የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ነሐሴ 2017 (እ.አ.አ)
የደቀ መዝሙር ህይወት
ከሰላሳ አመት በፊት በጋና ውስጥ፣ ዶ የምትባል የኮሌጅ ተማሪ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን መሰብሰቢያ ቤት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ገባች። ዶን አብሯት እንድትመጣ ጓደኛዋ ጋብዛት ነበር፣ እናም ዶም ቤተክርስቲያኗ ምን አይነት እንደሆነች ለማወቅ ፈልጋ ነበር።
ሰዎቹ በጣም ጥሩ እና አስደሳች በመሆናቸው፣ “ምን አይነት ቤተክርስቲያን ናት” በማለት ተደንቃ ነበር።
ዶ በጣም ተደንቃ ስለቤተክርስቲያኗ እና በጣም ብዙ በሆነ ደስታ ስለተሞሉት ህዝቧ ለመማር ወሰነች። ግን ይህን ለማድረግ በጀመረችበት ወዲያውኑ፣ ቀና ሀሳብ ያላቸው ቤተሰብ እና ጓደኞች በሁሉም ሁኔታ ይቃወሟት ጀመሩ። ስለቤተክርስቲያኗ መጥፎ ነገሮች ተናገሩ እናም እርሷ ሀሳቧን እንድትቀይር የሚችሉትን ያህል አደረጉ።
ነገር ግን ዶ ምስክርነትን ተቀብላለች።
እምነት ነበራት፣ እና ወንጌልን ትወዳለች፣ ይህም ህይወቷን በደስታ ሞላት። እና ስለዚህ፣ ወደ ጥምቀት ውሀ ገባች።
ከዚያም በኋላ፣ ራሷን በጥናት እና በጸሎት ዘፈቀች። ጾመች እናም የመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖች በህይወቷ ውስጥ ለማግኘት ፈለገች። በዚህም ምክንያት፣ የዶ ምስክርነት እና እምነት በጥንካሬና በጥልቀት አደገ። በመጨረሻም ጌታን በሙሉ ጊዜ ሚስዮንነት ለማገልገል ወሰነች።
ከሚስዮን ስትመለስ፣ ከሚስዮን ከተመለሰ
ዶ ካኩ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን ደስታ ለመጀመሪያ ጊዜ ካጋጠማት ብዙ አመቶች አልፈዋል። በዚያም ጊዜ፣ ህይወት ለእርሷ ሁልጊዜም አስደሳች አልነበረም። የራሷን ፋንታ የሆነውን ልብ መሰበር እና መከራ፣ እንዲሁም የሁለት ልጆች መሞትን ጸንታለች—የነዚያ አጋጣሚዎች ጥልቅ ሀዘን አሁንም በልቧ ላይ ከባድ ናቸው።
ነገር ግን እርሷ እና ባለቤቷ አንተኒ ወደ እርስ በራሳቸው እና በልባቸው በሙሉ ወደሚወዱት ወደ ውዱ የሰማይ አባታቸው ለመቀራረብ ጥረዋል።
ዛሬ፣ ወደ ጥምቀት ውሀ ከገባች ከ30 አመት በኋላ፣ እህት ካኩ ሌላ የሙሉ ጊዜ ሚስዮን ፈጸመች—በዚህ ጊዜ የናይጄሪያ ሚስዮን ፕሬዘደንት በነበረው በባለቤቷ ጎን ነበር ያገለገለችው።
እህት ካኩን የሚያውቁ ሁሉ በእርሷ አንድ ልዩ ነገር አለ ይላሉ። ድምቀት አላት። ከእርሷ ጋር ጊዜ አሳልፎ ደስታ ላለመሰማት አስቸጋሪ ነው።
ምስክሯ እርግጠኛ ነው፥ “አዳኝ እንደ ሴት ልጁ እና ጓደኛው እንደሚያየኝ አውቃለሁ ( ሞዛያ 5፥7፤ኤተር 3፥14ተመልከቱ)፣” ትላለች። “እናም በምለው ብቻ ሳይሆን በማደርገውም፣ የእርሱ ጓደኛ ለመሆን እየተማርኩኝ እና በጣም እየጣርኩኝ ነኝ።”
እኛ ደቀ መዛሙርት ነን
የእህት ካኩ ታሪክ ከብዙ ሌሎች ጋር የተመሳሰለ ነው። እውነትን ለማወቅ ፍላጎት ነበራት
ነገር ግን የሚቃረናት ምንም ያህል ቢሆን፣ ስቃዩም ምንም ያህል ቢሆን፣ በእምነት ወደፊት ገፍታለች። እናም እስከዚህም ያህል አስፈላጊ በሚሆነውም፣ ደስታዋን ጠብቃለች። የህይወት ክብደትን ለመፅናት ብቻ ሳይሆን ደግሞም የመበልጸግ መንገድን አግኝታለች።
ታሪኳ ከእናንተ እና ከእኔ ጋር የተመሳሰለ ነው።
ጉዞአችን ቀላል እና ፍተና የሌለበት ሆኖ የሚገኝበት አልፎ አልፎ ነው።
እያንዳንዳችን የየራሳችን የልብ ህመም
ተስፋ የምቆርጥበት እና አንዳንዴም በዚሁ የምንጥለቀለቅበት ጊዜዎች አሉ።
ነገር ግን የደቀ መዝሙር ህይወትን የሚኖሩት—ታማኝ የሚሆኑት እና ወደፊት በእምነት የሚገፉት፤ በእግዚአብሔር የሚያምኑት እና ትእዛዛቱን የሚጠብቁት፤1 በወንጌል ቀን በቀን እና ሰአት በሰአት የሚኖሩት፤ በአንድ መልካም ስራ በተራ የክርስቶስ አይነት አገልግሎት በአካባቢያቸው ላሉት የሚሰጡት—ትንሹ ስራቸው ታላቅ ልዩነት የሚያመጣላቸው ናቸው።
ትንሽ ደግ፣ በተጨማሪ ይቅርታ የሚሰጡ፣ እና ተጨማሪ መሀሪ የሚሆኑት ምህረት የሚቀበሉት መሀሪዎች ናቸው።2 ከአንድ እንክብካቤ እና የፍቅር ተግባር በመነሳት ይህን አለም የተሻለ የሚያደርጉት እና የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙርትነት የሆነውን የተባረከ፣ የሚያረካ፣ እና ሰላይ የሚሰጥ ህይወትን የሚኖሩት በመጨረሻ ደስታን የሚያገኙት ናቸው።
ህ የእግዚአብሔር ፍቅር፣ በሰው ልጆች ልብ ውስጥ ሁሉ ራሱን በስፋት የሚያፈስ፣ ከሁሉ ነገሮች በላይ አስፈላጊ እና ለነፍስ በጣም ደስ የሚያሰኝ”3 እንደሆነ ያውቃሉ።
© 2017 በIntellectual Reserve, Inc. መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/17 (እ.አ.አ)። ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/17 (እ.አ.አ)። First Presidency Message, August 2017 ትርጉም። Amharic 97928 506