2017 (እ.አ.አ)
የተቀደሰ ህይወት መኖር
ነሐሴ 2017 (እ.አ.አ)


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት መልእክት፣ ነሐሴ 2017 (እ.አ.አ)

የተቀደሰ ህይወት መኖር

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ የመንፈስ ምሪትን እሹ። የሴቶች መረዳጃ ማህበር እቅድን ማወቅ እንዴት የእግዚአብሔር ሴት ልጆችን ለዘለአለማዊ ህይወት በረከቶች ያዘጋጃል?

Relief Society seal

እምነት ቤተሰብ እርዳታ

የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን እንዳሉት፣ “መቀደስ ማለት መለየት ወይም አንድ ነገርን እንደ ለቅዱስ አላማ ለማተኮር የተወሰነ ነው ማለት ነው።” “በዚህ ህይወት እውነተኛ ውጤታማነት የሚመጣው ህይወታችንን—ያም ማለት፣ ጊዜአችንን እና ምርጫዎቻችንን—ለእግዚአብሔር በመቀደስ ነው።”1

የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ሽማግሌ ኒል ኤ. ማክስዌል እንዳሉት፣ “መቀደስን በመለኮት መመሪያ በሚሰጥበት ጊዜ ንብረቶቻችንን አሳልፈን እንደመስጠት አይነት እናስብበታለን። ነገር ግን የመጨረሻው ቅደሳ ራስን ለእግዚአብሔር መስጠት ነው።”2

ራሳችንን ለእግዚአብሔር አላማዎች ስንቀድስ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው ያለን እምነት ያድጋል። የተቀደሰ ህይወት ስንኖርበት፣ በእነዚያ ድርጊቶች ቅዱስ ለመሆን እንችላለን።

የሴቶች መረዳጃ ማህበር የመጀመሪያ አማካሪ ኬሮል ኤም፣ ስቲቨንስ እንዳሉት፣ “ሽማግሌ ሮበርት ዲ. ሔልስ እንዳስተማሩት፣ ‘ቃል ኪዳኖችን ስንገባ እና ስናከብር፣ ከአለም ወጥተን እና ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንገባለን።’

“ተቀይረናል ልዩ እንመስላለን፣ እናም ተግባራችንም የተለየ ነው የምናዳምጣቸው እና የምናነባቸው እና የምንላቸው ልዩ ናቸው፣ እናም የምንለብሰውም ልዩ ነው ምክንያቱም ከእርሱ ጋር የተሳሰርን የእግዚአብሔር ሴት ልጆች ሆነናልና።”3

ቅድስና እግዚአብሔር “ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር [የሚገባው] ቃል ኪዳን [ነውና]፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ህጌንም በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።” (ኤርምያስ 31፥33)። በተቀደሰ ህይወት መኖር እግዚአብሔር ለእኛ ካለው አላማ ጋር የሚስማማ ነው።

ተጨማሪ ቅዱሳት መጻህፍቶች

1 ተሰሎንቄ 1፥3፤ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 105፥5

reliefsociety.lds.org

ማስታወሻዎች

  1. ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን፣ “Reflections on a Consecrated Life,” Liahona፣ ህዳር 2010 (እ.አ.አ)፣ 16።

  2. ኒል ኤ. ማክስዊል፣ “Consecrate Thy Performance,” Liahona፣ ሐምሌ 2002 (እ.አ.አ)፣ 39።

  3. ኬሮል ኤም. ስቲቨንስ፣ “Wide Awake to Our Duties,” Liahona፣ ህዳር 2012 (እ.አ.አ)፣ 115–16።