የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ማስተማሪያ መልእክት፣ መጋቢት 2016 (እ.አ.አ)
ችሎታ የሚሰጠው የኢየሱስ ክርስቶስ እና የኃጢያት ክፍያው ሀይል
በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ መነሳሳትን እሹ። የሴቶች መረዳጃ ማህበር እቅድን ማወቅ እንዴት የእግዚአብሔር ሴት ልጆችን ለዘለአለም ህይወት በረከቶች ያዘጋጃል?
“ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ” (ፊልጵስዮስ 4፥13)። የቀዳሚ አመራር ሁለተኛ አማካሪ ፕሬዘደንት ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ እንዳሉት፣ “ደካማነት ሁላችንም ቢኖረንም፣ እነኚህን ለማሸነፍ እንችላለን።” “በእርግጥ፣ እራሳችንን ትሁት ካደረግን እና እምነት ካለን፣ ደካማ ነገሮቻችን ጠንካራ የሚሆኑልን በእግዚአብሔር ፀጋ ነው።”1
አዳኝ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ እንዳለው፣ “በፊታችሁ እሄዳለሁ። በቀኛችሁ እና በግራችሁ እሆናለሁ፣ እናም መንፈሴም በልቦቻችሁ ውስጥ ይገኛል፣ እናም መላእክቶቼም እንዲያዝሏችሁ ይከብቧችኋል” (ት. እና ቃ. 84፥88)።
የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር እንዳሉት፣ “ኔፊ ችሎታ የሚሰጠውን የአዳኝ ሀይል የሚያውቅ፣ የተረዳ፣ እና በዚህም የተመካ አንድ ምሳሌ ነው።” “የኔፊ ወንድሞች በገምድ አሰሩት እና የእርሱን መጥፋት አለሙ። እባካችሁ የኔፊን ጸሎት ምልክት አድርጉ፥ ‘አቤቱ ጌታ፣ በአንተ ባለኝ እምነት መሰረት፣ ከወንድሞቼ እጅ አታድነኝምን፤ አዎን፣ የታሰርኩበትንም እስር እበጣጥሰው ዘንድ ጥንካሬን ስጠኝ ’ (1 ኔፊ 7፥17፤ ትኩረት ተጨምሮበት)።
“… ኔፊ ሁኔታው እንዲቀየር አልነበረም የጸለየው። ግን፣ ጸሎቱ ሁኔታውን ለመቀየር ጥንካሬ እንዲኖረው ነው። እናም እንደዚህ የጸለየው ችሎታ የሚሰጠውን የኃጢያት ክፍያ ሀይልን ስለሚያውቅ፣ ስለሚረዳ፣ እና በዚህም ልምምድ ስለነበረው ነው ብዬ አምናለሁ።
“ኔፊ የታሰረበት ገመድ በአስማት ከእጆቹ እና ከእጆቹ አንጓዎች ወድቀዋል ብዬ አላስብም። ግን፣ በተፈጥሮ ካለው ችሎታ በላይ በመንፈስ ጥንካሬ እና በግል ጥንካሬ እንደተባረከ፣ ከዚያም እርሱ ‘በጌታ ጥንካሬ’ (ሞዛያ 9፥17) ገመዱን ጠመዘዘ እና ሳበ፣ እና በመጨረሻም ገመዱን ለመስበር ቻለ።”2
ተጨማሪ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶች እና መረጃ
© 2017 Intellectual Reserve, Inc. መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/16 (እ.አ.አ)። ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/16 (እ.አ.አ)። ትርጉም። Visiting Teaching Message, March 2017 ትርጉም። Amharic 97923 506