2021 (እ.አ.አ)
የእግዚአብሔር ክህነት
ነሐሴ 2021 (እ.አ.አ)


“የእግዚአብሔር ክህነት፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ነሐሴ 2021 (እ.አ.አ)፣ 20-21።

ወርሀዊ የ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ጥር 2021(እ.አ.አ)

እግዚያብሔርክህነት

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84

ስለክህነት እና ከእርሱ ጋር ስላለው ግንኙነት እያንዳንዱ ወጣት ሊያውቀው የሚገባ ነገር።

ወጣቶች

አንድ ቃል በሁለት መንገዶች ጥቅም ላይ ሲውል እንዴት የሚያምታታ ሊሆን እንደሚችል አስተውላችሁ ታውቃላችሁ? ለምሳሌ ኧርዝ የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል የምንኖርባትን ፕላኔትንም ከጫማችን ስር ያለውን ቆሻሻንም ሁለቱንም ያመለክታል። ሁለቱም ትክክል ናቸው፣ ነገር ግን ቃሉን ስትጠቀሙት ምን ማለታችሁ እንደሆነ በወቅቱ እየተናገራችሁ ባላችሁት ነገር ይወሰናል። ነገሩን ይበልጥ ግራ የሚያጋባ ለማድረግ፣ ምድር ፕላኔት የሚል ፍቺ ሲይዝ ቆሻሻ የሚለውንም ሃሳብ ያካትታል ምክንያቱም ቆሻሻ በፕላኔት ላይ ስላለ።

ክህነትየሚለውን ቃል መተርጎም

በቤተክርስቲያን በሁለት መንገዶች ከምንጠቀምባቸው ቃላት አንዱ ክህነትነው። ቃሉ አጠቃላይ የእግዚአብሔርን ሀይል እና ስልጣን ያመለክታል። ሆኖም ክህነት የሚለውን ቃል ይበልጥ በተወሰነ መንገድም እንጠቀምበታለን—“ የተሾሙ የክህነት ተሸካሚዎች ለእግዚያብሔር ልጆች ደህንነት የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ እርሱን ወክለው ለማድረግ እግዚያብሄር የሚሰጠውን ሃይል እና ስልጣን“1ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል።

ለሰው የተሰጠው ክህነት ሁሉም የእግዚያብሔር ሃይል የለውም። የሚከተለው ሰንጠረዥ ይህንን ነጥብ ያሳያል።

በዚህ ሰንጠረዥ ውስጥ የእግዚያብሔርን መጨረሻ የሌለው እና ገደብ አልባ ሃይል ጥቂት ምሳሌዎች ታያላችሁ። በዚያ ውስጥ፣ በክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዲሰሩ የእግዚአብሔር ክህነት ኃይል እና ስልጣን ስለሚሰጣቸው ብቁ ሰዎች ምሳሌዎችም ታያላችሁ።

የክህነት ስልጣን ምሳሌዎች በህይወታችሁ ውስጥ

ሁሉም የክህነት በረከቶች ለሁሉም ውድ የሰማያዊ አባት ሴቶች እና ወንዶች ልጆች ይገኛሉ፡፡ ሁለተኛው ዝርዝር በቀላሉ የክህነት ቁልፎችን በያዘ ወይም የክህነት ስልጣን በተሰጠው አማካኝነት ወደ እናንተ የሚመጡትን በረከቶች ይወክላል፡፡

ይህ እግዚአብሔር በምድር ላይ ላለችው ቤተክርስቲያኑ ያቋቋመው የአደረጃጀት እና የአስተዳደር ስርዓት ነው። ሌሎች የእግዚያብሔር የክህነት ስልጣን ምሳሌዎች የቡድኑን ሥራ ለመምራት ቁልፎች ያለውን የዲያቆናት ወይም የአስተማሪዎች ቡድን ፕሬዚዳንትን፣ በቤት ውስጥ የሚሰጡ የአባቶች በረከቶችን እና የቤተመቅደስ ስርዓቶችን እና ቃል ኪዳኖችን ያካትታሉ።

ወንዶች ሴቶች እና ክህነት

ምንም እንኳን የክህነት ሹመት የተሰጠው ለወንዶች ብቻ ቢሆንም፣ በቀዳሚ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ የሆኑት ፕሬዘዳንት ዳልን ኤች. ኦክስ አንድ አስፈላጊ መርህን አብራርተዋል፦ ክህነት የእግዚአብሔር ስራ ለመስራት የሚያገለግል ለሁሉም ልጆቹ ጥቅም እንዲውል በአደራ የተሰጠ መለኮታዊ ኃይል እና ስልጣን ነው። ክህነት ማለት ወደ ክህነት ክፍል የተጠሩት ሰዎች ወይም ስልጣኑን የሚለማመዱት ሰዎች ማለት አይደለም። ክህነትን የሚሸከሙ ሰዎች ክህነት አይደሉም።… የተሾሙ ወንዶችን ክህነቱ”ብለን መጥራት አይገባንም።2

ምንም እንኳን ሴቶች በክህነት ባይሾሙም ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ ሲሉ አብራርተዋል፣ “በማንኛውም ጥሪ ለማገልገል የክህነት ቁልፎችን በያዘ ሰው ስትለዩ በእዚያ ጥሪ ውስጥ እንዲሰሩ የክህነት ስልጣን ተሰጥቷችኋል።”3 የዚህ ጥቂት ምሳሌዎች የወጣት ሴቶች ክፍል አመራሮች፣ ወንጌልን የሚያስተምሩ እህት ሚስዮናውያን፣ እንዲያስተምሩ እና እንዲመሩ የተለየዩ በአጥቢያ እና በካስማ ያሉ መሪዎች እንዲሁም በቤተመቅደስ ውስጥ ያሉ የስርዓት ሰራተኞችን ያካትታል።

የክህነት ሃይል ሁሉንም ይባርካል።

በጥምቀት ጊዜ በገባችኋቸው ቃልኪዳኖች እና በቤተመቅደስ በምትገቧቸው ቃል ኪዳኖች አማካኘነት እናንተ ወጣት ወንዶች እና ወጣት ሴቶች የምትቀበሏቸው በረከቶች የእናንተ ናቸው። በቤታችሁ የክህነት ተሸካሚ ባይኖርም አንኳን ከእርሱ ጋር የገባችኋቸውን ቃል ኪዳኖች ስትጠብቁ በህይወታችሁ ውስጥ በእግዚያብሄር የክህነት ሃይል ትባረካላችሁ( 1 Nephi 14:14ይመልከቱ)።

በቃል ኪዳኖቻችን መሰረት ስንኖር የሚያጠናክሩንን እና የሚባርኩንን በረከቶችን እንቀበላለን። በህይወታችሁ ውስጥ ያሉትን የክህነት በረከቶች እንድታሰላስሉ እንጋብዛችኋለን—በእግዚአብሔር ህልቆ መሳፍርት የሌለው የክህነት ኃይል ምክንያት እና በተለይም በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ውስጥ በተሰጡ እና በተወከሉ የክህነት ስልጣን አማካኝነት የሚመጡ በረከቶችን።

ማስታወሻዎች

  1. ዴል ጂ. ረንለንድ እና ላይበርት ረንለንድ የመልከጼዴቅ የክህነት ስልጣን: ትምህርቱን መገንዘብ፣ መርሆዎቹን መኖር [2018(እ.አ.አ)]፣ 11)።

  2. ዳልን ኤች. ኦክስ፣ “The Melchizedek Priesthood and the Keys,” የካቲት 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 69])።

  3. ፐሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን፣ ”Spiritual Treasures፣” ጥቅ.2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ (ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 78)።