2017 (እ.አ.አ)
እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር መደሰት
ነሐሴ 2017 (እ.አ.አ)


ወጣቶች

እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር መደሰት

መጥፎ ቀን ኖሯችሁ ታውቃላችሁ? ለመደሰት ምን አደረጋችሁ? “እያንዳንዳችን የልብ የሚሰበርበት፣ ተስፋ የምንቆርጥበት፣ ስቃዮቻችን እንዳሉን፣ እንዲሁም ተስፋ የምንቆርጥበት እና አንዳንዴም የምንጥለቀለቅበት ጊዜዎች እንዳሉን” ፕሬዘዳንት ኡክዶርፍ ያውቃሉ።

መፍትሄአቸውም እርሳቸው “የደቀ መዝሙር ህይወት” ብለው የሚጠሩትን ህይወት መኖር ነው፥ “በታማኝነት መቆየት እና በእምነት ወደፊት መግፋት።” በእምነት ወደፊት ስንገፋ፣ እግዚአብሔርን ለማመን፣ ትእዛዛቱን ለመጠበቅ፣ እና ሌሎችን ለማገለገል—እናም በዚህ ሁሉም ደስታን ሊሰማን እንችላለን። ፕሬዘዳንት ኡክዶርፍ እንዳሉት፣ “የደቀ መዝሙር ህይወት የሚኖሩት … ትንሹ ስራቸው ታላቅ ልዩነት የሚያመጣላቸው ናቸው።”

የደቀ መዝሙር ህይወት ለመኖር የምትችሉበትን መንገዶች ለመዘርዘር አስቡበት። ለምሳሌ፣ “ለወላጅ ምግብ የማዘጋጀት” አይነት የአገልግሎት ሀሳብን ወይም “ለወንድሞቼና እህቶቼ ተጨማሪ ትዕግስት እንዲኖራችሁ” የሚል አይነት ትእዛዛት የሚጠበቅበት ሀሳብን ለመጻፍ ትችላላችሁ። በምትረበሹበት ወይም ከአቀማችሁ በላይ እንደሆነ በሚቀጥለው ጊዜ ሲሰማችሁ፣ የጻፋችሁትን ዝርዝር አውጡ፣ አንድ ሀሳብን ምረጡ፣ እና ሞክሩት።