2021 (እ.አ.አ)
አዳኛችን ለእኛ ምን አድርጎልናል?
ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)


“አዳኛችን ለእኛ ምን አድርጎልናል?፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)።

የክህነት ስብሰባ

አዳኛችን ለእኛ ምን አድርጎልናል?

ፅሁፎች

ምስል
የክርስቶስ ባዶ መቃብር

ኢየሱስ ክርስቶስ ለእያንዳንዳችን ምን አድርጎልናል? ከምድራዊ ሕይወት በሰማይ አባታችን ዕቅድ ውስጥ ወደተዘረዘረው ፍጻሜያችን ለምናደርገው ጉዟችን አስፈላጊውን ነገር ሁሉ አድርጎልናል። ስለዚያ ዕቅድ አራት ዋና ገፅታዎች እናገራለሁ። …

ይህ ትንሳኤ እያንዳንዳችን እንዲሁም የምንወዳቸው ሰዎች የሚያጋጥሟቸውን ምድራዊ ፈተናዎች ለመቋቋም የሚያስችል እይታን እና ጥንካሬን ይሰጠናል። በውልደት ወይም በስጋዊ ሕይወት ያገኘነውን አካላዊ፣ አዕምሮአዊ ወይም ስሜታዊ ጉድለቶችን የመመልክቻ አዲስ መንገድ ይሰጠናል። ሃዘኖችን፣ ውደቀትን እና ብስጭቶችን የምንቋቋምበት ጥንካሬ ይሰጠናል።

ትንሳኤው በምድራዊ ሕይወታችን ወቅት የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እንድንጠብቅ ኃይለኛ ማበረታቻ ይሰጠናል። …

ንስሃ ለሚገቡት ለሁሉም ሟቾች ሃጢያቶች መስዋዕት ለመሆን አዳኛችን እና ቤዛችን የማይገለፅ ስቃይን ተቋቋመ። ይህ የሃጢያት ክፍያ የመልካምነት መጨረሻ የሆነውን እንከን አልባውን ንፁህ ጠቦት የክፋት መጨረሻ መለኪያ ለሆነው ለመላው ዓለም ሃጢያቶች ሰጠ። …

… ኢየሱስ የደህንነትን ዕቅድ አስተማረን። ይህ ዕቅድ ፍጥረትን፣ የሕይወት ዓላማን፣ የተቃውሞ አስፈላጊነትን እና የምርጫ ስጦታን ያጠቃልላል። መታዘዝ ያለብንን ትዕዛዛት እና ቃልኪዳኖች እንዲሁም ወደ የሰማይ ወላጆቻችን የሚወስዱንን መለማመድ ያለብንን ስርዓቶች አስተማረን። …

አዳኛችን እንደ የሃጢያት ክፍያው አካል ሁሉንም በፍቃደኝነት ስለተለማመዳቸው ፈተናዎቻችን፣ ትግሎቻችን፣ የልብ ህመሞቻችን እና ስቃዮቻችን ይሰሙታል እንዲሁም ያውቃቸዋል። … በማንኛውንም ዓይነት ስጋዊ ድክመቶች የሚሰቃዩ ሁሉ አዳኛችን ያን ዓይነት ህመም እንዳየ እናም በሃጢያት ክፍያው አማካኝነት እንድንቋቋመው ለእያንዳንዳችን ጥንካሬን እንደሰጠን ማስታወስ አለባቸው።

አትም