2017 (እ.አ.አ)
ሌሎችን በእምነት ማገልገል
ሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ)


ወጣቶች

ሌሎችን በእምነት ማገልገል

ፕሬዘዳንት ኡክዶርፍ በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት “ከተግባር ጋር መሆን” እንዳለበት ነግረውናል። እምነታችን “በቋሚ ተግባር ሲደገፍ፣” ያ “ነብስን በሰላም እና ፍቅር ይሞላል” ብለው ገልጸዋል። በዚህ የበረከት ቃልኪዳን፣ እኛ ለውጥ ማምጣት እንችላለን ፣ እና በእምነት የተሞላ አገልግሎትን ስንሰጥ ይህንን በህይወታችን ማየት እንችላለን ሁሌ ጠዋት ሌሎችን ለማገልገል እንዲረዳን ጌታን መጠየቅ እንችላለን። ለምሳሌ፣ ወንድም ወይም እህት በስራ ድጋፍ ሲያስፈልጋቸው ወይም ጓደኛ ሙገሳ ሲያስፈልገው እንዲያሳያችሁ ጠይቁት። ከዛም፣ መነሳሳት ሲሰማችሁ፣ ተግብሩት! ይህንን ፀሎት እና አገልግሎት ልማድ ካደረጋችሁ፣ ከዛም ታማኝ፣ ቋሚ ተግባራችሁ የእናንተን እና የሌሎችን ህይወት ይባርካል። “ግሰቦችን፣ ቤተሰቦችን፣ ህዝቦችን፣ እና አለምን መቀየር እንደምትችሉ” ፕሬዘደንት ኡክዶርፍ ቃል ገብተዋል።

አትም