2016 (እ.አ.አ)
ዘላለማዊ ደስታን ማካፈል
ኦገስት 2016


ወጣቶች

ዘላለማዊ ደስታን ማካፈል

ከወንጌል በጣም መልካም ከሆኑ ነገሮች መካከል አንዱ የደህንነት ዕቅድ እውቀት ነው። ከቤተሰባችን ጋር ለዘላለም ለመሆን ግሩም እድል አለን። ያ እውቀት በዓለም የመገረም ስሜት ሲሰማን ተስፋ እንዲኖረን ይረዳናል። ፕሬዘደንት አይሪንግ እንዳስተማሩት፣ “የሚወደን የሰማይ አባታችን ልቦቻችንን ያውቃል። የእርሱ አላማ ደስታን ሊሰጠን ነው (2 ኔፊ 2፥25ተመልከቱ)። እናም ለዘላለም የሚቀጥለውን የቤተሰብ ትስስር ደስታን ለማስቻል የልጁን ስጦታ ሰጠ። … ይህም ወደ አለም የሚመጣ እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጅ የእራሱ ለማድረግ እንዲችል ተሰጠ እድል ነው።”

ያ በረከት የሚሰራው በአሁን ሰዓት ለምንኖረውና በሞት ላለፉት ሰዎች ነው--ነገር ግን ይህ የሚሆነው በራሳችን እርዳታ ብቻ ነው። በአሁን ሰዓት ቅድመ አያቶቻችን የቤተ-መቅደስ ሥነ-ስርዓቶች እነሱን በመወከል እንዲከናወንላቸው ስማቸውን እንድናዘጋጅ በመንፈስ ዓለም ውስጥ እየጠበቁን ነው ያሉት ። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ለእነሱ ስራን መስራት ከባድ ሊሆን ይችላል። በጣም ስራ ሊበዛብን ይችላል ወይም በተደጋጋሚ ቤተ-መቅደስ ለመሄድ በጣም እርቀን እንኖር ይሆና።

እንደ እድል ሆኖ ቅድመ አያቶቻችንን የምንረዳበት ሌላ መንገዶች አሉ እንደ የቤተሰብ ታሪክ ስራ መስራትን፣ ዝርዝር መፃፍን ወይም ወላጆቻችን ወደ ቤተ-መቅደስ ሲሄዱ ልጆች መጠበቅን የመሳሰሉ አሉ። በመርዳት ጌታን እናገለግላለን እንዲሁም በመጋረጃው ጀርባ ላሉት ሰዎች የዘለላለም ቤተሰብን ተስፋ እናመጣለን።

አትም