2017 (እ.አ.አ)
በፅድቅ መሳሪያ መታጠቅ
መጋቢት 2017 (እ.አ.አ)


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ መጋቢት 2017 (እ.አ.አ)

በፅድቅ መሳሪያመታጠቅ

በምድር የእግዚአብሔር ነቢይ የሆኑት፣ ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንዳወጁት፣ “ዛሬ፣ በአይናችን ፊት ተሰልፈው ያሉትን ታላቅ የኃጢያት፣ መጥፎ ምግባር፣ እና ክፉት ለመቃወም ተዘጋጅተናል”1

ፕሬዘደንት ሞንሰን እነዚህን ቃላት የተናገሩት ከ50 አመት በፊት መሆኑን በማወቃችሁ ትደነቃላችሁን? በዚያ ጊዜ ታይቶ የማይታወቅ ክፉነትን ለመቃወም ተዘጋጅተን ቢሆን ኖሮ፣ ዛሬ ምን ያህል ተጨማሪ ክፋት እያስፈራራን ይሆናልን? ለመልካም ምክንያት፣ ጌታ በእኛ ዘመን “እነሆ፣ ጠላትም ተባብሯል” ብሎ አውጇል (ት. እና ቃ. 38፥12)።

“የተመዘገብንለት”2 ጦርነት በምድር ላይ ከመወለዳችን በፊት የተጀመረ ነው። ይህም የተጀመረው ምድር ከመፈጠሩ በፊት ነበር። ይህም የተጀመረው ሰይጣን ባመጸበት እና “የሰው ነጻ ምርጫን ለማጥፋት በፈለገበት” (ሙሴ 4፥3) በቅድመ ህይወት ግዛት ከብዙ ሺህ አመታት በፊት ነበር ።

ሰይጣን በጦርነቱ ተሸነፈ እናም አሁንም ጦርነቱን ወደሚቀጥልበት “ወደ ምድር ተጣለ” (ራዕይ 12፥9)። በዚህ በምድር ላይም በውሸት፣ በማታለል፣ እና በፈተና “ከእግዚአብሔር ቅዱሳን ጋርም ተዋጋ፣ እናም በዙሪያቸውም ከበባቸው” (ት. እና ቃ. 76፥29)።

ነቢያት እና ሐዋሪያትን ይዋጋል። የንፅህና ህግ እና የጋብቻ ቅድስናን ይዋጋል። ቤተሰብ እና ቤተመቅደስን ይዋጋል። መልካም፣ ቅዱስ፣ እና የተቀደሰ የሆነውን ይዋጋል።

እንደዚህ አይነት ጠላትን እንዴት ነው የምንዋጋው? አለማችንን ያጥለቀለቀ የሚመስለውን ክፉ እንዴት ነው የምንታገለው? ጥሩራችን ምንድን ነው? ተባባሪዎቻችን ማን ናቸው?

የበጉ ሀይል

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዳስተማረው፣ ሰይጣን በእኛ ላይ ሀይል የሚኖረው እስከምንፈቅድለት ያህል ብቻ ነው።3

ቀናችንን በማየት፣ ኔፊ “በበጉ ቤተክርስቲያን ቅዱሳንና በምድር ገፅ ላይ ሁሉ በተበተኑት የጌታ የቃልኪዳን ህዝቦች ላይ የእግዚአብሔር በግ ኃይል ሲወርድ ተመለከትኩ፤ እነርሱም ፅድቅንና የእግዚአብሔርን ኃይል በታላቅ ክብር የታጠቁ ነበሩ።” (1 ኔፊ 14፥14፤ ትኩረት ተጨምሯል)።

ራሳችንን በጻድቅነት እና በሀይል እንዴት እናስታጥቃለን? የሰንበት ቀንን እንቀድሳለን እናም ክህነትን እናከብራለን። ቃል ኪዳኖችን እንገባለን እናም እናከብራለን፣ በቤተሰብ ታሪካችንም እንሰራለን፣ እናም ወደ ቤተመቅደስ እንሄዳለን። ንስሀ ለመግባት “ለኃጢአታችን ይቅርታን እናገኝ ዘንድና ልባችን ንፁህ ይሆን ዘንድ የክርስቶስን የደም ክፍያ በእኛ ላይ” እንዲደረግ ጌታን ለመለመን ሁልጊዜም እንጥራለን (ሞዛያ 4፥2)። እንጸልያለን እናም እናገለግላለን እናም እንመሰክራለን እናም በኢየሱስ ክርስቶስ እምነትን እንለማመዳለን።

ራሳችንንም “ዘወትር የህይወትን ቃል [በአዕምሮዎቻችን] ውስጥ [በማከማቸት]” በጻድቅነት እና በሀይል ለማስታጠቅ እንችላለን (ት. እና ቃ. 84፥85)። እነዚህን ቃላት የምናከማቸው ራሳችንን በቅዱስ መጻህፍት ውስጥ እና፣ የእርሱን ፍላጎት፣ አስተሳሰብ፣ እና ድምጽ ( ት. እና ቃ. 68፥4 ተመልከቱ) በሚቀጥለው ወር አጠቃላይ ጉባኤ በሚያካፍሉን፣ በጌታ በተመረጡት አገልጋዮች ቃላት ውስጥ በማጥለቅ ነው።

ከክፉ ጋር ባለን ትግል፣ በመጋረጃው ሁለት ጎኖች በኩል እርዳታ እንዳለን ማስታወስ አለብን። ተባባሪ ጓደኞቻችን በተጨማሪም የዘለአለም አባት እግዚአብሔር፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እና መንፈስ ቅዱስ ናቸው።

ተባባሪ ጓደኞቻችን ደግሞም የማይታዩ የሰማይ ሰራዊቶችን ይጨምራሉ። ኤልያስ የክፉ የጦር ሰልፍን በሚጋፈጡበት ጊዜ ለወጣቱ ሰው እንዲህ አለው፣ “ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ” ( ነገሥት ካልዕ 6፥15–16 ተመልከቱ)።

መፍራት አያስፈልገንም። እግዚአብሔር ቅዱሳኑን ይወዳል። መቼም አይተወንም።

እግዚአብሔር፣ በጸሎት መልስ፣ ከክፉ እንዲያድነኝ የለመንኩትን አሟልቷል። በእግዚአብሔር አብ፣ በአለም አዳኝ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ፣ የሚያጋጥሙንን ማንኛውንም የክፉ ሀይሎች ለመቋቋም ከሚበቃ ያህል ሀይል እንደሚሰጠን ለመረጋገጥ እንደምንችል እመሰክራለሁ።

በመጨረሻ ድላችን ልበ ሙሉ ለመሆን እንድንችል በጻድቅነት ሁልጊዜም እንታጠቅ።

ማስታወሻዎች

  1. ቶማስ ኤስ. ሚንሰን፣ “Correlation Brings Blessings፣” Relief Society Magazine፣ ሚያዝያ 1967 (እ.አ.አ)፣ 247።

  2. “We Are All Enlisted፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 250።

  3. Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith (2007 [እ.አ.አ])፣ 214 ተመልከቱ።

አትም