የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት መልእክት፣ ጥቅምት 2016 እ.ኤ.አ
ቤተሰብ በእግዚአብሔር የተሾመ ነው
በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ መነሳሳትን እሹ። “ቤተሰብ፥ ለአለም አዋጅን” መረዳት እንዴት እምነታችሁን በእግዚአብሔር እንድታዳብሩ እናም በጉብኝት ትምህርት በኩል የምትመለከቷቸውን ሰዎች እንዴት ይባርካቸዋል? ለተጨማሪ መረጃ፣ ወደ reliefsociety.lds.org ሂዱ።
“በህፃናት መዝሙር ላይ ያለው ቃል ‘ቤተሰብ ከእግዚአብሔር ነው’… ንፁህ ትምህርትን ያስታውሰናል” በማለት የአጠቃላይ የሴቶች መረዳጃ አመራር ውስጥ አንደኛ አማካሪዋ ካሮል ኤም ስቴፈንስ ተናገረች። “ቤተሰብ ከእግዚአብሔር መሆኑን ብቻ ሳይሆን የምንማረው ነገር ግን እያንዳንዳችን የእግዚአብሔር ቤተሰብ አካል እንደሆንን ነው።
“… የአባታችን እቅድ ለልጆቹ የፍቅር እቅድ ነው። እቅዱ ልጆቹን አንድ ማድረግ ቤተሰቡን ከእርሱ ጋር ማድረግ ነው።”
ሽማግሌ ኤል. ቶም ፔሪ (1922-2015) የአስራሁለቱ ሐዋሪያት ጉባኤ አባል እንዲህ አሉ፤ “እኛ ጠንካራ ባህላዊ ቤተሰብ ለጠንካራ ማሀበረሰብ፣ ለፀና ኢኮኖሚ እና ለጠንካራ ባህል መሰረታዊ ክፍል መሆኑን ብቻ ሳይሆን የምናምው ነገር ግን ለዘላማዊነት እና ለእግዚአብሔር መንግስት እና አስተዳደር መሰረታዊ አካል ነው።
“የመንግስተ ሰማያት መሰረት እና መንግስት የሚገነባው በቤተሰብ ዙሪያ ላይ እንደሆነ እናምናለን።”
ሁሉም ሰው የትዳር ሁኔታቸው ወይም የልጆቻቸው ቁጥር ብዛት ምንም ቢሆንም በቤተሰብ አዋጅ ውስጥ የተገለፀውን የጌታን እቅድ ተከላካዮች መሆን ይችላሉ። የጌታ እቅድ ከሆነ የኛም እቅድ መሆን አለበት።3
ተጨማሪ ቅዱስ መጻህፍቶች
የቤተሰብ ትምህርት
የቤተሰብ መንፈሳዊ ትምህርት በፍጥረት ላይ፣ በውድቀት እና በክርስቶስ የሀጥያት ክፍያ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ የቀድሞው አጠቃላይ የሴቶች መረዳጃ ፕሬዝዳንት የነበረቸው እህት ጁሊያ ቢ. ቤክ ስትል አስተምራለች፥
“የምድር መፈጠር ቤተሰብ መኖር የሚችልበት ቦታን አዘጋጀ። ለቤተሰብ እኩል አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ወንድን እና ሴትን እግዚአብሔር ፈጠረ። አዳም እና ሔዋን እንዲታተሙና ዘላለማዊ ቤተሰብን እንዲመሰርቱ የእግዚአብሔር እቅድ ነበር።
“ውድቀቱ ወንድ እና ሴት ልጆች እንዲኖራቸው አስችሏል
“የኢየሱስ ክርስቶስ የሀጥያት ክፍያ ቤተሰብ አንድ ላይ ለዘላለም እንዲታተሙ ያስችላል። ቤተሰብ ዘላለማዊ እድገት እና ፍጽምና የኢየሱስ ያደርጋል። የደስታ እቅድ እንዲሁም የደህንነት እቅድ ተብሎ የሚጠራው ለቤተሰብ የተሰራ እቅድ ነው።
“ይህ ነበር የክርስቶስ ትምህርት። …ያለቤተሰብ እቅድ የለም፣ ለእዚህ ህይወትም ምክንያት አይኖርም።”4
© 2016 በ Intellectual Reserve Inc. መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/16 (እ.አ.አ)። ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/16 (እ.አ.አ)። Visiting Teaching Message, October 2016 (እ.አ.አ) ትርጉም Amharic. 12870 506