2016 (እ.አ.አ)
የዘላለም ቤተሰብ ፍቅር ተስፋ
ኦገስት 2016


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ነሐሴ 2016 (እ.አ.አ)

የዘላለም ቤተሰብ ፍቅር ተስፋ

የሚወደን የሰማይ አባታችን ለልጆቹ ከሰጠው ስጦታዎች በሙሉ ታላቁ የዘላለም ሕይወት ነው (ት. እና ቃ. 14፥7 ተመልከቱ)። ስጦታው በእግዚአብሔር አብ እና በተወደደው ልጁ መገኛ ለዘላለም እንደ ቤተሰቦች መኖር ነው። በከፍተኛው የእግዚአብሔር የክብር ደረጃ፣ በሰለስቲያል ውስጥ፣ ብቻ ነው የቤተሰብ ሕይወት የፍቅር ግንኙነት የሚቀጥለው።

ሁላችንም በሚፋቀሩ ቤተሰቦች ውስጥ በደስታ ለመኖር ተስፋ እናደርጋለን። ለአንዳንዶቻችን ያልተለማመድነው ስሜት ነው--እንደሚቻል የምናውቀው ነገር ግን ያልተገነዘብነው ስሜት ነው። በሌሎች ሰዎች ሕይወት ውስጥ ተመልክተነው ሊሆን ይችላል። ለሌሎቻችን ሞት ከልጅ፣ ከእናት፣ ከአባት፣ ከወንድም፣ ከእህት ወይም ከሚወዱና ከሚወደዱ አያቶች ሲለየን የቤተሰብ ፍቅር የበለጠ እውንና የተለየ መስሎ ታይቶናል።

ሁላችንም በጣም የወደድነውንና አሁን እንደገና ለማቀፍ የምንጓጓለትን የዛን የቤተሰብ አባል የሞቀ ፍቅር የሆነ ቀን በድጋሜ ሊሰማን እንደሚችል ተስፋ ተሰምቶናል ።

የሚወደን የሰማይ አባታችን ልቦቻችንን ያውቀዋል። የእሱ አላማ ደስታን ሊሰጠን ነው (2 ኔፊ 2፥25 ተመልከቱ)። እናም ለዘላለም የሚቀጥለውን የቤተሰብ ትስስር ደስታን ለማስቻል የልጁን ስጦታ ሰጠ። አዳኙ የሞትን እስራት ስለፈታ ከሞት እንነሳለን። ለሃጢያቶቻችን መስዋዕት ስለከፈለልን እንዲመልስ ወደ ጆሴፍ በእምነታችንና በንስሃ እንዲመልስ ወደ ጆሴፍ ቤተሰቦች በፍቅር ለዘላለም በሚታሰሩበት ለሰለስቲያል የክብር ደረጃ ብቁ መሆን እንችላለን።

እንዲሁም ኤሊያስን የክህነትን ቁልፎች እንዲመልስ ወደ ጆሴፍ ስሚዝ ላከው (ት. እና ቃ. 110 ተመልከቱ)። ከእነዚያ ቁልፎች ጋር የዕትመት ኃይል እንዲሁም የእግዚአብሔርን ታላቅ ስጦታ እንዲመልስ ወደ ጆሴፍ ማለትም በአንድ ላይ በታሰሩ ቤተሰቦች ውስጥ የዘላለም ሕይወትን ለልጆቹ መስጠት እንዲመልስ ወደ ጆሴፍ አብሮ መጣ።

ማንኛውም ወደ ምድር የመጣ የእግዚአብሔር ልጅ የሚገባው ስጦታ ነው ። አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት የመንፈስ ልጆቹ በመንፈስ አለም ስጦታውን ተቃወሙ። በቂ እምነት ከማጣታቸው የተነሳና በአመፅ የሰማይ አባትን የዘላለም ቤተሰቦች ደስታን ስጦታ ፈፅመው ላለማወቅ መረጡ።

በቅድመ ምድራዊ የመንፈስ አለም ውስጥ የነበረውን ወሳኝ ፈተና ላለፍነውና የሚሞት ሰውነትን ለመቀበል ብቁ ለሆንነው፣ የዘላለም ሕይወት ታላቁ ምርጫ አሁንም የእኛ ነው ። የተመለሰውን ወንጌል እንድናገኝ ከተባረክን፣ ለዘላለም ሕይወት ብቁ የሚያደርጉን ቃል-ኪዳኖች ከእግዚአብሔር ጋር መግባትና መጠበቅ እንችላለን። በእዛ አማኝነት ውስጥ እስከመጨረሻው ስንፀና፣በቤተሰብ ውስጥ ለዘላለም በሰለስቲያል የክብር ደረጃ ውስጥ ለመኖር ወደ ዘላለማዊ ሕይወት ወደሚያመራው መንገድ ላይ እዳለን መንፈስ ቅዱስ ተስፋችንንና መተማመናችን ያረጋግጥልናል።

ለተወሰኑት ያ ዘላለማዊ ደስታ የጠፋ ወይም እየለቀቀ ያለ ተስፋ ሊመስል ይችላል። ወላጆች፣ ልጆች፣ ወንድሞችና እህቶች ለዘላለማዊ ሕይወት ብቁ ሊያደርጋቸው የማይችል ውሳኔዎችን አድርገው ሊሆን ይችላል። በኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ አማካኝነት ብቁ ለመሆናችሁ ግራ ልትጋቡ ትችሉ ይሆናል።

የእግዚአብሔር ነቢይ ሰላም የሚሰጠኝን ምክር አንዴ ለገሰኝ። የሌሎች ምርጫዎች ቤተሰባችንን በአንድ ላይ ለዘላለም እንዳይሆኑ ሊያግ ይችላል በማለት ተጨንቄ ነበር። አንዲህ አለ፣ “ስለተሳሳተ ችግር እየተጨነቅክ ነው። ለሰለስቲያል የክብር ደረጃ ብቁ ሆነክ ኑር፣ እናም የቤተሰብ ዝግጅቶቹ ከምታስበው የበለጠ ድንቅ ይሆናሉ።”

የግል ልምዳቸው ወይም ጋብቻቸውና ልጆቻቸው ወይም የነዚህ ነገሮች አለመኖር ተስፋቸው ላይ ጥላ ለጣለባቸው ሁሉ የሰማይ አባት እንደሚያውቅና እንደ መንፈስ ልጆቹ እንደሚወዳችሁ ምስክርነቴን እሰጣለው። ከዚህ ሕይወት በፊት ከእርሱና ከተወደደው ልጁ ጋር ስትኖሩ፣ በልቦቻችሁ ውስጥ የዘላለም ሕይወት ተስፋን አኖሩ። የኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ ኃይል እየሰራና መንፈስ ቅዱስ እየመራ አባታችሁና የተወደደው ልጁ እንድትቀበሉት በጣም የሚፈልጉትን የቤተሰብ ፍቅር አሁንና ወደፊት በሚመጣው ዓለም ውስጥ ሊሰማችሁ ይችላል።

ለሰለስቲያል የክብር ደረጃ ብቁ ሆናችሁ ስትኖሩ፣ “የቤተሰብ ዝግጅቶቹ ከምታስቡት የበለጠ ድንቅ ይሆናሉ” የሚሉት የነቢይነት ቃል-ኪዳን የእናንተ እንደሚሆን እምሰክራለሁ ።

የዚህ መልእክት ትምህርት

የምታስተምራቸውን ሰዎች ስለዘላለማዊ ቤተሰቦች ተስፋ አመስጋኝ ስለሆንክበት ጊዜ በመናገር መጀመርን አስብ። ስለዘላለማዊ ቤተሰቦች የአመስጋኝነት ስሜት ስለተሰማቸውን ወቅት እንዲያሰላስሉ ጋብዛቸው። ማካፈል ከፈለጉ ጠይቃቸው። ከዛ “የቤተሰብ ዝግጅቶቹ ከምታስቡት ከዛ “የቤተሰብ ዝግጅቶቹ ከምታስቡት የበለጠ ድንቅ” የሚለው የነቢይ ቃል-ኪዳን የእነሱ እንዲሆን፣ ለመሻሻል እና ለሰለስቲያል የክብር ደረጃ የበለጠ ብቁ ለመሆን የሚኖሩበትን መንገዶች እንዲያስቡ ጋብዛቸው።

አትም