2017 (እ.አ.አ)
ጻድቆች በእምነት ይኖራሉ
ሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ)


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ)

ጻድቆች በእምነት ይኖራሉ

መምህሩ እና ሳሙና ሰሪው

በእግዚያብሔር ስለማያምን አንድ የሳሙና ሰሪ የሚነገር የድሮ የአይሁድ ታሪክ አለ። አንድ ቀን ከመምህር ጋር እየተራመደ ሳለ እንዲህ አለ፣“አንድ ሊገባኝ የማይችል ነገር አለ።” ለሺህ አመታት ያህል ሀይማኖት ነበረን። ነገር ግን የትም ቦታ ስትመለከት ክፋት፣ ማጭበርበር፣ አለመታመን፣ ኢፍትሀዊነት፣ ህመም፣ ረሀብ፣ እና ብጥብጥ አለ። ሀይማኖት አለምን ምንም ያሻሻላት መስሎ አይታይም። ስለዚህ ልጠይቅህ እስቲ፣ ጥቅሙ ምንድነው?

መምህሩ ለጥቂት ጊዜ ምላሽ አልሰጠም ግን ከሳሙና ሰሪው ጋር መጓዙን ቀጠለ። ቆይቶም ልጆች፣ አብዋራ በአብዋራ ሆነው፣ በቆሻሻ ውስጥ የሚጫወቱበት ሜዳን ተቃረቡ።

“አንድ ያልገባኝ ነገር አለ፣” አለ መምህሩ። “እነዚያን ልጆች ተመልከታቸው። ለሺህ አመታት ያህል ሳሙና ነበረን፣ እና ግን እነዚያ ልጆች የቆሸሹ ናቸው። ሳሙና ጥቅሙ ምንድነው?”

ሳሙና ሰሪው እንዲህ ሲል መለሰ፣ “ግን መምህር፣ ስለነዚህ የቆሸሹ ልጆች ሳሙናንን መውቀስ ተገቢ አይደለም። ሳሙና ተግባሩን ከመፈፀሙ በፊት እኮ ልንጠቀምበት ይገባል።”

መምህሩ ፈገግ ብሎ እንዲህ አለ፣ “በትክክል።”

እንዴት ነው መኖር ያለብን?

ሐዋርያው ጳውሎስ፣ የብሉ ኪዳን ነብይን ጠቅሶ፣ አማኝ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በማጠቃለል በፅሁፉ እንዲህ አለ፣ “ጻድቅ በእምነት ይኖራል” (ሮሜ 1፥17)።

በእርግጥ በዚህ ቀላል አርፍተ ነገር ውስጥ ደካማ እና ውጤታማ ባልሆነ እና ህይወቶችን የመቀየር ሀይል ባለው ሀይማኖት መካከል ያለውን ልዩነት እንረዳለን።

ነገር ግን በእምነት መኖር ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት፣ እምነት ምን እንደሆነ መረዳት አለብን።

እምነት ከማመን በላይ ነው። ይህም ተግባርን አክሎ በእግዚአብሔር ላይ ሙሉ ለሙሉ መታመን ማለት ነው።

ይህም ከመመኘት በላይ ነው።

ይህም ቁጭ ብሎ ብቻ፣ እራስን ከመነቅነቅ፣ እና እንስማማለን ከማለት በላይ ነው። “ጻድቅ በእምነት ይኖራል፣” ስንል የምንመራው በእምነታችን ነው ማለታችን ነው። ተግባራችን ከእምነታችን ጋር በማይጣረስ መልኩ ይሆናል—ሀሳብ የለሽ ከሆነ የመታዘዝ ስሜት ሳይሆን ነገር ግን ለእግዚያብሔር እና ለልጆቹ ለገለጸው በዋጋ ለማይተመን ጥበብ ላለን እርግጠኛ እና ከልብ በሆነ ፍቅር መሆን አለበት።

እምነት ከተግባር ጋር መሆን አለበት፤ ያለበለዚያ ህይወት አይኖረውም ( ያእቆብ 2፥17ተመልከቱ)። ያ በፍፁም እምነት አይደለም። አለምን እንተወውና፣ አንድ ግለሰብን እንኳን ለመቀየር ሀይል የለውም።

እርግጠኛ በማይኮንባቸው ጊዜያትም ቢሆን፣ እንዲሁም በትክክል በማያዩበት እና በጥራት በማይረዱበት የሚያጠራጥር እና ክፉ ጊዜያትም እንኳን ቢሆን—የእምነት ወንዶች እና ሴቶች በመሀሪው የሰማይ አባታቸው ላይ ይታመናሉ።

የእምነት ወንዶች እና ሴቶች የደቀመዝሙርነትን መንገድ ከልባቸው ይጓዛሉ እና የተወዳጁ አዳኛቸው፣ የኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌ ለመከተል ይጥራሉ። እምነት ያበረታል እና፣ በእርግጥም፣ ልባችንን ወደ ሰማይ እንድናደርግ እና ለወገኖቻችን ለመድረስ፣ ከፍ ለማድረግ፣ እና ለመባረክ ያነሳሳናል።

ሀይማኖት ያለተግባር ማለት ልክ በካርቶኒ ውስጥ እንደሚቆይ ሳሙና ነው። አስደናቂ አቅም ይኖረዋል፣ ነገር ግን በተግባር የታቀደለትን አላማ እስኪያሳካ ድረስ ለውጥ ለማምጣት ጥቂት ሀይል ብቻ ነው ያለው። በዳግም የተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የተግባር ወንጌል ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እውነተኛ ሀይማኖትን እንደ የተሰፋ፣ የእምነት፣ እና የልግስና መልእክት፣ ሌሎችን በመንፈሳዊ እና በምድራዊ መንገዶች መርዳትንም ጨምሮ ታስተምራለች።

ከጥቂት ወራት በፊት፣ ባለቤቴ፣ ሀርየት፣ እና እኔ ከልጆቻችን ጋር በሜዲትሬንያ አከባቢ የቤተሰብ ጉዞ ላይ ነበርን። አንዳንድ የስደተኞች መንደርን ጎበኘን እና በጦርነት ከፈራረሱ አገራት የመጡ ቤተሰቦችን አገኘን። እነዚህ ሰዎች ከእኛ እምነት አልነበሩም፣ ነገር ግን የእኛ ወንድሞች እና እህቶች ነበሩ እናም አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸው ነበር። የእኛ ቤተክርስቲያን አባላት ንቁ እምነታቸው እንዴት በችግር ላይ ላሉት ወገኖች፣ ሀይማኖታቸው፣ ዜግነታቸው ወይም ትምህርታቸው ምንም ይሁን ምን እርዳታን፣ ድጋፍን፣ እና ተስፋን እንደሚያመጣ በቀጥታ ስንመለከት ልቦቻችን በጣም ተነክተው ነበር።

ቋሚ በሆነ ተግባር የሚታገዝ እምነት ልብን በደግነት፣ አእምሮን በጥበብ እና መረዳት፣ እናም ነብስን በሰላም እና ፍቅር ይሞላዋል።

እምነታችን በአከባቢያችን ያሉትን እና እራሳችንንም ሊባርክ እና የቅድስና ተፅእኖ ሊያሳድር ይችላል።

እምነታችን አለምን በመልካምነት እና ሰላም ሊሞላት ይችላል።

እምነታችን ጥላቻን ወደ ፍቅር እናም ጠላቶችን ወደ ጓደኝነት ሊቀይር ይችላል።

ጻድቅ፣ ከዛም፣ በእምነት ትግበራ ይኖራሉ፤ በእግዚአብሔር በመታመን እና በእርሱ መንገድ በመራመድ ይኖራሉ።

እናም የዛ አይነት እምነት ነው ግለሰቦችን፣ ቤተሰቦችን፣ ህዝቦችን፣ እና አለምን ሊቀይር የሚችለው።

አትም