2016 (እ.አ.አ)
ቤተሰቦች ለዘላለም ናቸው
ኦገስት 2016


ልጆች

ቤተሰቦች ለዘላለም ናቸው

በኢየሱስ ክስቶስ የሃጢያት ክፍያ አማካኝነትና በክህነት ቁልፎች መመለስ ከቤተሰቦቻችን ጋር ለዘላለም መኖር እንችላለን። ሰለ ቤተሰባችሁ ምን ትወዳላችሁ? ቤተሰባችሁን ለማክበር ይህን የወረቀት ሰንሰለት ለመስራት እነዚህን ትዕዛዞች ተከተሉ።

  1. አንድን ወረቀት ግማሽ በግማሽ ሁለት ጊዜ እጠፉ።

  2. የታጠፉትን የወረቀት ጫፎች በእጆቹ የሚነካ አንድን ሰው ሳሉ።

  3. የሳላቹትን ሰው ቁረጡት። እጆቹ የሚነኩትን የታጠፉ የወረቀት ጫፎች አትቁረጧቸው ።

  4. ዘርጉት። ስለእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የምትወዱትን ነገር ፃፉ ወይም ሳሉ።

  5. ትልቅ ቤተሰብ ካላችሁ ብዙ ሰንሰለቶችን በአንድ ላይ አያይዙ!

አትም