2017 (እ.አ.አ)
የክህነት መሀላ እና ቃልኪዳን
ሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ)


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ማስተማሪያ መልእክት፣ ሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ)

የክህነት መሀላ እና ቃልኪዳን

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ መነሳሳትን እሹ። የሴቶች መረዳጃ ማህበር እቅድን ማወቅ እንዴት የእግዚአብሔር ሴት ልጆችን ለዘለአለማዊ ህይወት በረከቶች ያዘጋጃል?

ምስል
Relief Society seal

እምነት ቤተሰብ እርዳታ

የክህነት መሀላ እና ቃልኪዳን እንዴት በግላችን እንደሚሰራ እኛ እንደ እህቶች የበለጠ ስንረዳ፣ በበለጠ ሁኔታ የክሀነት በረከቶች እና ቃልኪዳኖችን በእቅፍ እንቀበላለን።

ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ጉባኤ ሽማግሌ ኤም. ራስል ባላርድ እንዲህ አሉ፣ “ከጌታ ጋር ቅዱስ ቃል ኪዳን የገቡ እና እነዚያን ቃል ኪዳኖች የሚያከብሩ የግል ራዕይ ለመቀበል፣ በመላእክት አገልግሎት ለመባረክ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር፣ የወንጌልን ሙላት ለመቀበል፣ እና በመጨረሻም፣ አብ ያላቸውን ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ጎን ወራሾች ለመሆን ይችላሉ።”1

የክህነት መሀላ እና ቃል በረከቶች እና ቃልኪዳን ለወንዶች እና ለሴቶች ለሁለቱም የሚገቡ ናቸው። በቀድሞ የአጠቃላይ የሴቶች መረዳጃ አመራር ውስጥ አማካሪ የነበረችው፣ እህት ሼሪ ኤል. ደው እንዲህ አለች፣ “በጌታ ቤት ውስጥ በከፍተኛ ስርአቶች የሚካተተው የክህነት ሙላት የሚገኘው ወንድ እና ሴት በጋራ በመሆን ብቻ ነው።”2

እህት ሊንዳ ኬ. በርተን፣ የአጠቃላይ የሴቶች መረዳጃ ፕሬዘደንት፣ ይህንን ጥሪ አስተላልፋለች፣ “በ ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 84፥33-44ውስጥ የሚገኘውን የክህነት መሀላ እና ቃልኪዳን በአእምሮአችሁ እንድትይዙ እጋብዛለሁ። ይህንን በማድረግ፣ መንፈስ ቅዱስ ስለ ክህነት ያላችሁን መረዳት እንደሚያሳድገው እና በድንቅ መንገዶች እንደሚያነሳሳችሁና ከፍ እንደሚያደርጋችሁ ቃል እገባለሁ።”3

ዮሴፍ ስሚዝ ለሴቶች መረዳጃ የሰጠው መመሪያ ሴቶችን “ወደ ክህነት እድሎች እና በረከቶች እናም ስጦታዎች እንዲመጡ” ለማዘጋጀት ታቅዶ ነበር። ይሄ የሚሳካው በቤተመቅደስ ስነስርዓቶች አማካኝነት ነው።

“የቤተመቅደስ ስነስርአቶች የክህነት ስነስርአቶች ናቸው፣ ነገር ግን እነርሱ ለወንድ ወይም ለሴት መለኮታዊ ቢሮን አይሰጡም። [እነዚህ ስነስርአቶች የሚሟሉት] ወንድ እና ሴት የሆኑት የጌታ ሰዎች ‘ከላይ በሚመጣ ሀይል እንደሚታደሉ ነው’ [ት. እና ቃ. 38፥32]።”4

ተጨማሪ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶች እና መረጃ

ትምህርትና ቃልኪዳኖች 84፥19-40፤; 121፥45–46፤reliefsociety.lds.org

ማስታወሻዎች

  1. ኤም. ራስል ባለርድ፣ “Men and Women and Priesthood Power፣” Liahona፣ መስከረም 2014 (እ.አ.አ.)፣ 36።

  2. ሼሪ ኤል. ደው፣ Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society [2011 (እ.አ.አ.)]፣ 128።

  3. ሊንዳ ኬ. በርተን፣ “Priesthood Power—Available to All፣” Ensign፣ ሰኔ 2014 (እ.አ.አ.)፣ 39–40።

  4. Gospel Topics, “Joseph Smith’s Teachings about Priesthood, Temple, and Women,” topics.lds.org.

አትም