ወጣቶች
እግዚአብሔር ሆይ፣ ለነቢይ እናመሰግንሀለን
ነቢያችን፣ ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ እናንተን እንዴት አነሳስተዋል? ስለእርሳቸው ከሁሉም በላይ የምታስታውሱት ምንድን ነው? በማስታወሻችሁ ውስጥ ስለፕሬዘደንት ሞንሰን እና ስለህይወታቸው ለመጻፍ አስቡበት—ልክ በዚህ መልእክት ውስጥ እርሳቸው ያስታወሱትን የእያንዳንዱ ነቢያት ተፅዕኖን እንደገለጹ አይነት።
ከእርሳቸው የምትወዱትን ጥቅሶች ለመምረጥ እና በትምህርት ቤት መፅሐፍ ወይም በክፍላችሁ ውስጥ ማስታወሻ ውስጥ ሁልጊዜ ለማየት በምትችሉበት ቦታ ለመጻፍ አስቡበት። የጥቅስ ፎቶ በመስራትም የእጅ ስልካችሁ ላይ የጀርባ ምስል ለማድረግ ትችላላችሁ። ጥቅሱን ስትመለከቱም ጊዜ ሁሉ፣ ስለህያው ነቢያት አስፈላጊነት ለማሰላሰል እና ዛሬ በዚህ ያሉት እኛን ለማፍቀር እና ለመምራት እንደሆነ ለማስታወስ ትችላላችሁ።