2021 (እ.አ.አ)
ቤተመቅደስን ማየት እወዳለሁ፣
ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)


“ቤተመቅደስን ማየት እወዳለሁ፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ሚያዝያ 2021 (እ.አ.አ)።

የቅዳሜ ጠዋት ክፍለ ጊዜ

ቤተመቅደስን ማየት እወዳለሁ፣

ፅሁፎች

ምስል
ቤተመቅደስ

የጌታ ቤተመቅደሶች የተቀደሱ ቦታዎች እንደሆኑ አውቃለሁ። የዛሬው ስለቤተመቅደስ የመናገር አላማዬ የእናንተን እና የእኔን ብቁ የመሆን ፍላጎት ለመጨመር እና ለእኛ እየመጡ ላሉት እየጨመሩ ላሉት የቤተመቅደስ ልምዶች እድሎች ዝግጁ ለመሆን ነው።…

እናንተ ወይም እኔ ያለበቂ ንጽህና ወደ ቤተመቅደስ ከሄድን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ስለአዳኙ በቤተመቅደስ ውስጥ መቀበል የምንችለውን መንፈሳዊ ትምህርት ማየት አንችልም።

እንደዚህ ዓይነት ትምህርትን ለመቀበል ብቁ ስንሆን በቤተመቅደስ ልምዳችን አማካኝነት ተስፋ፣ ደስታ እና አወንታዊ አስተሳሰብ በሕይወታችን ሁሉ ሊያድግ ይችላል። ያ ተስፋ፣ ደስታ እና አወንታዊ አስተሳሰብ ዝግጁ የሚሆነው በቅዱስ ቤተመቅደሶች ውስጥ የሚተገበሩትን ሥርዓቶች በመቀበል ብቻ ነው። በቤተመቅደስ ውስጥ ነው ከሞት በኋላ እና ለዘላለም የሚቀጥልን የተወዳጅ ቤተሰብ ትስስሮች ማረጋገጫ መቀበል የምንችለው። …

… እናም የእኛ የዘላለም ደስታ የሚመሰረተው ተመሳሳይ ዘላቂ የሆነ ደስታን አስከምንችለው ድረስ ለብዙ ዘመዶች ለመስጠት የተቻለንን ስናደርግ እንደሆነ እናውቃለን።

በሕይወት ያሉ ቤተሰቦችን የቤተመቅደስ መታተም ሥርዓቶችን ለመቀበል እና ለማክበር ብቁ እንዲሆኑ ለመጋበዝ ውጤታማ ለመሆን ተመሳሳይ ፍላጎት ይሰማኛል። ያ ቃል የተገባው በመጨረሻው ቀናት በሁሉቱም የመጋረጃው በኩል ያለውን እስራኤል የመሰብሰብ አካል ነው።

ምስል
የሶልት ሌክ ቤተመቅደስ እደሳ

አትም