2017 (እ.አ.አ)
እኔም ወስኜአለሁ
መጋቢት 2017 (እ.አ.አ)


ወጣቶች

እኔም ወስኜአለሁ

ደራሲዋ በዩታ፣ ዩኤስኤ ነው የምትኖረው።

አንድ ቀን በወጣት ሴቶች ክፍል ውስጥ ስለወሲባዊ ንጹነት ዋጋ ያለው ትምህርት ተማርኩኝ—ይህም ርዕስ ብዙዎቹ ወጣቶች በተቀመጡበት ትርመስመስ እንዲሉ አደረጋቸው። በዚያ ቀን የተማርኩትን ሁሉንም ነገሮች አላስታውስም፣ ነገር ግን መሪዬ ሁልጊዜም በወስባዊ ንጹህ ለመሆነ ስለነበራት ስለግል መሰረታዊ መርሆዋ የተናገረችውን አስታውሳለሁ። ቃላቷ ከእኔ ጋር ቆዩ፣ እና ከዚያም ይህን እንደ ግል ዋጋዬ አንዱ አድርጌ ለመከተል የህሊና ውሳኔ አደረግኩኝ።

አንድ ቀን በአውቶቡስ ከስፖርት ድርጊት ወደቤት ስመለስ፣ አንድ ሰው በአውቶቡሱ ላይ እውነት ወይም ድፍረት የሚል ጨዋታ ጀመረ። በስልቹነት፣ አንዳንድ ሌሎች ልጆች እና እኔ ወደ ጨዋታው ተቀላቀልን። የእኔ ተራ ሲደርስ፣ ትክክል እንዳልሆነ የማውቀውን ነገር እንዳደርግ ገፋፉኝ። ይህ ውሳኔ ለእኔ ከባድ ይሆን ነበር፣ ነገር ግን የወጣት ሴቶች መሪዬ ቃላት በአዕምሮዬ መጣልኝ፣ እና ምርጫው ቀላል ነበር። ወዲያውም እምቢ አልኩኝ። በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ምን እንደማደርግ አስቀድሜ ወስኜ ነበርና።

ወደ ቤተክርስቲያን ስንሄድ እና በዚያ ለምንማረው ነገሮች ቦታ ስንሰጥ፣ በታላቅ መንፈሳዊ ጥንካሬ እና ከአለም ፈተናዎች በመጠበቅ እንደምንባረክ አውቃለሁ።