ልጆች
ቤተሰቦች ለዘላለም ናቸው
በኢየሱስ ክስቶስ የሃጢያት ክፍያ አማካኝነትና በክህነት ቁልፎች መመለስ ከቤተሰቦቻችን ጋር ለዘላለም መኖር እንችላለን። ሰለ ቤተሰባችሁ ምን ትወዳላችሁ? ቤተሰባችሁን ለማክበር ይህን የወረቀት ሰንሰለት ለመስራት እነዚህን ትዕዛዞች ተከተሉ።
-
አንድን ወረቀት ግማሽ በግማሽ ሁለት ጊዜ እጠፉ።
-
የታጠፉትን የወረቀት ጫፎች በእጆቹ የሚነካ አንድን ሰው ሳሉ።
-
የሳላቹትን ሰው ቁረጡት። እጆቹ የሚነኩትን የታጠፉ የወረቀት ጫፎች አትቁረጧቸው ።
-
ዘርጉት። ስለእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የምትወዱትን ነገር ፃፉ ወይም ሳሉ።
-
ትልቅ ቤተሰብ ካላችሁ ብዙ ሰንሰለቶችን በአንድ ላይ አያይዙ!