኑ”5 ብሎ ተጣራ።
መንገዱ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። አንዳንዶች ንጹህነትን ታማኝነትን እና ለእግዚአብሔር ትእዛዛት መታዘዝን በሚያሳልቁ ሞኞች አስቀያሚ ንግግሮች እና መሳለቂያዎችን ለመቋቋም አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል። ነገር ግን አለም በመሰረታዊ መርህ ላይ መመካትን ሁልጊዜም ትሳልቃለች። ኖህ መርከብን እንዲገነባ መመሪያ ሲሰጠው ሞኝ የነበሩት ህዝቦች ዳመና የሌለውን ሰማይ ተመልክተው ዝናቡ እስከሚመጣ ድረስ ያሾፉና ያፌዙ ነበር።
ከረጅም ክፍለ ዘመናት በኋላ በአሜሪካ አህጉር ላይ፣ እሳት ዛራሄምላን እስኪያጠፋት ድረስ ሰዎች ተጠራጠሩ፣ ተጨቃጨቁ፣ እንዲሁም አልታዘዝም አሉ፣ ምድር ሞሮኒሃን ሸፈነች፣ እናም ውሃ ሞሮኒን ዋጠው። የፌዝ ሳቅ፣ መሳለቅ፣ ብልግና የተሞላበት ቀልድ፣ እና ሀጢያት መኖራቸውን አቆሙ። ሰላም ባለው ፀጥታ እና ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ ተተኩ። የእግዚአብሔር ትእግስት አበቃ፣ የእሱ የጊዜ ሰንጠረዥ ተሟላ።
በእንግሊዝ የነበረው የሀይማኖት ተቃውሞ፣ “እግዚአብሔር ወዳዘጋጀው ቦታ ያረገችው አስቸጋሪ ጉዙዋ፣”6 ለቤተሰቧ እና ለቤተክርስቲያን ስትል የፀናቻቸው ተከታታይ መከራዎች ቢኖርም ማሪያ ሊንፎርድ እምነቷን አጥታ አታውቅም ነበር።
እ.አ.አ በ1937 ለማሪያ ማስታወሻነት ከተደረገው የመቃብር ስርኣት ላይ ፣ ሽማግሌ ጅዎርጅ አልበርት ስሚዝ [1870–1951 (እ.አ.አ)] እንዲህ ሲል የእሷን ዘሮች ጠየቀ፥ “ለቅድመ አያቶቻችሁ እምነት በእውነት ትኖራላችሁን? … [እነሱ] ለእናንተ ለከፈሉት መስእዋትነት ሁሉ ብቁ ለመሆን ጣሩ።”7
በልቦቻችን ውስጥ፣ በቤቶቻችን ውስጥ፣ በመንደራችን ውስጥ እና በሀገሮቻችን ውስጥ ፅዮንን ለመገንባት በምንሻ ጊዜ፣ የተመለሰውን ወንጌል በረከቶች፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በሀጢያት ክፍያ አማካኝነት የመጣውን ተስፋ እና ቃልኪዳን እንድንደሰትበት ሁሉ ነገራቸውን የሰጡትን ሰዎች፣ ቆራጥ ብርታት እና ፅኑ እምነት እናስታውስ።
© 2016 በ በIntellectual Reserve Inc. መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት 6/16 (እ.አ.አ)። ትርጉም የተፈቀደበት 6/16 (እ.አ.አ)። First Presidency Message, July 2016. ትርጉምAmharic 12867 506