2016 (እ.አ.አ)
ቤተሰቦችን በአንድ ላይ መንከባከብ
ኦገስት 2016


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት መልእክት፣ ነሐሴ 2016 (እ.አ.አ)

ቤተሰቦችን በአንድ ላይ መንከባከብ

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ እሹ። ለአለም አዋጅን መረዳት እንዴት እምነታችሁን በእግዚአብሔር እንድታዳብሩ እናም በጉብኝት ትምህርት በኩል የምትመለከትዋቸውን ሰዎች እንዴት ይባርካቸዋል? ለተጨማሪ መረጃ ወደ reliefsociety.lds.org ሂዱ

እምነት፣ ቤተሰብ፣ እርዳታ

ፕሬዘደን ት ሩሴል ኤም. ኔልሰን፣ የአስራሁለቱ ሐዋርያት ምልዓተ ጉባኤ ፕሬዘደንት እንዲህ አሉ፣ “ባልና ሚስት እርስ በእርሳቸው እንዲፋቀሩና ልጆቻቸውንም ጨምሮ እንዲንከባከቡ ክቡር ሃላፊነት አለባቸው።”1 “ቤት የእግዚአብሔር የፍቅርና የአገልግሎት ቤተ-ሙከራ መሆን አለበት።”

“የሰማይ አባታችን ባሎችና ሚስቶች እርስ በራሳቸው ታማኝ እንዲሆኑና ልጆቻቸውን እንዲያከብሩና ከጌታ የወረሷቸው አድርገው እንዲመለከቷቸው ይፈልጋል።”2

በመጽሐፈ ሞርሞን ውስጥ ያቆብ ባሎች ለሚስቶቻቸው ያላቸው ፍቅር፣ ሚስቶች ለባሎቻቸው ያላቸው ፍቅር እና ሁለቱም ለልጆቻቸው ያላቸው ፍቅር ላማናውያን እና ኔፋውያን በአንድ ወቅት የበለጠ ፃድቅ ከነበሩበት ምክንያቶች አንዱ ነበር አለ (ያዕቆብ 3፥7 ተመልከቱ)።

ወደ ቤታችን ፍቅርና መስማማትን ለመጋበዝ በጣም መልካም ከሆኑ መንገዶች መካከል አንዱ ለቤተሰብ አባሎቻችን በደግነት መናገር ነው። በደግነት መናገር መንፈስ ቅዱስን ያመጣል። እህት ሊንዳ ኬ በርተን፣ አጠቃላይ የሴቶች መረዳጃ ፕሬዘደንት ይህን እንድናስብ ጠየቁ፤ “እርስ በእርስ ምን ያህል ጊዜ ነው ደግ የሆኑ ቃሎችን የምንናገረው?”3

ተጨማሪ ቅዱሳት መጻህፍት

ሮሜ 12፥10፤ ሞዛያ 4፥15፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥5

ህያው ታሪኮች

ሽማግሌ ዲ. ታድ ክርስቶፈርሰን የአስራ ሁለት ሐዋርያት ምልዓተ ጉባኤ እርሳቸውና ወንድማቸው የሚፋቀሩ የቤተሰብ ጥቅም ያሳደረባቸውን የልጅነት ልምዳቸውን አካፈሉ። እርሳቸውና ወንድማቸው ልጆች በነበሩበት ሰዓት፣ እናታቸው ቀኝ እጇን ለመጠቀም በጣም የሚያማትን የካንሰር ቀዶ ጥገና አደረገች። በወንድ ልጆች በተሞላ ቤተሰብ ውስጥ፣ ብዙ የሚተኮሱ ልብሶች ነበሩ ነገር ግን እናታቸው ስትተኩስ በተደጋጋሚ በማቆም ወደ መኝታ ክፍል በመሄድ ህመሙ እስኪቀንስ ታለቅስ ነበር።

የሽማግሌ ክርስቶፈርሰን አባት የተፈጠረውን ነገር ሲገነዘብ፣ ልብስ መተኮስን የሚያቀል መሳሪያ ለመግዛት በቂ ብር ለማጠራቀም በድብቅ ለአንድ ዓመት ለሚሆን ጊዜ ምሳ ሳይበላ ሄደ። ለሚስቱ ባለው ፍቅር በቤተሰብ ውስጥ ለወንድ ልጆቹ የመንከባከብ ምሳሌን አስቀመጠ። ስለዚህ ደግ ግንኙነት ሽማግሌ ክርስቶፈርሰን እንዲህ አሉ፣ “በዛን ጊዜ ስለአባቴ መስዋትነትና ለእናቴ ስላሳየው የፍቅር ተግባር አላወቅኩኝም ነበር፣ ነገር ግን አሁን ስለማውቅ፣ ለራሴ ‘ያም ወንድ ነው’ እላለው።”4

ማስታወሻዎች

  1. “ቤተሰብ፤ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” Liahona፣ ህዳር 2010፣129

  2. ሩሴል ኤም ኔልሰን፣ “Salvation and Exaltation፣” Liahona፣ ግንቦት 2008 እአአ፣ 8።

  3. ሊንዳ ኬ በርተን፣ “We’ll Ascend Together፣” Liahona፣ ግንቦት 2015 እአአ፣ 31።

  4. ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ “Let Us Be Men፣” Liahona, ህዳር 2006፣ 46።

ይህንአስቡበት

እርስ በእርስ መፋቀርና መንከባከብ እንዴት ነው መንፈስን ወደ ቤታችን የሚጋብዘው?

አትም