ወጣቶች
እሳት እና የታዛዥነት ትምህርት
አንድ ጊዜ ፕሬዝዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን የታዛዥነት ጥቅም ምን እንደሆነ አንድ ወቅት እንዴት እንዴት እንድተተማሩ። የስምንት አመት ልጅ በነበሩ ጊዜ የቤተሰባቸው በተራራው ላይ የሚገኘውን ጎጃቸውን ጎበኙ። እሱ እና ጓደኛው ለማረፊያ ሳራማ የሆነውን ቦታ ለማጽዳት ፈለጉ። ሳሩን በእጃቸው ለማስወገድ በሚችሉት አቅም ሞከሩ፣ ነጩ፣ ጎተቱ ነገር ግን ያገኙት በመዳፍ የሚሞላ አረም ብቻ ነበር። ፕሬዝዳንት ሞንሰን እንዲህ ሲሉ አብራሩ፤ “በዛ በስምንት አመት ጭንቅላቴ ውስጥ የመጣው ሀሳብ ትክክለኛ መፍትሔ ነው ብዬ አሰብኩ። ለዳኒ እንዲህ አልኩት፤‘ የሚያስፈልገን ይህንን አረም በእሳት ማያያዝ ነው። የአረሙን ክብ ያህሉን ብቻ እናቃጥል!’”
ክብሪት መጠቀም እንደማይችሉ ቢያውቁም ወደ ጎጆ ቤቱ ክብሪት ለማምጣጥ ሮጠው ሄዱ፣ ከዛም እርሳቸው እና ዳኒ በሳር የተሸፈነውን ቦታ ትንሽ ክፍል ብቻ እሳት አያያዙት። በራሱ ይጠፋል ብለው ጠብቀው ነበር ነገር ግን በተቃራኒው ወደ ትልቅ እና አደገኛ ወደ ሚሆን እሳት ተቀየረ። እርሳቸው እና ዳኒ እርዳታ ለማግኘት ሮጡ ከዛም ወዲያው ትልልቅ ሰዎች እሳቱ ወደ ዛፎቹ ሳይወጣ በፊት ለማጥፋት ደረሱ።
ፕሬዝዳንት ሞንሰን ቀጠሉ፣ “እኔ እና ዳኒ በዛ ወቅት የተለያዩ ከባድ ነገር ግን ጠቃሚ ትምህርቶችን ተማርን–ከዛ ውስጥም ትንሽ ያልሆነውን የመታዘዝን ጥቅምን ተማርን” (“ታዛዥነት በረከትን ያመጣል” Liahona፣ 2013 ግንቦት 2013 (እ.አ.አ) 89–90 ተመልከቱ።)
ልክ እንደ ፕሬዝዳንት ሞንሰን ከባድ በሆነ መንገድ ስለ ታዛዥነት ትምህርት የተማራችሁበት መንገድ አለ? ለወደፈት እራሳችሁን በታዛዥነት ደና ለማድረግ ምን አይነት ግቦችን ልታስቀምጡ ትችላላችሁ?