የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ጥቅምት 2016 (እ.አ.አ)
የታዛዥነት በረከቶች
ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንዲ ሲሉ አስተምረዋል “በዚህ ምድር ላይ የምንማረው ትልቅ ትምህርት እግዚአብሔር ሲናገር እና እኛ ስንታዘዝ ሁልጊዜም ትክክል እንሆናለን።”1
እንዲሁም እንባረካለን። በቅርቡ በተካሄደው አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ፐሬዘደንት ሞንሰን እንዳሉት፥ “ትዕዛዛቶችን ስንጠብቅ ህይወታችን ይበልጥ ደስተኛ፣ አርኪ እና ያን ያህል ያልተወሳሰበ ይሆናል። ፈተናዎቻችንን እና ችግሮቻችንን ለመሸከም ይቀላል እንዲሁም እግዚአብሔር ቃል የገባልንን በረከቶች እንቀበላለን።”2
በሚከተለው የፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንደ ቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንትነት ካስተማሩት ምንባብ፣ ለትዕዛዛቶች መገዛት ወደ ደስታ እና ሰላም የሚመራን እርግጠኛ መመሪያ እንደ ሆነ ያሳስቡናል።
ለጉዞው መመሪያዎች
“የእግዚአብሔር ትዕዛዛቶች እቅዳችንን እንዲያከሽፉ ወይም ለደስታችን እንቅፋት እንዲሆኑ አይደለም የተሰጡት። እውነታው የዚህ ተቃራኒ ነው። ታላቅ ደስታን ለማግኘት እንዴት መኖር እንዳለብን እኛን የፈጠረን እና የሚወደን እርሱ ፍፁም በሆነ መልኩ ያውቃል እነሱን የምንከተላቸው ከሆነ በዚህ ክህደት ባለበት አለማዊ ጉዟችን በደህንነት እንድናልፍ የሚያግዙን መመሪያዎችን አዘጋጅቶልናል። በደንብ የምናውቀውን ‘ትዕዛዛትን ጠብቁ!’ በዚህ ውስጥ ደህንነት አለ፤ በዚህ ውስጥ ሰላም አለ’ የሚለውን መዝሙር እናስታውሳለን።” [“ትዕዛዛትን ጠብቁ” መዝሙር ቁጥር 303 ተመልከቱ]።”3
ጥንካሬ እና እውቀት
“ታዛዥነት የነቢያት ልዩ መለያ ነው፤ በዘመናት ሙሉ ጥንካሬን እና እውቀት ሰቷቸወዋል። እኛም ለዚህ ጥንካሬና እውቀት ምንጭ መብት እንዳለን መረዳታችን አስፈላጊ ነው። ይህም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ስናከብር እያንዳንዳችን ልናገኘው እንድንችል የተዘጋጀ ነው። …
“የጌታን ትዕዛዛት በፍቃደኝነት የምንታዘዝ ከሆነ የዚህን የተለዋዋጭ እና የተወሳሰበ አለም ፈተናዎችን ለመጋፈጥ ዛሬ የምንሻው እውቀት፣ የምንጓጓላቸው መልሶች እና የምንፈልገው ጥንካሬ የራሳችን ሊሆኑ ይችላሉ።”4
መታዘዝን ምረጡ
“የአሁኑ ጊዜያችን ትርጓሜ ነገሮች ትክክል ባይሆኑም እዳሉ መቀበል ነው። ብዙ ወጣቶች መሆንን የሚመኟቸው— የመጽሔቶች እና ቴሌቪዥን ሾዎች የፊልም መሪ ተዋናይ፣ የአትሌቲክስ ጀግኖችን ይገልጻሉ — የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ችላ እንድንል በማድረጉ ሀጢያታዊ ስርአቶችን የማንፀባረቅ ክፉ ተፅእኖ የሌላቸው ይመስላሉ። ይህን አትመኑ! የማወቂያ ጊዜ አለ—እንዲሁም መዝገቡ እኩል የሚደረግበትም ጊዜ ጭምር። እያንዳንዷ ሲንደሬላ በዚህ አለም ባይሆንም በሚቀጥለው ህይወት የራሷ የሆነ እኩለ ለሊት አላት። የፍርድ ቀን ለሁሉም ይመጣል። …መታዘዝን እንድትመርጡ እለምናችኋለሁ።”5
ሀሴት እና ሰላም
“አንዳንዴ በአለም ውስጥ ያሉት ከናንተ በላይ እየተደሰቱ ያሉ ሊመስላችሁ ይችላል። አንዳንዶቻችሁ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ባሉት የተግባር መመሪያዎች የተገደባችሁ ይመስላችኋል። ነገር ግን፣ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ለእናንተ አውጅላችኋለሁ አዳኙን ስንከተል እና ትዕዛዛቱን ስንጠብቅ ወደ ህይወታችን ብዙ ሀሴትን ወይንም ብዙ ሰላምን ወደ ነፍሳችን ማምጣት ከሚችለው መንፈስ በላይ ምንም የለም።”6
በታማኝነት ተጓዙ
“ቃል የተገቡልን በረከቶች ከመጠን በላይ እንደሆኑ እመሰክርላችኋለሁ። ምንም እንኳ የአውሎንፋስ ደመና ቢሰበሰብ፣ ዝናብ በላያችን ላይ ቢወርድም በታማኝነት እና ትእዛዛትን በመጠበቅ ስንጓዝ ስለወንጌሉ ያለን እውቀት እና ለሰማይ አባታችን እና ለአዳኛችን ያለን ፍቅር ይደግፈናል እናም ሀሴትን ወደ ልባችን ያመጣል። በዚህ አለም ውስጥ እኛን የሚያሸንፈን ነገር ምንም አይኖርም።”7
አዳኙን ተከተሉት
“ሀዘንን የሚያውቅ የህማም ሰው ይህ ማነው? ይሔ የሰራዊት ጌታ የክብር ንጉስ ማነው? እርሱም መምህራችን ነው። አዳኛችን ነው። እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። የደህንነታችን ጸሀፊም ነው። ‘ተከተሉኝ’ ብሎ ይጠራል። ‘ሂዱና እንዲሁ አድርጉ’ ብሎ ያስተምራል። ‘ትእዛዛቴን ጠብቁ’ ብሎም ይለምናል።
“እንከተለው። የእርሱን ምሳሌንም እንከተል። ቃላቱንም እናክብር። ይህንም በማድረግ ለእርሱ መለኮታዊ ስጦታ የሆነውን ምስጋና እንሰጠዋለን።”8
© 2016 በ Intellectual Reserve Inc. መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/16 (እ.አ.አ)። ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/16 (እ.አ.አ)። First Presidency Message, October 2016 (እ.አ.አ) ትርጉም Amharic. 12870 506