2021 (እ.አ.አ)
የጥበብ ቃል
ነሐሴ 2021 (እ.አ.አ)


“የጥበብ ቃል፣” ጓደኛ፣ ነሐሴ 2021 (እ.አ.አ)

ወርሃዊ የ ጓደኛ መልእክት፣ ነሐሴ 2021 (እ.አ.አ)

የጥበብ ቃል

ምስል
ጆሴፍ ስሚዝ በቡድን ያሉ ወንዶችን ሲያስተምር

ጆሴፍ ስሚዝ ሰዎችን ስለ ወንጌል ለማስተማር ስብሰባዎችን አካሂዷል። አንዳንድ ጊዜ ሰዎቹ ትምባሆ ያጨሱ እና ያኝኩ ነበር።

ምስል
ጆሴፍ እና ኤማ ስሚዝ

ይህም ኤማ ስሚዝን አሳስቧት ነበር። ጭሱ እና ትምባሆው ትልቅ ውጥንቅጥ ፈጠሩ እናም አንድ ትክክል ያልሆነ ነገር እንደነበረ ያስታውቅ ነበር። ኤማ እና ጆሴፍ እግዚያብሔር ስለዚህ ነገር እንዴት ይሰማዋል ሲሉ አሰቡ።

ምስል
ጆሴፍ ስሚዝ እየጸለየ

ጆሴፍ ጸለየ፣ እናም ጌታ መለሰ። ጌታ የቤተክርስቲያኗን አባላት ስለማጨስ እና ትምባሆ አስጠነቀቀ። ለሰውነታችን ጥሩ እንዳልሆኑ ተናገረ። ሻይ፣ ቡና፣ እና አልኮል ስለመጠጣትም አስጠነቀቀ።

ምስል
አትክልት

ፍራፍሬ፣ አትክልት እና ሌሎች ጤናማ ምግቦችን እንዲበሉ እግዚአብሔር ተናገረ። እነዚህን ትምህርቶች የጥበብ ቃል ብለን እንጠራቸዋለን።

ምስል
ሴት ልጅ እየተመገበች

የጥበብ ቃልን ለመኖር እችላለሁ። ሰውነቴን ስንከባከብ የሰማይ አባት ይባርከኛል።

የሚቀባ ገፅ

ሰውነቴን መንከባከብ እችላለሁ።

ምስል
ልጆች ገመድ እየዘለሉ

ሰውነታችሁን ለመንከባከብ ምን ታደርጋላችሁ?

ለማውረድ ስዕሉ ላይ ጠቅ ያድርጉ።

ስእል በኤፕረል ስቶት

አትም