2017 (እ.አ.አ)
ነቢያት ይመሩናል
መስከረም 2017 (እ.አ.አ)


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ መስከረም 2017 (እ.አ.አ)

ነቢያት ይመሩናል

ከጥቂት አመት በፊት፣ ቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ጉባኤ በሳምንት አንዴ በሚሰበሰቡበት በሶልት ሌክ ቤተመቅደስ ክፍል ውስጥ ተቀምጬ ነበር። የቀዳሚ አመራር የሚያዩትን ግድግዳ ተመለከትኩኝ እና በዚያም የእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ፕሬዘደንቶችን ፎቶዎች አየሁ።

እነርሱን ስመለከት፣ የእኔ ቀዳሚዎች፣–ከነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ [1850–1844 (እ.አ.አ)] እስከ ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሒንክሊ [1910–2008 (እ.አ.አ)]–እንዲህ አሰብኩኝ፣ “ከእያንዳንዱ ለነበሩት መመሪያዎች እንዴት ምስጋና ይሰማኛል።”

እነዚህ ያልተነቃነቁ፣ በምንም ያልተደናቀፉ፣ እና በምንም ያልወደቁ ታላቅ ሰዎች ነበሩ። እነዚህም የእግዚአብሔር ሰዎች ነበሩ። ስለማውቃቸው እና ስለማፈቅራቸው ስለነዚህ ዘመን ነቢያት ሳስብ፣ ህይወታቸውን፣ ጸባዮቻቸውን፣ እና የእነርሱን በመንፈስ የሚያነሳሱ ትምህርቶችን አስታውሳለሁ።

በተወለድኩበት ጊዜ ፕሬዘደንት ሒበር ጄ. ግራንት (1856–1945) የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት ነበሩ። የእርሳቸውን ህይወት እና ያስተማሩትን ሳሰላስልባቸው፣ ፕሬዘደንት ግራንት እንደ ምሳሌ የሚያሳዩ ጸባይ በአቋም በፅናታቸው–መልካም እና ልዑል በሆኑት ነገሮች ላይ አቋም ፅናት እንደነበራቸው አምናለሁ።

ፕሬዘደንት ጆርጅ አልበርት ስሚዝ [1870–1951 (እ.አ.አ)] የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት የነበሩት በሶልት ሌክ ስቲ ዎርዴ ውስጥ እንደ ኤጲስ ቆጶስ በማገለግልበት ጊዜ ነበር። በጌታ እና በጠላት መካከል ታላቅ ጦርነት እንደነበር አመልክተው ነበር። እንዲህ አስተምረዋል፣ “በጌታ መስመር በኩል ከቆያችሁ፣ በእርሱ ተፅዕኖ ስር ትሆናላችሁ እናም ስህተት ለማድረግ ምንም ፍላጎት አይኖራችሁም።”1

በ1963 (እ.አ.አ) በፕሬዘደንት ዴቪድ ኦ. መኬይ [1873–1970 (እ.አ.አ)] እንደ አስራ ሁለት ሐዋሪያት ቡድን አባል እንዳገለግል ተጠርቼ ነበር። በህይወት አኗኗራቸው ለሌሎች ስለማሰብ አስተምረው ነበር። እንዲህ ብለዋል፣ “እውነተኛ ክርስቲያንነት ተግባር ያለው ፍቅር ነው።”2

የቤተክርስቲያኗ ታዋቂ ጸሀፊ የነበሩት ፕሬዘደንት ጆሴፍ ፊልዲንግ ስሚዝ [1876–1972 (እ.አ.አ)] በወንጌል ምሁር ህይወታቸው ውስጥ የመመሪያ መሰረታዊ መርሆ ነበራቸው። ባለማቆም ቅዱሳት መጻህፍትን አነበቡ እናም ከማውቃቸው ከማንም ሰዎች በላይ በእነዚህ ገጾች ውስጥ የሚገኙትን ትምህርቶች በደንብ ያውቋቸው ነበር።

በልጅነቴ ፕሬዘደንት ሔሮልድ ቢ. ሊ [1899–1973 (እ.አ.አ)] እንደ ካስማዬ ፕሬዘደንት ያገለግሉ ነበር። እርሳቸው ለመጥቀስ የሚወዱት “በቅዱስ ቦታዎች ቁሙ፣ እናም አትነቃነቁ”3የሚለው ነበር። ቅዱሳን የመንፈስ ቅዱስ ማሾክሾክን እንዲያዳምጡ እና ለዚህም መልስ እንዲሰጡ አበረታትተዋል።

የፕሬዘደንት ስፔንሰር ደብሊው. ኪምባል [1895–1985 (እ.አ.አ)] የህይወት መመሪያ መሰረታዊ መርሆ ቢኖር እራስን መስጠት ነው ብዬ አምናለሁ። እርሳቸው በሙሉነት እና በምንም በማያሻማ እራሳቸውን ለጌታ ሰጥተው ነበሩ። በወንጌል ለመኖር እራሳቸውን ሰጡ

ፕሬዘደንት ኤዝራ ታፍት ቤንሰን [1899–1994 (እ.አ.አ)] የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት ሲሆኑ፣ በቀዳሚ አመራር እንደ እርሳቸው ሁለተኛ አማካሪ እንዳገለግል ጥሪ ሰጡኝ። የእርሳቸው መመሪያ መሰረታዊ መርሆ የሆነው ፍቅር በሚወዱት ጥቅስ ላይ የተገበረ ነበር፣ “እናንተ ምን ዐይነት ሰዎች ትሆኑ ዘንድ ይገባችኋል? እውነት እላችኋለሁ እንደ እኔ ሁኑ።”4

ፕሬዘደንት ሀወርድ ደብሊው. ሀንተር [1907–1995 (እ.አ.አ)] ሁልጊዜ በሌሎች ላይ የተሻለ ነገሮችን የሚመለከቱ ነበሩ። ሁልጊዜም ሩህሩህ ነበሩ፤ ሁልጊዜም ትሁት ነበሩ። እንደ እርሳቸው ሁለተኛ አማካሪ ማገልገሌ ለእኔ ክብር ነበር።

ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሒንክሊ ለማድረግ ከምንችለው በላይ እንድናደርግ ነበር ያስተማሩን። ስለአዳኝ እና ስለተልዕኮው ሀይለኛ ምስክርነት ሰጥተዋል። በፍቅርም አስተምረውናል። እንደ መጀመሪያ አማካሪው ማገልገልም ለእኔ ክብር እና በረከት ነበር።

አዳኝ ነቢያትን የሚልከው ስለሚወደን ነው። በዚህ ጥቅምት አጠቃላይ ጉባኤ፣ የቤተክርስቲያኗ አጠቃላይ ባለስልጣኖች እንደገና የእርሱን ቃላት የማካፈል እድል አላቸው። ይህን ሀላፊነት በታላቅ ክብር እና ትህትና እንቀርበዋለን።

በዳግም የተመለሰችው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምድር ላይ በመሆኗ እና ቤተክርስቲያኗም በራዕይ አለት ላይ የተመሰረተች በመሆኗ እንዴት የተባረክን ነን። ቀጣይ ራዕይ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መሰረታዊ ነገር ነው።

በአጠቃላይ ጉባኤ አብዝቶ የሚመጣውን የግል ራዕይ ለመቀበል እንዘጋጅ። ህያው ነቢያትን እና ሐዋሪያትን ለመደገፍ እጆቻችንን ስናነሳ ልባችን በዝልቅ ቆራጥነት ይሞላ። መልእክቶቻቸውንም ስናዳምጥ፣ እኛም እንብራራ፣ ከፍ ከፍ እንደረግ፣ እንፅናና፣ እናም እንጠናከር። ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ–ለወንጌሉ እና ለስራው–ራሳችንን ለመስጠት እናም ትእዛዛቱን ለመጠበቅና ፈቃዱን ለማከናወን በታደሰ የልብ ውሳኔ ለመኖር እንዘጋጅ።

አትም