የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ማስተማሪያ መልእክት፣ መስከረም 2017 (እ.አ.አ)
በልብ አንድ
በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ የመንፈስ ምሪትን እሹ። የሴቶች መረዳጃ ማህበር እቅድን ማወቅ እንዴት የእግዚአብሔር ሴት ልጆችን ለዘለአለማዊ ህይወት በረከቶች ያዘጋጃል?
“እነርሱ አንድ ልብ እና አንድ አእምሮ ስለነበሩ፣ እና በጽድቅም ስለኖሩ፣ ጌታ ህዝቡን ፅዮን ብሎ ጠራቸው፤ እና በመካከላቸውም ማንም ድሀ አልነበረም” (ሙሴ 7፥18)። አንድ ለመሆን እንዴት እንችላለን?
የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ሽማግሌ ኤም. ራስል ባለርድ እንዳሉት፥ “በእንግሊዘኛው ቃል atonement ውስጥ አንድየሚል ቃል አለ። የሰው ዘር በሙሉ ይህን ቢረዳ፣ እድሜ፣ ዘር፣ ጾታ፣ ሀይማኖት፣ ወይም የህብረሰብ ወይም የኢኮኖሚ ሁኔታ ምንም ቢሆን የማናስብበት ማንም አይኖሩም። የአዳኝን ምሳሌ ለመከተል እንጥራለን እናም ለሌሎች በምንም ክፉ፣ ግድ የለሽ፣ ክብር የማይሰጥ፣ ወይም ስሜት የሌለው አንሆንም።”1
ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ፣ የቀዳሚ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ እንዳስተማሩት፥ “ሰዎች መንፈስ ሲኖራቸው፣ ስምምነትን ይጠብቃሉ የእግዚአብሔር መንፈስ በምንም ጠብን አይፈጥርም ( 3 ኔፊ 11፥29 ተመልከቱ)። … ወደ ግል ሰላም እና ከሌሎች ጋር አንድ ወደመሆን ስሜት ይመራል።”2
ስለቤተሰብ ፈተና ሲናገሩ፣ እንደ ሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ ያገለገሉት ኬሮል ኤም. ስቲቨንስ፣ እንዲህ ብለዋል፥ “ከጋብቻ በመፋታት፣ በመተው በሚመጣ ስቃይና አለመረጋጋት፣ ወይም ያላገባች እናት ከመሆን ጋር በተያያዘ ሀላፊነት አልኖርኩም። የልጅን መሞት፣ ልጅ ለመውለድ አለመቻልን፣ ወይም ከአንድ አይነት ጾታ ጋር መዋደድን አጋጥሞኝ አያውቅም። መጎሳቀልን ወይም መጥፎ በሽታን ወይም ሱስንም በህይወቴ አጋጥሞኝ አያውቅም። እነዚህ እኔ የምሞከርበት እድሎች አልነበሩም።
“… ነገር ግን የራሴ የግል ፈተናዎች በኩል …ይህን ከሚረዳ ጋር ተዋውቄአለሁ። …በተጨማሪም፣ በሴት ልጅ፣ በእናት፣ በሴት አያት፣ በእህት፣ በአክስት፣ እና በጓደኛ በኩል የጠቀስኳቸው ስጋዊ ፈተናዎች አጋጥመውኛል።
“እንደ እግዚአብሔር የቃል ኪዳን ጠባቂ ሴት ልጆች እድላችን ከፈተናዎቻችን ለመማር ብቻ አይደለም። ይህም ቃል እንደገባነው ሌሎች የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባላትን በሚታገሉበት በሀዘን እና በርህራሄ አንድ መሆን ነው።”3
ተጨማሪ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶች እና መረጃ
© 2017 በ Intellectual Reserve, Inc. መብቶች ሁሉ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ. ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/17 (እ.አ.አ)። ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/17 (እ.አ.አ)። Visiting Teaching Message, September 2017 ትርጉም። Ahmaric 97929 506